ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዛሬው እለት ወደ ሃገራቸው ገቡ

በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዛሬው እለት ወደ ሃገራቸው ገቡ።
ኮሎኔል ጎሹ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የቀድሞው ሚኒስትር በቦሌ አለም ዓቀፍ አየር መንገድ በሰጡት መግለጫ የደርግን አገዛዝ በመቃወም ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው በመልቀቅ ላለፉት 32 አመታት ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገው መቆየታቸውን ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ያለውን አጠቃላይ የለውጥ ሂደት ለመመልከት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅና የተጀመረውን የሰላም፣ የፍቅርና የመደመር ሂደት በሚችሉት መጠን ለመደገፍ ወደ ሃገራቸው መምጣታቸውንም አንስተዋል

Source:FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa