በጌዴኦና ምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች አጎራባች ቦታዎች
በጌዴኦና ምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች አጎራባች ቦታዎች የተከሰተውን ግጭት በዘላቅነት ለመፍታት ሁሉቱ አባጋዳዎች በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገለጹ
ግጭቱን ተከትሎም የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አከባቢያቸው ለመመለሰም ሁሉንም የህብረተሰሰብ ክፍሎች ያሳተፈ ርብርብ እንደሚጠይቅም ጠቅሰዋል::
የጌዴኦና የጉጅ አባገዳዎች የጋራ የምክክር መድረክ ለሶስተኛ ጊዜ ተኳሂዷል፡፡
በዉይይቱም ችግሩን በዘላቅነት ለመፍታታት ሁሉንም የማህበረስብ ክፍሎች ጋር ምክክር ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸዉን ገልፀዋል፡፡
በውይይቱም ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የጉጂ አባገዳ ጅሎ ማኞ ለሦስት ወራት የዘለቀዉን የሰላም ዕጦት
ለመፍታት አስፈላጊ የሆኑ ሰራዎችን ለመስራት መስማማታቸዉን ገልፀዉ ...ለዝህም በባህላቸዉ መሰረት ችግሩን ከምንጩ
ለማድረቅ በሁለቱም በአጎራባች አከባቢዎች የሚስተዋሉ ወንጀሎች የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችና ጥቃቅን ትንኮሳዎችን
እንድያቆሙ ጥረያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
የጌዴኦ አባገዳ ደንቦብ ማሩ በበኩላቸዉ ለረጅም ዘመናት
ተከባብረዉ አብረዉ ስኖሩ የቆዩ ሁለት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረዉን የፀጥታ ችግር ለመፍታት
የተደረገ የሰላም ድርድር ስከታማ መሆኑን ተናግረዉ...ችግሩን በማያዳግም መልኩ ለመቅረፍ ሁሉንም የህብረተሰብ
ክፍሎች ለግጭት መነሻ ከምሆኑ እኩይ ተግባራት እንድቆጠቡ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
ቀሪ ባህላዊ
የግጭት አፈታት ስራዎችንም የሁለቱም ወገን የባህል ሽማግሌዎች ከሁሉም አከባቢ የተወከሉ ወጣቶች፤የባህል መሪዎች
፤ከየቀበሌ ተወክለዉ ከሚመጡ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር በማድረግ ሁሉም የአከባቢ ሰላም ለመጠበቅ ዘብ እንድቆም
ለማድረግ የጋራ ቀጠሮ መያዛቸዉን አብራርተዋል፡፡
በደም፤ በባህልና በአኗኗር ዘይባቸዉ ሊነጣጠሉ
የማይችሉ ህዝቦች አንድነትና መተማመኑን መልሶ ለማጎልበት ሁለቱም ወገኖች ወጣቱን ያሳተፈ የጋራ እሴቶች ማጠናከረያ
ትምህርት መስጠት አስፈላግ መሆኑን የባህል አባቶቹ ተስማምተዋል፡፡
በተጨማርም የምዕራብ ጉጅ ዞን ፀጥታ
መምህረያ ኃላፍ የሆኑት አቶ ደስታ ኤቴና በበኩላቸዉ የሁሉት አባገዳዎች ዉይይት በአካባቢው የሰላም ንፋስ እንድነፍስ
ጉልህ ሚና እንዳለዉ አብራርተዉ ...ሁለቱንም ህዝቦች የሚመሩ ባህላዊ ስርዓቶች ተመሳሳይ በመሆናቸው የነበረዉን
ሰላምና አብሮነት መልሶ ለማስፈን የጎላ ድርሻ እንደምጫወት አብራርተዋል፡፡
ባህላዊ የዕርቅ ሰላም
ምክክር የተፈለገዉን ዉጤት እንድያስገኝ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጥፋተኞችን በማጋለጥና ጥቃቅን የግጭት መነሻ
የሚሆኑትን ትኮሳዎችን በማቆም የሰላም ማስፈኑን ስራ እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ፀጥታ
አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ እንግዳወርቅ ዳካ በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ቀድሞ የነበረዉን ሠላምና
መተማመን ለማስፈን የሁለቱ አባገዳዎች የሰላም ምክክር በአጭር ጊዜ ለማረጋጋት ያለዉን አስፈላጊነት አብራሪተዉ
ቀጣይ ዉጤት ለማየትና ህዝቦቹ ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ ጉልሀህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡
ቀጣይ ዉጤት ለማየትና ህዝቦቹ ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ ጉልሀህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡
የሰላም ማስፈን ስራ ዉጤታማ ለማድረግ በሁለቱም ወገኖች መካከል የሚሰተዋሉ ጥቃቅን የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸዉን ድርሻ እንድወጡ ጠይቀዋል::
ሐምሌ 18/2010
Source:- Gedeo Zone Governmental Communication office
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ