ትጥቅ አለመፍታት ቀይ መስመር ነው- የኢትዮጵያ መንግስት


ከሰሞኑ በኦነግ ታጣቂዎች ጉዳይ እዚህም እዚያም ሲወረወር የነበረውን አድምጠናል የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዋልታ  ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስም በግልፅ ለህዝብ ቀርቧል
ሊቀመንበሩ የትጥቅ መፍታትን ጉዳይ በተመለከተ የተናገሩትና የሰጡት አስተያየት አሻሚ ነው የተብራራ አይደለም እሳቸው ማለት የፈለጉትን ነገር እንደ መሪ በግልፅ መናገር መቻል አለባቸው ዳር ዳር ማለት ለትርጉም ያጋልጣል፤ሆኖ የተገኘውም ይኸው ይመስለኛል
እነ አንቶኔ ደግሞ ይህቺን ነጥለው በማውጣት የኦሮሞን አንድነት ለማፍረስ ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል በአንድ አገር ውስጥ ሁለት መንግስት የለም ከማለት ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሲባል ሰንብቷል።የኦሮሞን አንድነት የማይፈልጉ ኃይሎች ይህቺን ክፍተት በደንብ ይፈልጓታል የኦሮሞ አንደነት ሲናድ ሾልከው በሚፈልጓት ቦታ ላይ ጉብ ለማለት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥርላቸው ርብርባቸውን አይተናል ታዝበናል።ኦነግ ለጅቦቹ ቀዳዳ በመክፈት ዳግም ታሪካዊ ስህተት መፈፀም የለበትም

ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብም ሆነ አንደ ድርጅት ለኦነግ የሚበጀውና አማራጭ የሌለው መንገድ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተወያይቶና ተስማምቶ ወደ አገር የተመለሰበትን ስምምነት አጥብቆ በመያዝ መንቀሳቀስ ነው፤ከዚህ ውጪ ለመሄድ መሞከር አይጠቅምም ጎጂ ነው
የኦነግ ሊቀመንበር  አቶ ዳወድ ኢብሳ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ትጥቅ ፈቱ መባልን አንፈልግም” ብለው ሲናገሩ ተሰምተዋል ይህ ምን ማለት እንደሆነ በግልፅ የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ናቸው ምክንያቱም ይህ ቃል የወጣው ከአንደበታቸው ነውና
ኦነግም ሆነ ሌላው የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የቆየ ፓርቲ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ትጥቅ መፍታቱ ግድ ነው፤ምክንያቱም ትጥቅ ሳይፈቱ በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ የሚባል ነገር የለም!
የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትጥቅ አለመፍታት ቀይ መስመር ነው ብሏል።የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሰሁን ጎፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኦነግ ወደ አገር የተመለሰው ትጥቁን ፈትቶ ነው በትግራይ በኩል ከኤርትራ ወደ አገር የተመለሱ፤የኦነግ ታጣቂዎችም ካምፕ አንዲገቡ ተደርጎ በስልጠና ላይ ይገኛሉ ብለዋል
የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለሚዲያ መግለጫ የመስጠት ልምድ ያላቸው አይመስሉም ትጥቅ ፈቱ መባልን አንፈልግም ብለው የተናገሩት ነገር የተወለካከፈ ነው በአንዳንድ ነገሮች ላይ መንግስት ግልፅ አላዳረገም ይላሉ እንጂ አቶ ዳውድ ራሳቸው የሚሉትም ግልፅ አይደለም
ለህዝብ ሲሉ ሁሉንም ግልፅ ያድርጉት፤ለማንኛውም መልካሙ ነገር አቶ ዳውድ በሰጡት ቃል ኦነግ ወደ አገር የገባው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ከመንግስት ጋር ተስማምቶ ነው ብለዋል።በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ ትጥቅ ይዞ እንዳልሆነ አቶ ዳውድ በደንብ ያውቃሉ ማለት ነው።ትጥቅ አለመፍታት ቀይ መስመር ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa