ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከላዊ ኮሚቴአቸውን ማሰልጠን መብታቸው ነው!

 


ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴአቸው በመደመር ፍልስፍና ላይ ያተኮረ ስልጠና ለምን ሰጡ? የስልጠናው ሂደትም ለምን በሚዲያዎች ተላለፈ? የሌሎች ፓርቲዎች ስልጠና እንዲተላለፍ ይደረጋል? የሚል ኡኡታ ተሰምቷል

ኡኡታው በዚህ ደረጃ ከማልጠብቃቸው ግለሰቦችና ዩቱበሮች ጭምር መሰማቱ አስገርሞኛል፤ከሰሞኑ ከኢሳት ተለይተናል ብለው ዩትዩብ ከፍተው ስለ አገራቸው መልካም ጉዳዮቸ ላይ ሲወያዩ የሰነበቱ ሰዎች በዚህ ጉዳይ እንዲህ መንጨርጨር ይጠበቅባቸዋል? ጎ ፈንድሚዋ በዚህ ሙቀት ትጨምራለች፤የወዳጆች ቁጥርም በሽበሽ ይሆናል ብለው ካሰቡ በጣም ተሳስተዋል፤ለእናንተ ወቅታዊው ሙቀት ሳይሆን ዘላቂው ጥቅም ይበልጥባችኋል፤ለነገሩ ሲሳይ አጌና መኖሩ መልካም ነው ነገሩን ሚዛናዊ በማድረግ ከአደጋ ይጠብቃችኋል

ብልፅግና ፓርቲ የምርጫው አሸናፊ ሆኖ አገራችንን እስከ አስተዳደረ ድረስ በአገሪቱ ሚዲያዎች ተጠቅሞ የስልጠናው ይዘትም ሆነ ሌላ ጠቃሚ ጉዳይ ለሰፊው ህዝብ እንዲደርስለት ቢያደርግ ምን ችግር አለው? ሌሎች ፓርዎችም አቅም ኖሮአቸው ለተከታዮቻቸው ስልጠና ሰጥተው በመገናኛ ብዙሃን ቢተላልፍላቸው ምንም ችግር ያለው አይመስለኝም፤ደግሞም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚሰጠችው መግለጫዎች፤የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በመገናኛ ብዙሃን እየተላለፈላቸው ነው አቅም አዳብረው እንደ ብልፅግና የሚሰጡት ስልጠና በሚዲያ ለተከታዮቻቸው ቢተላለፍ አንዳችም የሚፈጥረው ችግር የለም የሚል እምነት አለኝ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman