ከፊንፊኔ ውጡልኝ የሚል አንድም ኦሮሞ የለም!
የኦሮሞ ብሄር አቃፊ ነው
ኦሮሞ የአግላይነት ባህሪ የለውም ኦሮሞ አቃፊ ለመሆኑ የጉዲፈቻ ስርዓቱ ዋነኛ ማስረጃ ነው ይህ ታላቅ ህዝብ ለዘመናት ተገፊ አንጂ
ገፊ ሆኖ አያውቅም
ኦሮሞ አሁንም ወደፊትም
ሌላውን የመግፋት ዓላማ የለውም ሊኖረውም አይችልም ተፈጥሮው አይደለማ፤በፊት የሌለውን ባህሪ አሁን ከየት ሊያመጣ ይችላል?
የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ጉዳይ
ሲነሳ ብዙዎች ያለምንም ተጨባጭ ምክንያት ይደነባበራሉ፤ይህ መሆን የሌለበት ነው በቅርቡ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች
ስለ ፊንፊኔ/ አዲስ አበባ መግለጫ አወጡ ተብሎ ያልተባለ ነገር የለም ማለት ይቻላል
ፊንፊኔ/አዲስ አበባ የኢትዮጵያ፤የአፍሪካ
አህጉርና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መዲና ናት።ሁሉም ኦሮሞ በዚህ ይኮራል አንጂ አያፍርም፤ፊንፊኔ ወደፊትም የብዙዎች መዲና
ሆና ትቀጥላለች
ፊንፊኔ/አዲስ አበባ የፌዴራል
መንግስት መቀመጫ፤የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ፤የብዙ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ ሆና መቀጠሏ ላይ ማንም
መጠራጠር የለበትም አይገባም!
ፊንፊኔ/አዲስ አበባ የአሁን
ቅርፅዋን ከመያዝዋ ከ130 ዓመታት በፊት የኦሮሞዎች መኖሪያ ነበረች ይህን መካድ አይቻልም ተጨባጭ ማስረጃዎች አሁን ድረስ ስላሉ ኦሮሞና ፊንፊኔ/አዲስ አበባን መለያየት የሚቻልበት ሁኔታ በፍፁም የለም አስከ
አሁን ድረስ በኦሮሞ ስያሜዎች የሚጠሩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኦሮሞ መኖሪያ ባትሆን ኖሮ አይሰየሙም ነበር፤ጉለሌ፤ቦሌ፤ቡልቡላ…..ከየት
መጡ?ከኦሮሞ ስያሜ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው
አሁን በፊንፊኔ/አዲስ አበባ
ዙሪያ የሚኖሩ ኦሮሞዎች የቀድሞ ስርዓቶች በፈጠሯቸው የተለያዩ ምክንያቶችና
በጉልበት ከመሃል አዲስ አበባ ተገፍተው የወጡ ናቸው፤የዚህ ፅሑፍ ፀሃፊ አያቶች የእርሻ መሬት ፍለጋ አሁን ካራ ቆሬ ከሚባል የአዲስ
አበባ አካባቢ ወደ አርሲ አሰላ አካባቢ አንደተሰደዱ ያውቃል።
ስለዚህ ፊንፊኔ በአሁኑ ተጨባጭ ሁኔታ ኦሮሞን ጨምሮ የብዙዎች መኖሪያ ናት፤እኔ አንጂ ኦሮሞ እዚህ
ድርሽ አይልም ማለት በፍፁም አይቻልም፤ከኦሮሞም አንድም ኦሮሞ ከፊንፊኔ ውጡልኝ የሚል የለም!ተሰሚነትን ለማግኘት ሲባል ብቻ የፊንፊኔ/አዲስ
አበባን ጉዳይ ማጦዝ ይቁም!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ