ከአቶ በረከት ስሞን ውትውታ በስተጃርባ


ከሰሞኑ አቶ በረከት ስሞን የአገር ውስጦቹን ጨምሮ የውጭ ሚዲያዎችን በመግለጫ አጥለቅልቀዋል፤በመግለጫዎቹም አርቲ ቡርቲውንም ነግረውናል እኛም ሰምተናል መልካም ነው።ነገር ግን አቶ በረከት ስሞን ምን እያሉን እንደሆነ አስተውለን ይሆን?
ቀደም ሲል ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት መግለጫ ለመስጠት ሚዲያዎችን የሚያማርጡ ግለሰብ አሁን ምን ተገኝቶ ይሆን በዘመቻ መልክ መግለጫዎችን ደራርበው በላይ በላዩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች ለመስጠት የተገደዱት?

እመኑኝ ባልልም እኔ ይህን አምናለሁ አቶ በረከት አይወድቁ አወዳደቅ ወድቆ ከተፈጠፈጠውና ለውጡን ለመቀልበስ እየተፍጨረጨረ ካለው ኃይል ብርቱ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል
ምክንያት፡አቶ በረከት ከቅርብ አመታት ወዲህ የጠቅላይ ሚኒስትር የፖሊሲ አማካሪ ሆነው ቢቆዩም ቀደም ባሉት ዓመታት ከማስታወቂያ ሚኒስትር ጀምሮ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፤የሁሉም ነገር ዘዋሪ አንደሆኑም ይታወቃል
ሰውዬው በእነዚህ የኃላፊነት ቆይታቸው ወደ ተለያዩ ሚዲያዎች ቀርበው የመናገርና የማሳመን ችሎታ አዳብረው የቆዩ በመሆናቸው በቀን ጅቦቹ ተመርጠው ተልዕኮውን ተቀብለው ኃለፊነታቸወን በመወጣት ላይ ይገኛሉ
“ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋ ድስት ጥዶ ማልቀስ”እንዲሉ አቶ በረከት ነገር ሁሉ ካለቀ በኋላ አሁን የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተው እየቆሰቆሱ ያለቃቅሱብናል፤በርካታ የኢህአዴግ አባላት በተለይም ከታች የሚገኙት በየመድረኩ ድርጅታችን ተበላሽቷል እረ ተው እንስተካከል ብለው ሲወተውቱ አቶ በረከት በማን አለብኝነት ዝም ብለው ለምን ቆዩ?
አቶ በረከት አሁን እያደረጉ ያሉት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” የሚለውን ብሂል ያስታውሰናል።አይ በርዬ ደግሞ ዘና ብለው “አልተደመርኩም አልተቀነስኩም” ይሉናል?እርስዎ በእኩይ ተግባርዎት ምክንያት ሊደመሩ አይችሉም ሲያምርዎ ይቀራል!ላለመቀነስዎም ምንም አይነት ዋስትና የለዎትም!
ለውጡን አነ ማን እንደሚደግፉና አነ ማን ደግሞ እንደሚቃወሙ አፍረጥርጠው እንደሚናገሩ በመግለጫዎችዎ ገልጠውልናል፤ይህ የተለመደው የማባላትና የማጋጨት ስልትዎ እንደሆነ በደንብ ስለሚታወቅ በአሁኑ ወቅት የሚሞኝልዎት አካል የሚኖር አይመስለኝም።ብቻ እርስዎ የተሰጥዎትን ተልዕኮ ይወጡ ብርታቱን ይስጥዎት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው የተጀመረው ለውጥ በእርስዎና መሰሎችዎ ጥረትና መፍጨርጨር አይቀለበስም!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa