አሥር ሴቶች የተካተቱበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ...
አሥር ሴቶች የተካተቱበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ካቢኔ በፓርላማ ፀደቀ
ከአፈ ጉባዔነታቸው መልቀቂያ አቅርበው በተነሱት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሚመራው አዲሱ የሰላም ሚኒስቴር ሰላምና የሕግ የበላይነት በኢትዮጵያና በአካባቢው አገሮች ለማስፈን እንዲሠራ የተመሠረተ መሆኑ ሲገለጽ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)፣ የፌዴራል ፖሊስና የፋይናንስ ደኅንነት መረጃ ማዕከልን በበላይነት ይመራል፡፡ ከዚህ ቀደም የቀድሞው የፌዴራልና የአርብቶ አደር ጉዳዮች ልማት ሚኒስቴር የነበረውን ሥልጣንና ተግባር ይረከባል፡፡
እንደ አዲስ ለተዋቀረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ብቃት አላቸው ተብለው የተመደቡት ሚኒስትሮች ሹመት፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በፓርላማው ሙሉ ድምፅ ይሁንታ አግኝቶ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ የካቢኔ አባላቱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የሰላም ሚኒስቴር - ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
2. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር - ወ/ሮ አይሻ መሐመድ (ኢንጂነር)
3. የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር - አቶ አህመድ ሺዴ
4. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ - አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
5. የግብርና ሚኒስቴር - አቶ ኡመር ሁሴን
6. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር - ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር
7. የገቢዎች ሚኒስቴር - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
8.የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር - ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር)
9.የትራንስፖርት ሚኒስቴር - ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
10.የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር - አቶ ዣንጥራር ዓባይ
11. የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር - ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር)
12. የትምህርት ሚኒስቴር - ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር)
13. የማዕድና ነዳጅ ሚኒስቴር - አቶ ሳሙኤል ሆርቆ
14. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
15. የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር - አሚን አማን (ዶ/ር)
16. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር - ሒሩት ወልደ ማርያም (ዶ/ር)
17.የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር - ወ/ት የዓለም ፀጋይ አሰፋ
18. የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
19. የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር - ሒሩት ካሳው (ዶ/ር)
20. የፕላንና የልማት ኮሚሽን - ወ/ት ፍፁም አሰፋ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ