ልጥፎች

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከላዊ ኮሚቴአቸውን ማሰልጠን መብታቸው ነው!

ምስል
  ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴአቸው በመደመር ፍልስፍና ላይ ያተኮረ ስልጠና ለምን ሰጡ? የስልጠናው ሂደትም ለምን በሚዲያዎች ተላለፈ? የሌሎች ፓርቲዎች ስልጠና እንዲተላለፍ ይደረጋል? የሚል ኡኡታ ተሰምቷል ኡኡታው በዚህ ደረጃ ከማልጠብቃቸው ግለሰቦችና ዩቱበሮች ጭምር መሰማቱ አስገርሞኛል፤ከሰሞኑ ከኢሳት ተለይተናል ብለው ዩትዩብ ከፍተው ስለ አገራቸው መልካም ጉዳዮቸ ላይ ሲወያዩ የሰነበቱ ሰዎች በዚህ ጉዳይ እንዲህ መንጨርጨር ይጠበቅባቸዋል? ጎ ፈንድሚዋ በዚህ ሙቀት ትጨምራለች፤የወዳጆች ቁጥርም በሽበሽ ይሆናል ብለው ካሰቡ በጣም ተሳስተዋል፤ለእናንተ ወቅታዊው ሙቀት ሳይሆን ዘላቂው ጥቅም ይበልጥባችኋል፤ለነገሩ ሲሳይ አጌና መኖሩ መልካም ነው ነገሩን ሚዛናዊ በማድረግ ከአደጋ ይጠብቃችኋል ብልፅግና ፓርቲ የምርጫው አሸናፊ ሆኖ አገራችንን እስከ አስተዳደረ ድረስ በአገሪቱ ሚዲያዎች ተጠቅሞ የስልጠናው ይዘትም ሆነ ሌላ ጠቃሚ ጉዳይ ለሰፊው ህዝብ እንዲደርስለት ቢያደርግ ምን ችግር አለው? ሌሎች ፓርዎችም አቅም ኖሮአቸው ለተከታዮቻቸው ስልጠና ሰጥተው በመገናኛ ብዙሃን ቢተላልፍላቸው ምንም ችግር ያለው አይመስለኝም፤ደግሞም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚሰጠችው መግለጫዎች፤የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በመገናኛ ብዙሃን እየተላለፈላቸው ነው አቅም አዳብረው እንደ ብልፅግና የሚሰጡት ስልጠና በሚዲያ ለተከታዮቻቸው ቢተላለፍ አንዳችም የሚፈጥረው ችግር የለም የሚል እምነት አለኝ

Ibsa Mootummaa Naannoo Oromiyaarraa kenname.

ምስል
  Tarkaanfiin shororkeessitoota qulqulleessuu cimee itti fufa! Ibsa Mootummaa Naannoo Oromiyaarraa kenname guutuunsaa kunooti: Humni shororkeessaa, shaneen, jaarmiyaa siyaasaa akeekaa fi kaayyoo dantaa sabaa ka’umsa godhate kan hin qabne ta’uu isaanitiif gocha hammeenyaa waggoottan afran darban ummata Oromoorratti raawwateen mirkaneesseera.   Tarkaanfii qindaa’aa tibba kana irratti fudhatamaa jiruun kan guyyaan itti dukkanaa’e hoggantoonni humna shororkeessaa kanaa qabatamaatti waan dhalli namaa namarratti hin raawwanne ummata Oromoorratti raawwachaa kan turaniifi jiran  ta’uu ofumaan ragaa ofirratti bahuu eegalaniiru. Daataan ummata Oromoo afaan qawween osoo hin taane, caalmaa yaadaa fi yaadamaa siyaasaa dirree demokraasii keessatti dhalatuun mirkanaa’aa waan ta’eef, humni kun qabsoo karaa nagaatti akka  deebi’u  yaalii bal’aan taasifamaa turee jira. Waamichi qabsoo karaa nagaa kun Mootummaadhaan alattis  ummata Oromoo hundarraa dhiyaachaa kan ture ta’ulle...

የሁላችንም አሻራ የሚፈልገው የሰላም ጉዳይ...

ምስል
  ሰላም በገንዘብ ሊተመን የማይችል ፣በወርቅም ሆነ በአልማዝ ልንመዝነው የማንችል፣ሩቅ ሄደን ማግኘት የማንችል ይልቁንስ በእያንዳንዳችን የእጅ መዳፍ ውስጥ የሚገኝ ማህበራዊ ሀብት ነው፡፡ ይህንኑ ሰላማችን ደግሞ መጠበቅ ከእያንዳንዳችን ዜጋ የሚጠበቅ ሀላፊነት እንጂ የግድ መንግስት ያሰማራው የፀጥታ ሀይል አባል መሆን አይጠበቅብንም፤በዜግነታችን ብቻ ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡ በለውጦች መካከል ሰላማችንን ሊያደበዝዙ የሚችሉ አጋጣሚዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ዋልታዎች ድረስ በሁሉም አቅጣጫ የሰላምን አየር ከመተንፈስ ይልቅ ለዘመናት በፍቅርና በአንድነት ከኖረው ህዝብ ይልቅ በህዝብ ጭንብል የራሳቸው ክብርና ዝና ለማግኘት ፀብ አጫሪ ንግግሮችን በመናገር፣የተዛቡ ፅሁፎችን በመፃፍ፣ምስሎችን በማህበራዊ ሚዲያዎች በመለጠፍ ህዝብ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን አለፍ ሲልም ቂም በማስያዝ ወደ ግጭት እንዲያመራ የሚሰሩ እፉኝቶች መኖራቸው ጥርጥር የለውም፡፡ 40ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት ሮናልድ ሬገን በአንድ ወቅት ስለ ሰላም እንዲህ ሲሉ መናገራቸው ይታወቃል፤ "Peace is not absence of conflict, it is the ability to handle conflict by peaceful means "ሠላም ጥል የሌለበት ማለት አይደለም፤ሠላም ማለት ግጭቶችን በሠላማዊ መንገድ መፍታት መቻል ማለት ነው" ብለዋል፡፡ ሀገሪቱን ለመበታተን የሚጥሩ የእነዚህንና መሰሎቻቸውን ሀላፊነት የጎደለው እኩይ ተግባር ደባ ማጋለጥ ብሎም ከመንግስት ጎን ሆኖ ሀላፊነትን መወጣት ለነገ የማይባል የዛሬ የቤት ስራ ሊሆን ይገባዋል፡፡ እያንዳንዱ አስፈፃሚ አካልም ከህዝቡ፣ከወጣቱ፣ከተማሪዎች፣ከንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ከ...

የትዳር አጋሩን ቀኝ እጅ በገጀራ የቆረጠው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

ምስል
  የቀድሞ ትዳር አጋሩን የቀኝ እጅ በገጀራ በመቁረጥ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት አስታወቋል። መስፍን ማሞ የተባለው ግለሰብ፤ ወንጀሉን የፈፀመው በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ሠላም ቀበሌ ልዩ ሥሙ ዳውሮ ሠፈር በሚባል አካባቢ ሲሆን የቀድሞ ትዳር አጋሩ የነበረችውን ገነት ኃይሌን የካቲት 03 ቀን 2014 ዕለተ ሐሙስ በግምት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ የቤቱን በር በኃይል በርግዶ በመግባት በያዘው ገጀራ የቀኝ እጇን ሙሉ በሙሉ ቆርጦ በመጣል መሆኑን ከአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃልና ተቆርጦ በተጣለው እጇ ፎቶ ግራፍ ለማረጋገጥ መቻሉን በችሎቱ ተገልጿል። በተጨማሪም እጇ ከተቆረጠ በኋላ ህይወቷን ለማትረፍ ስትል በጓሮ በር ሩጣ ለማምለጥ ስትሞክር፤ ተከታትሎ በያዘው ገጀራ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿን በመቆራረጥ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንዳደረሰባት ከአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃልና የሰነድ ማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል። ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ ከቀድሞ የትዳር አጋሩ ገነት ኃይሌ አንድ ወንድ ልጅ እንደወለደና በ2009 በፍርድ ቤት በህጋዊ መንገድ ፍቺ ከፈፀሙ በኋላ በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ግዝመሬት ቀበሌ ላይ ትዳር መስርቶ ይኖር እንደነበረ ተረጋግጧል። በዚህ መሠረት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት መስፍን ማሞ የተባለው ግለሰብ በፈፀመው ከባድ የሆነ ሰው የመግደል ሙከራ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን አዲስ ማለዳ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ገንዘብ ቸግሮኛል ያሉት ግለሰብ እንዲባዛልኝ ብለው ለተጠርጣሪዎቹ 2 ሚሊየን ብር ስለመስጠታቸው

ምስል
  ገንዘብ እናባዛለን በሚል ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ለማጭበርበር የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ገንዘብ እናባዛለን ብለው ከአንድ ግለሰብ ላይ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ለማጭበርበር የሞከሩ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ቦሌ ሆምስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው በቁጥጥር የዋሉት፡፡ አንድ ግለሰብ በአጋጣሚ ለተዋወቁት ሰው ገንዘብ እንደቸገራቸው ከነገሩት እና ይህ ሰውም "ገንዘብ የሚያባዛ ሰው አውቃለሁ፤ ችግር የለም ያባዛሎታል" ካላቸው በኋላ ነበር የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው፡፡ ገንዘብ ቸግሮኛል ያሉት ግለሰብ እንዲባዛልኝ ብለው ለተጠርጣሪዎቹ 2 ሚሊየን ብር ስለመስጠታቸው በምርመራ ወቅት መግለፃቸውን ተመላክቷል፡፡ ገንዘብ እንዲባዛ አደርጋለሁ ያለው ተጠርጣሪ የናይጄሪያ ዜግነት ካለው ግብረአበሩ ጋር በመሆን የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እያሉ ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ገንዘብ ይባዛበታል በተባለው ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ብርበራ መከናወኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡ በተደረገው ብርበራም ግለሰቡ እንዲባዛላቸው ሰጥቻለሁ ካሉት 2 ሚሊየን ብር ውስጥ 1 ሚሊየን 555 ሺህ 8 00 ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በተጨማሪም በብር መጠን የተቆራረጠ በርካታ ወረቀት፣ ኬሚካል እና ማተሚያ ማሽን መያዙን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው የቀጠለ ሲሆን ÷ፖሊስ ገንዘብ ይባዛበታል ወደ ተባለው ቤት ለብርበራ በሄደበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ማስረጃ ለማጥፋት በማሰብ በብር መጠን ተቆራርጦ የተቀመጠውን ወረቀት ...

Dinqisiifannaa Jaanaraalota keenyaa!

ምስል
  Qondaaltoonni loltummaa Itiyoophiyaa tibbana hojiiwwan misoomaa jiddu gala biyyaatti hojjetamaa jiran akka daawwatan taasifameera.Qondaaltoonni loltummaa hojiiwwan misoomaafi caasaawwan gara garaa teeknooloojii hammayaa’aa qaban kan daawwatan yoo ta’u watoota daawwatanitti akka gammadan himaniiru. Nuti waraanarra turre waan ta’eef jiddu gala biyyaatti hojiiwwan misoomaa itti fufiinsa qaban waan hojjetamaa jiran nutti hin fakkaatu ture kan jedhan qondaaltoonni loltummaa Itiyoophiyaa kun haalli adda waraanaa taa’uudhaan ittiin yaadan dogopngora ta’uusaa hojiiwwan misoomaafi guddinaa erga daawwatanii booda hubannoon     dogongoraa qaban akka sirraa’e dubbatan. Tika biyyaalessaa Kanaan dura akka daawwannuuf carraa akka hin qabnes himuudhaan caasaan tika biyyaalessaa haala amansiisaadhaan ijaaramuusaa daawwannaa taasifneen qabatamaan mirkaneessuu dandeenyee jirra jedhaniiru.

ጽንፈኞች በመንግስት መዋቅር ዉስጥም እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ

ምስል
    ጽንፈኞች በሃይማኖትና በፖለቲካ ፖርቲዎች ብቻ ሳይሆን በመንግስት መዋቅር ዉስጥም እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶ / ር ቀነአ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄዱ በነበሩ ህዝባዊ የዉይይት መድረኮች ላይ ሲነሱ በነበሩ የጸጥታ ጥያቄዎችና እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ዙሪያ ለ OBN ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር : የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት : የፌደራል መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ነች። በርካታ አህጉር አቀፍና አለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫቸዉ እዚሁ የአዲስ አበባ ከተማ ነዉ። የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች : ሃይማኖቶች : የፖለቲካ ፖርቲዎች : የንግድ ማዕከላት : አንጋፋ የግልና የመንግስት ተቋማት መገኛ የሆነችዉ አዲስ አበባ በርካቶች በመግባባት : በመቻቻልና መከባበር የሚኖሩባት ከተማ ነች። አዲስ አበባ ይህንን የመሠለ ሃገር አቀፍና አለም አቀፍ ገጽታ ቢኖራትም አንዳንድ ጽንፈኞች ግን ሃይማኖትን : ብሔርንና ፖለቲካን መሠረት ያደረገ አጀንዳ በማንሳት የከተማዋን ጸጥታ ለማደፍረስ ሲሯሯጡ ይስተዋላል። የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዉ ዶ / ር ቀነአ ያደታ ባለፉት ሳምንታት በከተማዋ ሲካሄዱ በነበሩ ህዝባዊ የዉይይት መድረኮች ላይ አራት መሠረታዊ ጥያቄዎች ትኩረት አግኝተዉ መለየታቸዉ ይናገራሉ። ከነዚህ መሠረታዊ ጥ...