የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት በማንሳት አዳዲስ አመራሮች መሾማቸውን ገለፀ።
የማረሚያ ቤት አስተዳደር ህገ መንግስታዊ ግዴታውን በተገቢው ሁኔታ መወጣት ባለመቻሉ እና ሰብዓዊ መብቶችን
ከማክበር አንጻር ሰፊ ክፍተት በመኖሩ ለውጥ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
ገልጿል።
ቀደም ሲል የነበሩትን አመራሮች በማንሳት አዳዲስ አመራሮች መመደባቸውንም ነው ያስታወቀው።
በዚህም መሰረት ጀማል አባሶ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሾሙ ረዳት ኮሚሽነር ያረጋል አደመ፣
ኮማንደር ወንድሙ ጫላ፣ ኮማንደር ሙላቱ ዓለሙ እና ኮማንደር ደስታ አስመላሽ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት
ተሹመዋል።
አዳዲሶቹ አመራሮችም የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት በህገ መንግስቱ የሰፈሩ ሰብዓዊ መብቶችን እና ህጎችን ባከበረ መልኩ እንዲሰሩ መመሪያ እንደተሰጠም ተመልክቷል።
አመራሮቹ ከሃላፊነት የተነሱት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ህገመንግስቱን ለማስከበር በማሰብ መሆኑም ነው የተገለፀው።
ህግ የጣሱ አካላት ማጣራት እየተደረገባቸው ወደ ፍትህ እንደሚቀርቡም ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገልጿል።
ሹመቱ
የተሰጠው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንደሆነ መገለፁን ፋና ዘግቧል
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ