የትዳር አጋሩን ቀኝ እጅ በገጀራ የቆረጠው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

 


የቀድሞ ትዳር አጋሩን የቀኝ እጅ በገጀራ በመቁረጥ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት አስታወቋል።
መስፍን ማሞ የተባለው ግለሰብ፤ ወንጀሉን የፈፀመው በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ሠላም ቀበሌ ልዩ ሥሙ ዳውሮ ሠፈር በሚባል አካባቢ ሲሆን የቀድሞ ትዳር አጋሩ የነበረችውን ገነት ኃይሌን የካቲት 03 ቀን 2014 ዕለተ ሐሙስ በግምት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ የቤቱን በር በኃይል በርግዶ በመግባት በያዘው ገጀራ የቀኝ እጇን ሙሉ በሙሉ ቆርጦ በመጣል መሆኑን ከአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃልና ተቆርጦ በተጣለው እጇ ፎቶ ግራፍ ለማረጋገጥ መቻሉን በችሎቱ ተገልጿል።


በተጨማሪም እጇ ከተቆረጠ በኋላ ህይወቷን ለማትረፍ ስትል በጓሮ በር ሩጣ ለማምለጥ ስትሞክር፤ ተከታትሎ በያዘው ገጀራ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿን በመቆራረጥ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንዳደረሰባት ከአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃልና የሰነድ ማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።
ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ ከቀድሞ የትዳር አጋሩ ገነት ኃይሌ አንድ ወንድ ልጅ እንደወለደና በ2009 በፍርድ ቤት በህጋዊ መንገድ ፍቺ ከፈፀሙ በኋላ በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ግዝመሬት ቀበሌ ላይ ትዳር መስርቶ ይኖር እንደነበረ ተረጋግጧል።
በዚህ መሠረት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት መስፍን ማሞ የተባለው ግለሰብ በፈፀመው ከባድ የሆነ ሰው የመግደል ሙከራ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን አዲስ ማለዳ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman