ልጥፎች

የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር.....

ምስል
የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ መሰረት መሰረት ከአሁን በፊት የነበሩ እና ከዚህ በኋላ የማይቀጥሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች 1. የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ሚኒስቴር- በሰላም ሚኒስቴር ስር የተጠቃለለ 2. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት- በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክረተሪያት የሚተካ 3. የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር - የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተጠቃለሉ 4. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር- በአንድ ላይ የተዋሃዱ 5. የከተማ እና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር-ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የተዋሃዱ

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ያቀረቡት የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሕግ ተጠያቂነት.....

ምስል
ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ካልተወያየን በማለት ቤተ መንግሥት የገቡት የመከላከያ ሠራዊት ኮማንዶዎች፣ በፈጸሙት ድርጊት ምክንያት የሕግ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ተገለጸ፡፡ ወታደሮቹ ቡራዩ አካባቢ የተሰጣቸውን ፀጥታ የማስከበር ግዳጅ ከፈጸሙ በኋላ ነበር ወደ ቤተ መንግሥት ያቀኑት፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ሪፖርተር በስልክ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ወታደሮቹ ከግዳጃችን ከተመለስን ሁለተኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማግኘት ዕድል ስለሌለን፣ አጋጣሚውን ተጠቅመን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት አለብን በማለት ነው ተያይዘው የሄዱት፤›› ሲሉ አስረድተው፣ ‹‹አንደኛውና ትልቁ ነገር በዚህ ድርጊት ላይ ከተሳተፉት አካላት ጋር ሕገ መንግሥት እንደተጣሰ፣ አካሄዳቸው ስህተት እንደሆነና በዚህም ምክያት እንደተፀፀቱ መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ ድርጊቱ ስህተት ነው፡፡ በዚህ አግባብ መሄድ ለአገርም ሆነ ለተመልካችና ለኅብረተሰቡ ተገቢ አይደለም፡፡ በዚያ መንገድ መሄድ አልነበረብንም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሆኖም ለወደፊት በዝርዝር እየታየ ለምንድነው እዚህ ደረጃ ላይ የተደረሰው? በወቅቱ እዚህ ደረጃ ላይ ከመደረሱ በፊት በቅርበት ያለው አመራር እንዴት አላየም? ለሌላውስ እንዴት አላሳወቀም? የሚሉት ነገሮች ደግሞ በቀጣይ ይታያሉ፤›› ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያና በቡራዩ አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ከጦላይ፣ ከሶማሌ ክልልና ከተለያዩ ሥፍራዎች እንደመጡ የተነገረላቸው ኮማንዶዎቹ፣ ግዳጃቸውን ፈጽመው ወደ ጦር ሠፈራቸው እየተመለሱ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማግኘት ወደ ቤተ መንግሥት ከማቅናታቸው በፊት፣ ከግዳጅ ሥፍራቸው ሳይንቀሳቀሱ ሐሙስ መስከረም 2...

ትጥቅ አለመፍታት ቀይ መስመር ነው- የኢትዮጵያ መንግስት

ምስል
ከሰሞኑ በኦነግ ታጣቂዎች ጉዳይ እዚህም እዚያም ሲወረወር የነበረውን አድምጠናል የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዋልታ   ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስም በግልፅ ለህዝብ ቀርቧል ሊቀመንበሩ የትጥቅ መፍታትን ጉዳይ በተመለከተ የተናገሩትና የሰጡት አስተያየት አሻሚ ነው የተብራራ አይደለም እሳቸው ማለት የፈለጉትን ነገር እንደ መሪ በግልፅ መናገር መቻል አለባቸው ዳር ዳር ማለት ለትርጉም ያጋልጣል፤ሆኖ የተገኘውም ይኸው ይመስለኛል እነ አንቶኔ ደግሞ ይህቺን ነጥለው በማውጣት የኦሮሞን አንድነት ለማፍረስ ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል በአንድ አገር ውስጥ ሁለት መንግስት የለም ከማለት ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሲባል ሰንብቷል።የኦሮሞን አንድነት የማይፈልጉ ኃይሎች ይህቺን ክፍተት በደንብ ይፈልጓታል የኦሮሞ አንደነት ሲናድ ሾልከው በሚፈልጓት ቦታ ላይ ጉብ ለማለት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥርላቸው ርብርባቸውን አይተናል ታዝበናል።ኦነግ ለጅቦቹ ቀዳዳ በመክፈት ዳግም ታሪካዊ ስህተት መፈፀም የለበትም ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብም ሆነ አንደ ድርጅት ለኦነግ የሚበጀውና አማራጭ የሌለው መንገድ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተወያይቶና ተስማምቶ ወደ አገር የተመለሰበትን ስምምነት አጥብቆ በመያዝ መንቀሳቀስ ነው፤ከዚህ ውጪ ለመሄድ መሞከር አይጠቅምም ጎጂ ነው የኦነግ ሊቀመንበር   አቶ ዳወድ ኢብሳ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ትጥቅ ፈቱ መባልን አንፈልግም” ብለው ሲናገሩ ተሰምተዋል ይህ ምን ማለት እንደሆነ በግልፅ የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ናቸው ምክንያቱም ይህ ቃል የወጣው ከአንደበታቸው ነውና ኦነግም ሆነ ሌላው የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የቆየ ፓርቲ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ትጥቅ መፍታቱ ግድ ነው፤ምክንያቱም ትጥቅ ሳይፈቱ በሰላማ...

የደኢህዴን ጉባዔ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ

ምስል
ደኢህዴን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ። ደኢህዴን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ባለው ጉባዔ ነው ነባር አመራሮቹን በክብር ያሰናበተው። በዚህም መሰረት፦ 1. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ 2.አቶ ሽፈራው ሽጉጤ 3. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ 4. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ 5. አቶ ተክለወለድ አጥናፉ 6. አቶ ሳኒ ረዲ 7. አቶ ታገሰ ጫፎ 8. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን 9. ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም 10. አቶ ደበበ አበራ 11. አቶ መኩሪያ ሀይሌ 12. አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ 13. አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ 14. አቶ ተመስገን ጥላሁን 15. አቶ ወዶ ኦጦ 16. አቶ ያዕቆብ ያላ 17. አቶ ሰለሞን ተስፋዬ 18. አቶ ፀጋዬ ማሞ 19. አቶ ንጋቱ ዳንሳ 20. አቶ አድማስ አንጎ 21. አቶ ኑረዲን ሀሰን 22. አቶ ሞሎካ ወንድሙ 23. አቶ አብቶ አልቶ ናቸው ከማእከላዊ ኮሚቴው በክብር የተሰናበቱት። ከማእከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱት አባላት ከ17 እስክ 15 ዓመታት በተለያየ የሀላፊነት ደረጃ ያገለገሉ መሆኑም ተገልጿል። ጉባዔው በተጨማሪም ከድርጅቱ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አቶ ካሚል አህመድን በክብር አሰናብቷል። እንዲሁም የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ እስከ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በእግድ እንዲቆዩ አድርጓቸው የነበሩ አባላትንም ድርጅታዊ ጉባዔው አሰናብቷል። በዚህም መሰረት፦ 1. ወይዘሮ አማረች ኤርሚያስ 2. አቶ ሳሙኤል ደምሴ 3. ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ከድርጅቱ ተሰናብተዋል።

የመገለባበጥ አጀንዳ ግብ

አሁን ያለው ለውጥ የተገኘው በምንም ሳይሆን በትግል ነው፤የትግሉ ተዋናዮች ደግሞ ብዙ ናቸው ከውስጥም ከውጭም ያሉ የትግሉ ተሳታፊዎች አሁን በተጨባጭ ለሚታየው ለውጥ የማይናቅ አስተዋፅኦ አበርከተዋል።የመራራው ትግል ተሳታፊዎች በርካታ ስለሆኑ ለውጡን ያመጣሁት እኔ ነኝ የሚለው አካሄድ በምንም አይነት ምክንያት ተቀባይነት የለውም።ሁሉም እንደ አቅሙ ለለውጡ መገኘት የበኩሉን ሚና ስለተጫወተ ለውጡ በሁላችን ጥረት የመጣ ነው ብሎ ማመን ተገቢ ነው። ከለውጡ መገኘት በኋላ የመጣው ሂደት ይታወቃል፤አንዳንድ ኃይሎች ለውጡን የሚደግፉ መስለቀው በመቅረብ ህዝባዊውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚችሉትን ሁሉ ማድረጋቸው በተጨባጭ ታይቷል፤ነገር ግን ሙከራው ሁሉ ሳይሳካ ቀርቷል። የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች ዘርፈው   ባካበቱት የገንዘብ ኃይል ቅጥረኞችን በማሰማራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ ባለፈው ሰኔ ወር የግድያ ሙከራ ከማድረግ ጀምሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር በፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች ለማጣጣል ሰፊ ጥረት አድርገዋል፤ጥረታቸው ከንቱ ሆኖ ቢቀርም አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ። በለመዱት የማሸበር ልምድ ተጠቅመው ህብረተሰቡ አዲሱን አመራር አንዲጠራጠር፤እንዳይደግፍ፤እዲሱ አመራር ዳግም አንዳይመረጥ አጀንዳዎችን በመቀያየር አሁንም በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ፤ዋነኛው የመገለባበጥ አጀንዳው ግብ ይህ ነው። አዲሱ አመራር ህዝብ ታፍኖ ለአመታት የቆ በመሆኑ በዴሞክራሲያዊ አካሄዶች ፈታ ይበል ብሎ ሆደ ሰፊ ሲሆን ምቹ ሁኔታውን በመጠቀም በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም አንዲደፈርስ፤የሰዎች ሕይወት እንዲጠፋና ንብረት አንዲወድም አድርገዋል።የለውጡ አደናቃፊዎች መክረውና አሰልጥነው ያሰማሯቸው ሰዎች ለፖሊስ በሰጡት ቃል በገንዘብ ተቀጥረው የተሰማሩ መሆና...

‹‹ለረዥም ጊዜ አልመንና አስበን የጀመርነው ትግል በትንንሽ ሙከራዎች እንደማይደናቀፍ በጉባዔያችን ተረጋግጧል››

ምስል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የኦዴፓ ሊቀመንበር ከመስከረም 8 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በጅማ ከተማ ዘጠነኛው ጉባዔውን ያደረገው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በመሸጋገር፣ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ በኦዴፓ ጉባዔ ማጠናቀቂያ ላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት ያስተላለፉት የኦዴፓ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የፓርቲው ጉባዔ ለረዥም ጊዜ ታስቦበትና ታልሞበት የተጀመረው ትግል በትንንሽ ሙከራዎች እንደማይደናቀፍ ማረጋገጡን አስታውቀዋል፡፡   የድርጅቱ ሊቀመንበር ባስተላለፉት መልዕክት፣ ‹‹የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ድርጅታችን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ስሙን፣ ዓርማውን፣ ሕገ ደንቡን፣ አመራሩን፣ አመለካከቱንና አደረጃጀቱን 21ኛው ክፍለ ዘመን የሚጠይቀውን አመራር ለመስጠት በሚያስችለው ደረጃ ላለፉት አራት ቀናት በውቢቷ ከተማ ጅማ ያደረገው ዘጠነኛው ጉባዔ በድል ተጠናቋል፤›› ብለዋል፡፡ ድርጅቱ ስሙንና ዓርማውን ቀይሮ ብቻ ከዚህ ጉባዔ የሚወጣ የመሰላቸው በርካታ ሰዎች ቢኖሩም፣ በሚያስደንቅ ሁኔታ ላለፉት ሦስት ዓመታት የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ከነበሩ 81 ሰዎች መካከል አዲሱን አመራር እንዲቀላቀሉ ጉባዔው የጠቆማቸው 19 አባላት ብቻ እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለአዲሱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለማለፍ የቻሉት 16 ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ድርጅቱ የተማሩ፣ ለመምራት የተዘጋጁና ብቃት ያላቸው ወጣቶች ወደፊት በማምጣት ስያሜውን ብቻ ሳይሆን፣ የአመራር ብቃቱን ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለመውሰድ በሚያስችል ቁመና ራሱን ያዘጋጀና ያደራጀ በመሆኑ፣ ሌሎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታ...

Ibsa Ijjannoo Yaa’ii dhaabbatummaa ODP

ምስል
Ibsa Ijjannoo Yaa’ii dhaabbatummaa ODP Hirmaattota Yaa’ii dhaabbatummaa 9ffaan qophaa’e ---- Barri isaa fagoodha yaadannoon isaa ammoo dhiyoodha DhDUO kaleessaa, ODP hardhaa imala waggoota darbanii keessatti daandiin irra darbe kan injifannoon baayyeen itti galmaawan tahullee gufuuwwan isa mudataniis salphaa miti. Yaa ta’u malee duudhaan dhaloota isaarraa qabee Oromummaan dagaagfataatiifii qajeeltoo jireenya isaa godhachaa dhufe kufanii ka’uuf halaalatti quba qabuun dura quba ofitti qabanii of dhaggeeffatanii ofitti deebi’uun of ceepheessaa of haaroomsaa deemuudha. Seenaa kufanii ka’uutiif kan akka dubbii hanqaaquu yookiin killee caphaan alaa dhuftu du’a, caphaan keessaa futtaatu lubbuu akka taatee rakkoofii gaaga’ama hamaa hamma Ummanni Qabsoofnuuf duugda nutti gara galuu gahee turee yaadannoo yeroo dhiyooti. Paartiin keenya Qabsoo keessoo isaatti karaarraa maqnee karatti yaa deebinuu taasiseen bu’aan harra naannoo keenya bira dabree biyyaaf ifuu ...