ልጥፎች

የሕግ የበላይነት ይጠበቃል፤ይከበራል

ብዙዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ለሁላችንም የሚበጅ ለውጥ ታየቷል ለውጡን አስተማማኝ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ጥቂት አመራሮች የሚያሳዩት ቁርጠኝነት ብቻ ለውጡን ማስቀጠልና አስተማማኝ ማድረግ አይችልም ስለዚህ ሁሉም በእኔነት ስሜት መስራት ይጠበቅበታል ሁሉም ተባብሮ ሲንቀሳቀስ የህግ የበላይነት ይጠበቃል ይከበራልም ሁላችንም ኃላፊነታችንን በአግባቡ ከተወጣን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየው አግባብ ያልሆነ አካሄድ ይስተካከላል የመንግስት የመጀመሪያ ስራ ሕግን ማስከበር ስለሆነ መንግስት ወዶ ሳይሆን በግዴታ የህግ የበላይነትን ያስከብራል ሁሉም ዜጋ ግን ለህግ ማስከበር ስራ መተባበርና ግዴታውን መወጣት ይጠበቅበታል መንግስት ህግ ማስከበር አልቻለም ብሎ ማሰብ ስህተት ነው አንዳንድ የአገራችን ሚዲያዎች በዚህ አይነት መልኩ ሲሰሩ ይሰማል በተለይም አንዳንድ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችና የቴሊቪዥን ጣቢያዎች ኃላፊነት የጎደለው ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ የብሮድካስት ባለስልጣን የሚባለው ተቋምማ አንቀላፍቷል ባለስልጣኑ ንቁ ሆኖ ቢከታተል ኖሮማ ማንም አንደፈለገ አይዘባርቅም ነበር ሁሉም ሚዲያዎች ከመዘባረቅ ወጥተው ለህዝብና አገራችን ተስፋ ሰጪ የሆኑ ስራዎችን ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል

Mana Abbaabbuu Mana Shaashee

Mana Abbaabbuu Mana Shaashee Eenyu jedhe maal abbaashee Maraataan kun maal jedhee? Mana Shaahsee,galma   Shaashamannee እንኳን አላየ ፀጋዬ ይህንን ጉድ እንደኔ Marataan kun maal jedhee? Maal dubbatee Maaltuu galee mana Shaashee? እንዳላለሽ ጥላዬ ‹‹ Kottumee Magaalaa deemnaa koottumee Shaashii binnaa ›› ሻሼ ልጅዋ ታረደ   በገዛ በራስዋ መንደር በኖረችበት ከተማ መባሉን እንኩዋን አልሰማ ፀ ጋዬ እንኩዋን አልሰማ ገረሱ እንኳን አልሰማ ጃገማ እንኳን አልሰማ ………. እንኳን አልሰማ Mana Shaashee Shaasahamnnee   ሁሉ እንዳላለሽ የኔ የኔ እንዳላለሽ ሁሉ አላፊ አግዳሚው በሙሉ አጋንንት ያደረባቸው ዲያቢሎስ ‹‹ አርጉ ›› ያላቸው ባንቺ ጥላ ስር ያሉ በጎጆሽ አድረው የዋሉ የልጅሽን አንገት ሲቀሉ አንቺስ እንዴት አስቻለሽ ኗሪዎችሽስ የት አሉ? ቄሱና ሼኪው የት ገቡ ዘማሪውና ፓስተሩ ወቶ አደር ፖሊስ መምህሩ ዳኛ ጠበቃው ዶክተሩ ያን እለት የት ተሰወሩ? መካሪ አባቶች በሙሉ ያን እለት ወየት ነበሩ? የተፈፀመውን በዚች ከተማ እንኳንስ ፀጋዬ አልሰማ እንኳንም ጃገማ አልሰማ ያልታደልነውማ   ደማ ልባችን ደማ ደማ ውስጣችን ደማ፡፡ ሙሉጌታ ተስፋዬ ነሃሴ 7/201 0

Fayyisaa Lalisa waamicha dhiyaateef gammachuun fudhate

ምስል
Gootni Atileet Fayyisaa Lalisa waamicha dhiyaateef gammachuun fudhachuun gara biyyasaatti akka deebi’u yaada kenneen mirkaneesseera. Goota gara biyyasaatti deebi’u kanaaf simannaan gootaa taasifamuu qaba!Qabsoon farra gabrummaa sadarkaa idila addunyaatiin beekkamtii akka argatuuf shoorri inni gumaache ol’aanaadha waan ta’eef shoorri Atileet Fayyisaan gumaache akka waan salphaatti kan ilaalamu miti. Qabsoon farra gabrummaa akka finiinuuf shoora ol’aanaa kan gumaachite Atileet Fayyisaa Lalisaa maatiikee jaallattuun wajjin gara biyyakeefi ummatakee jaallattutti garaa gutuudhaan deebi’i. Amma gufachiiftoonni jijjiiramaa waan jiraniif kaayyoon qabsookee fashalaa’ee duubatti akka hin deebineef biyya keessatti kanneen qabsaa’aa jiran wajjin qabsookee finiinsuutu sirraa eegama. Keessumattuu Tokkummaa Saba Oromoo daran jabeessuu keessatti namni akkakee beekkamtii ol’aanaa horate shoorri gumaachuu danda’u ol’aanaa waan ta’eef tokkummaa Oromoo cimsuuf hojjechuu qabda.Qabsoon kunis...

Obbo Ahimad Shidee dura taa'aa PDUSI ta'uun filataman

ምስል
Obbo Ahimad Shidee dura taa'aa Paartii Demokiraatawa Ummata Somaalee Ityoophiyaa ta'anii filataman Paartiin Demokiraatawa Ummata Somaalee Ityoophiyaa obbo Ahimad Shidee dura taa’aa paartichaa taasisuun filateera Koreen giddu galeessa PDUSI guyyoota sadan darbanitti rakkoo naannichatti muudate irratti gamaaggama bal'aa gaggeessun dura taa’aa paartichaa haarawa filateera. Paartichi naannicha tasgabeessuf cimee hojjeta jedhameera. Ministira dhimmoota komonikeeshinii Mootummaa Federaalaa ta'uun tajaajilaa kan jiran Ob.Ahmad Shidee akkaataa filannoo ammaatiin pireezidaantii Naannoo Sumaalee Itiyoophiyaa ta'u jedhamee eegama. Obbo Ahmad pireezidaantii Naannoo Sumaalee Itiyoophiyaa ta'uun ammoo rakkoo hedduu mudataa turee fala waaraa akka ta'u abdatama

በጌዴኦና ምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች አጎራባች ቦታዎች

ምስል
በጌዴኦና ምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች አጎራባች ቦታዎች የተከሰተውን ግጭት በዘላቅነት ለመፍታት ሁሉቱ አባጋዳዎች በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገለጹ ግጭቱን ተከትሎም የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አከባቢያቸው ለመመለሰም ሁሉንም የህብረተሰሰብ ክፍሎች ያሳተፈ ርብርብ እንደሚጠይቅም ጠቅሰዋል:: የጌዴኦና የጉጅ አባገዳዎች የጋራ የምክክር መድረክ ለሶስተኛ ጊዜ ተኳሂዷል፡፡ በዉይይቱም ችግሩን በዘላቅነት ለመፍታታት ሁሉንም የማህበረስብ ክፍሎች ጋር ምክክር ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸዉን ገልፀዋል፡፡ በውይይቱም ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የጉጂ አባገዳ ጅሎ ማኞ ለሦስት ወራት የዘለቀዉን የሰላም ዕጦት ለመፍታት አስፈላጊ የሆኑ ሰራዎችን ለመስራት መስማማታቸዉን ገልፀዉ ...ለዝህም በባህላቸዉ መሰረት ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ በሁለቱም በአጎራባች አከባቢዎች የሚስተዋሉ ወንጀሎች የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችና ጥቃቅን ትንኮሳዎችን እንድያቆሙ ጥረያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ የጌዴኦ አባገዳ ደንቦብ ማሩ በበኩላቸዉ ለረጅም ዘመናት ተከባብረዉ አብረዉ ስኖሩ የቆዩ ሁለት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረዉን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የተደረገ የሰላም ድርድር ስከታማ መሆኑን ተናግረዉ...ችግሩን በማያዳግም መልኩ ለመቅረፍ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ለግጭት መነሻ ከምሆኑ እኩይ ተግባራት እንድቆጠቡ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ ቀሪ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስራዎችንም የሁለቱም ወገን የባህል ሽማግሌዎች ከሁሉም አከባቢ የተወከሉ ወጣቶች፤የባህል መሪዎች ፤ከየቀበሌ ተወክለዉ ከሚመጡ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር በማድረግ ሁሉም የአከባቢ ሰላም ለመጠበቅ ዘብ እንድቆም ለማድረግ የጋራ ቀጠሮ መያዛቸዉን አብራርተዋል፡፡ ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥና በውጭ የነበሩት ሲኖዶሶች በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ተስማሙ

ምስል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሁለቱ ሲኖዶስ የነበረው ልዩነት በዕርቀ ሰላም ወደ አንድነት ተመለሰ። ባለፉት 27 ዓመት በሁለት ሲኖዶስ ስትመራ የቆየችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርሲቲያን ወደ አንድ ለማምጣት የሰላምና የእርቅ ጉባዔው በዋሸንግተን ደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ባለፈው እሁድ የሁለቱም ልኡካን አባቶች በተገኙበት የጋራ ጸሎትና የመክፈቻ መርሐ ግብር ተጀምሯል። ሲኖዶሶቹ ለሁለት በመከፈላቸው ምክንያት ችግር ላይ የነበሩ የእምነቱን ተከታዮች ወደ አንድነት ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት በማድረግ ወደ አንድነት እንደተመለሱ ታማኝ ምንጮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል። በእስካሁኑ ውይይታቸው በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተነገረው። በተጨማሪም "የሀገር ቤት ሲኖዶስ" እና "ስደተኛ ሲኖዶስ" የሚባለውን ለማስቀረት ተስማምተዋል። ይህ የሰላምና የእርቅ ጉባዔ እስከ አርብ ድረስ የሚቆይ እንደሆነና በውይይቱ መጨረሻ መግላጫ እንደሚሰጥ ነው የተገለፁው። በቅርቡ ወደ አሜሪካ ያቀኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፅህፈት ቤታቸው ማነጋገራቸው የሚታወስ ነው። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱ በእርቅና ሰላም ረገድ አርዓያ መሆን እንዳለባቸው በመጥቀስ፥ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላም የሀገር ሰላም እንደሆነ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ የጠፋውን ሰላም ወደ ነበርበት እንዲመለስ ለማድረግም ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከዚህ በፊት ማስታወቀቸው ይታወሳል። በ2010 ዓመተ ምህረት ጥቅም...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነገው ዕለት ወደ አሜሪካ ያቀናሉ

ምስል
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነገው ዕለት ወደ አሜሪካ ያቀናሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስና በዋሽንግተን ዲ ሲ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነገ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 24 ቀን ድረስ ነው በአሜሪካ ቆይታ የሚያደርጉት። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ የመንግስት ለመንግስት ግንኙነትን መሰረት ያደረገ ሳይሆን፥ በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተገናኝተው መወያየትን ዋና ዓላማው ያደረገ መሆኑን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። “ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉት ጉዞ በአጠቃላይ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ በሀገራቸው እየተካሄደ ላለው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል ሆነው ለሀገሪቱ ልማትና እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያውያኑና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተሳታፊ በመሆን ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ በማለም የሚካሄድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀምሌ 21 ቀን በዋሽንግተን ዲ ሲ እና ሀምሌ 22 ቀን በሎስ አንጀለስ ከተማዎች ሁሉም ወገን የሚሳተፍባቸው ጉባዔ የሚያደርጉ ይሆናል። ሁለቱ ከተሞች በምስራቁና በምዕራቡ የአሜሪካ ግዛቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ አቅራቢያ ማዕከል ለማሰባሰብ አመች በመሆናቸው ለጉባኤው መመረጣቸውም ነው የተሰማው። በተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን በየአካባቢያቸው ለመቀበል ፍላጎት ያሳዩ ቢሆንም፥ ካለው ጊዜ አንፃር ግን ሁሉንም ለማዳረስ አዳጋች በመሆኑ ሁለቱ ከተሞች ...