የመገለባበጥ አጀንዳ ግብ
አሁን ያለው ለውጥ የተገኘው በምንም ሳይሆን በትግል ነው፤የትግሉ ተዋናዮች ደግሞ ብዙ ናቸው ከውስጥም ከውጭም ያሉ
የትግሉ ተሳታፊዎች አሁን በተጨባጭ ለሚታየው ለውጥ የማይናቅ አስተዋፅኦ አበርከተዋል።የመራራው ትግል ተሳታፊዎች በርካታ ስለሆኑ
ለውጡን ያመጣሁት እኔ ነኝ የሚለው አካሄድ በምንም አይነት ምክንያት ተቀባይነት የለውም።ሁሉም እንደ አቅሙ ለለውጡ መገኘት
የበኩሉን ሚና ስለተጫወተ ለውጡ በሁላችን ጥረት የመጣ ነው ብሎ ማመን ተገቢ ነው።
ከለውጡ መገኘት በኋላ የመጣው ሂደት ይታወቃል፤አንዳንድ ኃይሎች ለውጡን የሚደግፉ መስለቀው በመቅረብ ህዝባዊውን
ለውጥ ለማደናቀፍ የሚችሉትን ሁሉ ማድረጋቸው በተጨባጭ ታይቷል፤ነገር ግን ሙከራው ሁሉ ሳይሳካ ቀርቷል።
የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች ዘርፈው ባካበቱት የገንዘብ
ኃይል ቅጥረኞችን በማሰማራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ ባለፈው ሰኔ ወር የግድያ ሙከራ ከማድረግ ጀምሮ
የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር በፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች ለማጣጣል ሰፊ ጥረት አድርገዋል፤ጥረታቸው ከንቱ ሆኖ ቢቀርም አሁንም ተስፋ
ባለመቁረጥ በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ።
በለመዱት የማሸበር ልምድ ተጠቅመው ህብረተሰቡ አዲሱን አመራር አንዲጠራጠር፤እንዳይደግፍ፤እዲሱ አመራር ዳግም
አንዳይመረጥ አጀንዳዎችን በመቀያየር አሁንም በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ፤ዋነኛው የመገለባበጥ አጀንዳው ግብ ይህ ነው።
አዲሱ አመራር ህዝብ ታፍኖ ለአመታት የቆ በመሆኑ በዴሞክራሲያዊ አካሄዶች ፈታ ይበል ብሎ ሆደ ሰፊ ሲሆን ምቹ ሁኔታውን
በመጠቀም በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም አንዲደፈርስ፤የሰዎች ሕይወት እንዲጠፋና ንብረት አንዲወድም አድርገዋል።የለውጡ አደናቃፊዎች
መክረውና አሰልጥነው ያሰማሯቸው ሰዎች ለፖሊስ በሰጡት ቃል በገንዘብ ተቀጥረው የተሰማሩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፤ጫኝ አውራጅ
ከሆነ ሰው የባንክ አካውንትም 8 ሚሊየን ብር መገኘቱ ተረጋግጧል።ከህዘብ በተገኘ ገንዘብ ህዝብን መጉዳት መቼም ቢሆን ተመራጭ
አያደርግም።ከአሁን በኋላ ለየትኛውም የለውጥ አደናቃፊ ኃይል ለውጡን የማደናቀፍ ጥረት አይሳካም መክኖ ይቀራል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ