ልጥፎች

የኮሮና ሪፖርትና ቆሻሻው ልምምድ

የኢትዮጵያ ከተገለጸ በኋላ በትግራይ ክልል የሚለው ሌላ መግለጫ ችግሩ የማንም ይሁን ያልተገባ ልምምድ ነው፡፡ ሀገር ነን፤ ለህዝብ ክብር ስትሉ ተቀናጁ፡፡ የኮሮና ጉዳይ ሀገራዊ ብቻ አይደለም እንደውም በዓለም ደረጃ የዓለም የጤና ድርጅት ምድርን የተመለከተ አቃፊ ሀሳቦች መረጃዎችና ጉዳዮችን እውን የሚያደርግበት የምድር ቀውስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ መረጃዎችን ብሔራዊ በሆኑ ተቋማት በኩል ስትሰጥ ቆይታለች፡፡ ዘግይተውም ቢሆን ክልሎች የጀመሩት የምርመራ ስራ ውጤቱ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ተቀናጅቶ በጤና ሚኒስትር በኩል ሲነገር ቆይቷል፡፡ አሁንም ቢሆን የሁሉም ክልሎች ውጤትና የኮሮና ወቅታዊ ሁኔታ በማዕከላዊነት በጤና ሚኒስትር በኩል እየተገለጸ ነው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ የሃያ አራት ሰዓት መረጃ ይፋ ከሆነ በኋላ የትግራይ በሚል ሌላ ቁጥር ተነግሯል፡፡ ይሄ ፖለቲካ አይደለም፤ የሰው ህይወትና የሀገር ትርጉም ነው፡፡ ችግሩ ከየቱም ወገን ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንዲህ ያለ ቆሻሻ ልምምድ ግን በኢትዮጵያ ምድር ሊኖር አይገባም፡፡ ይሄንን እንደ ህዝብ ልንቆጣው ይገባናል ምክንያቱም ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ውጤቱ ሳይደርስ የትግራይ ሪፖርት የሚዘገይበት አግባብ ካለ የፌዴራሉን ሪፖርት አዘግይቶ የሃያ አራት ሰዓቱን ሪፖርት አንድ ላይ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ አሊያ ደግሞ ሁሉም ክልሎች በራሳቸው ሚዲያና አግባብ መረጃውን እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡ ኢትዮጵያና ትግራይ ማለት ምን አገባኝ ባይነት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡ ነውርም ጭምር፤ ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እንዲህ ያሉ ልምምዶች ፖለቲከኞችን ያሰክራሉ፤ ክፉና ስውር ደባ ያላቸው ሰዎች ልምምዱን ወደ መጥፎ ልዩነት ይዘውት ይጓዛሉ፡፡ በትግራይ የሚደረገው የማዕከላዊ መንግስቱ ኮሮናን የመከላከ...

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ስርዓትን በመጠቀም ሊፈፀም የነበረ የ110 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ማጭበርበር እና ዘረፋ ወንጀል ከሸፈ

ምስል
በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማጭበርበር እና ዘረፋ ወንጀል ማክሸፉን ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ስርዓትን በመጠቀም 110 ሚልዮን ዶላር የማጭበርበርና የዘረፋ የወንጀል ሙከራ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በመግለጫው ተጠርጣሪዎቹ ነዋሪነቱ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሆነው ኒል ቻርለስ የተባለ ግለስብ ስም በባንክ የተቀመጠ 110 ሚሊየን ዶላርን የባንክ ሂሳብ ባለቤቱ እንዳዘዘ አስመስለው አዲስ አበባ ከተማ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ተብሎ ከሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማውጣት የተለያዩ የማጭበርበር ስልቶችን ሲያቀናጁ እንደነበር አስታውቋል፡፡ ይሁንና ህገወጥ የገንዘብ ማዘዋወርና ዘረፋ ወንጀሉ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ስር የነበረ በመሆኑ፤ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር 60 ሚሊየን 990 ሺህ 939 ብር ከተጠቀሰው ባንክ አውጥተው በማዳበሪያ ጭነው በአዘጋጁት ተሸከርካሪ ሊወስዱ ሲሉ እዚያው ባንክ ውስጥ እያሉ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ ወንጀሉን በማቀነባበር ከሚታወቁት መካከል አድይሚ አድርሚ አብዱልራፊ (Adeymi Aderemi Abdulrafiu) የተባለ ናይጄሪያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሸገር እንግዳ ማረፊያ በቀን 450 ብር እየከፈለ ከአንድ አመት በላይ በመቀመጥ ተልእኮውን ለማስፈጽም ሲንቀሳቀስ እንደነበር ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲያካሂድ በነበረው ክትትል አረጋግጧል፡፡ ይኸው ግለሰብ ተልእኮውን ለማስፈጸም ዓለም አቀፍ ኤቲም ካርድ ያዘጋጀ ሲሆን፤ገንዘቡንም ከአሜ...

የፒኮክ ፖለቲካ ምንጭ የአጀንዳ እጦት ነው!

“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ይላል ያገሬ ሰው።ግራ የገባቸው አንዳንድ የፖለቲካ ሐይሎች የፒኮክን ምስል ከቤተመንግስት ለማስነሳት ፊርማ እየሰበሰብን ነው ሲሉ ሰማን፤ጉድ ነው! እነርሱስ አጀንዳ በማጣት ግራ ገብቶአቸው ነው።ገራሚዎቹ እሺ ብለው የሚፈርሙላቸው ናቸው።ቤተ መንግስት የተገነባውን የፒኮክ ወፍ ምስል ልናስፈርስ ነው ይፈርሙሉን ተብሎ ሲጠየቅ ይገርማል። መታወቂያችን አንበሳ ነው!(የንጉሳዊያን ነው)።ስልጣን በዘር የሚተላለፍበት።የፒኮክ ፖለቲካን በማራማድ ላይ የሚገኙ ሐይሎች ምን እያሉን እንደሆነ ግልፅ ነው። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ይህን ያረጀና ያፈጀ የበሰበሰ የገለማ አስተሳሰብ በፍፁም እንደማይቀበሉት መረዳት አለመቻል ድንቁርና ነው። ለማንኛውም የፒኮክ ፖለቲካ ምንጭ የአጀንዳ እጦት ነው! ለማለት ያህል ነው።በኮቪድ 19 ጊዜ ይህን የፒኮክ ፖለቲካ በመቀበል የሚነጉድ ወገን ካለ እርሱ አልገባውም።ፒኮክዬ እምር ብለሽ ለዘላለም ኑሪ!

invastimantii Oromiyaa caalmatti cimsuuf qajeelfamni dambii haaraan ba'ee hojiirra ooluu eegaleera

ምስል
Finfinnee Eebila 15/2012(TW) Sochii misooma invastimantii Oromiyaa caalmatti cimsuuf qajeelfamni dambii haaraan bahee hojitti galameera- Komishiinara komishiinii Invastimantii naannoo Oromiyaa Obbo Hayluu Jaldee. Sochii misooma invastimantii bu’a qabeessa ta’e lafa qabsiisuuf qajeelfama danbii haaraa boordiin mirkanaa’ee hojitti galamuu isaa obbo Hayluu Jaldee ibsa guyyaa har’aa miidiyaaleef kennaniin ibsaniiru. Dambiin haaraan kun karaa Qonnaan bulaa fi Horsiisee bulaa fayyadamaa taasisuu da nda’uun tumamuu isaa kan dubbatan Obbo Hayluu Abbootii qabeenyaa sadarkaan jiran hojitti galchuu keessattis xiyyeefannoon kan itti kenname ta’uu dubataniiru.Qajeelfama kana keessatti facaatii tajaajiltummaa seektaroota gara garaa keessatti argaman gara tokkotti fiduun tajaajila iddoo tokkoo akka argataniiif haala kan mijeessudha jedhan. Qonnaan Bulaa fi Horsiisee Bulaa karaa liizii fi kiraa irraa bilisa ta’een gara invastimantiitti galchuu fi Lafti Qonnaan bulaa invastima...

Ogeessoota fayyaa kana hunda Koronaadhaan dhabuun nama gaddisiisa

Kanneen kun hundumtuu Vaayirasii Koronaa dhabamsiisuuf wayitacarraaqanitti lubbuusaanii marartuu kanneen dhabanidha jedheera The Independent Seenaa gabaanaa namoota kanaa dubbisaa: https://www.independent.co.uk/news/uk/home-news/coronavirus-nhs-workers-deaths-healthcare-a9476861.html

ሰውዬውን የያዘው ጋኔን አሁንም አለበት!

ምስል
ለውጡ መጣሁ መጣሁ ሲል በነበረበት ወቅት ከሶስት አመታት በፊት በነበረው የስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ በሚሰጠው መግለጫ ከአንደበቱ የሚወጡ ቃላት ለከት አልነበራቸውም። የኦሮሞ ወጣቶች(ቄሮዎች) ሲያደርጉት የነበረውን ትግል ሲያንቋሽሽ ነበር፤እንዲያውም "የያዛቸው ጋኔን ሲለቃቸው ተቃውሞው ይቆማል" ብሎ በምፀት ተናግሯል። ተቃውሞው ሲበረታበት ለከት በሌለው አንደበቱ በአደባባይ ያለውን ለማስተባበልና ይቅርታ ለመጠየቅም ተገድዶ እንደነበር ይታወሳል። ጌታቸው ረዳ አሁንም በጋኔን ተይዞ ተጠፍንጎ እንዳለ ከአንደበቱ የሚወጡ ቃላት ማረጋገጫ ናቸው። ይህ ሰው የጥላቻ ንግግር ህግን በመጣስ ላይ ይገኛል።በአደባባይ ባለስልጣናትን በስም እየጠራ" ወፈፌ" እያለ ሲሳደብ ታይቷል፤ተሰምቷል። ለነገሩ ተስፋ ከቆረጠ ሰው የሚጠበቀውን ነው በማድረግ ላይ የሚገኘው።ጌተቸው ረዳን ጨምሮ ሸሽተው መቀሌ የገቡ የቀድሞ ባለስልጣናት(ይህን አገላለፅ አምርረው ይጠሉታል) በሚሰጧቸው የሚዲያ ቃለ መጠይቅ ውስጥ የሚነበብ ቁጭትና መንገብገብ ይታያል።እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም! ለኦሮሚያ መሬት ዘረፋ ተጠያቂው የኦሮሞ ባለስልጣናት ናቸው ብሎ እንደ ገደል ማሚቱ ለአመታት የተባለውን በመደጋገም ላይ የሚገኘው ጌታቸው ረዳ እርሱና መሰሎቹ በኦሮሚያም ሆነ በሌሎቹ የአገራችን ክፍሎች የተሰራው ወንጀል ሁሉ አዘጋጅና አሰተባባሪ አቀናባሪ ራሳቸው መሆናቸውን ዘንግተዋል።"የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለረመዳን ጾም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ምስል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ የሚጀመረው የረመዳን ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዚህ ዓመት የረመዳን ወር የሚውለው ዓለም በኮሮና በተጠቃችበትና ወረርሽኙን ለመከላከል አለመጨባበጥ፣ መራራቅና በቤት መወሰን ዋና የመከላከያ መንገዶች ሆነው በመላው ዓለም በሚተገበሩት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡ ነብዩ መሐመድ የወረርሽን መስፋፋት ለመከላከል ካስተማሩት አንዱ የሰዎችን እንቅስቃሴዎች መገደብ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ “ንጽሕና የእምነት ክፍል ነው በማለት ነብዩ እንዳስተማሩት የራሳችንን፣ የቤተሰባችንን፣ የአካባቢያችንን ንጽሕና በመጠበቅ ኮሮናን በእምነትም በምግባርም እንከላከለው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡ “የረመዳን ወር አንዱ ትልቅ እሴት ዘካና ሰደቃ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሌሎች ማካፈል፣ ለሌሎች መትረፍ መቻል ነው፣ ለሌሎች የሚሰጥ በጎ ነገር ለሰጪው ደስታን፣ ለተቀባዩ ደግሞ የኑሮ ድጋፍን የሚያስገኝ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ የዚህ ዓመት ዘካችንና ሰደቃችን ንግዳቸው የተቀዛቀዘባቸው፣ የቤት ክራይ የሚከፍሉትን ላጡ፣ የትምህርት ቤት ክፍያን ለመክፈል የተቸገሩ፣ ልጀቻቸውን ለመመገብ የከበዳቸውን እንዲያስባቸው እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡ ረመዳን የመጣው በሚያስፈልገን ጊዜ ነውና ለወቅታዊ ችግራችን መፍቻነት እንጠቀምበት፤ ለመልካም ስራ ተሽቀዳደሙ በማለት ቁርዓን እንዳስተማረን እገዛችንን ከሚፈልጉ ወገኖቻችን ጎን ለመቆም እንሽቀዳደም፣ የገንዘብ አቅም የሌለን ሰዎች ሁሉ በመልካም ተግህባር ሁሉ እንሰማራ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡ ረመዳን የመሰባሰቢያ ወቅት መሆኑን ሁላችንም የሚንገነዘብ ቢሆንም ያለንበት ወቅት ይህን እን...