መክነው የቀሩ ሶስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች
ሰፊው ሕዝብ ለውጡን ይፈልጋል፤ለውጡ እንዳይቀለበስበትም ብርቱ ፍላጎት አለው።ሕዝብ ለውጡ እንዳይቀለበስ
ከፍተኛ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል የለውጡ ጠባቂና ዘብም ሰፊው ህዝብ መሆኑ እየታየ ነው።ይህ ባይሆን ኖሮማ አዲሱ አመራር አገርን
የማስተዳደር ኃላፊነት ከተረከበ ወዲህ ብቻ የተሞከሩ ሦስት የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎች ሳይሳኩ መክነው አይቀሩም ነበር፤ሶስቱ የመንግስት
ግልበጣ ሙከራዎች በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው
1ኛ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ቦምብ በማፈንዳት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን
የመግደል ሙከራ
2ኛ መስከረም 2 እና 3 ቀን 2011 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ የተፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት እንቃወማለን
በሚል ሰበብ መስከረም 7 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደ ሰልፍ
3ኛ ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ጋር ካልተወያየን በማለት ተንጋግተው ቤተ መንግሥት የገቡት የመከላከያ ሠራዊት ኮማንዶዎች ሙከራ ናቸው።
እነዚህ በተለያዩ ወቅቶች በኢትዮጵያ
የታዩ የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎች ሙሉ በሙሉ የመከኑ ሳይሳኩ የከሸፉ ሙከራዎች ናቸው፤የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎቹ አንዲደረጉ ከኋላ
ሆነው ያቀዱ ያስተባበሩ በገንዘብ የደገፉና የፈፀሙ ኃይሎች ሁሉ ከማንም ብሄር ብሄረሰብና ህዝብ የወጡ ይሁኑ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች
ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው፤ይህ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል!
የሙከራው አድራጊዎች የኢትዮጵያ
ህዝቦች የወደዱትንና የደገፉት አመርቂ ለውጥ ለመቀልበስ አስበውበትና
ተዘጋጅተውበት የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው ምክንያት መቼም ቢሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጠላቶች ናቸው።
ከሙከራዎቹ አንዱ እንኳ ቢሳካ ኖሮ
አሁን በዚህ አይነት ሁኔታ ስለ መንግስት ግልበጣ ሙከራዎቹ ጉዳይ መነጋገርና ማውሳት በፍፁም አይቻልም፤ጠላቶቻችን እንድንበላላ፤ድግሰውለን
ነበር ድግሳቸው ውሃ ጠጣ ተበላሸባቸው።
ለዓላማቸው ከግብ መድረስ እስከ
አሁን ጠላቶቻችን የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፤ህሊና የላቸውምና ጠላቶች ሌላ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ያደርጉ ይሆናል።እኛ ግን እንላለን
ክንዳችን ሃያል ነው የማትችሉትን አትሞክሩ፤ለውጡን መቀልበስ የሚሞክር እንጂ ለውጡን መቀልበስ የሚችል አንድም ኃይል በምድራችን
ላይ የለም!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ