የሰንደቁ ጉዳይ ይቆይ!


ከሰሞኑ ስለ ሰንደቅ ዓላማ የሚደረገው ውይይት ሞቅ ደመቅ ብሎ ቆይቷል ሃሳብ መለዋወጡ መልካም ነገር ነው ተጠናክሮ መቀጠልም አለበት በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እንደ ዜጋ የምናካሂደው የትኛውም ውይይት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም
እና ሰሞኑን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ከተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ጋር በተያያዘ በአደባባይ ላይ የታዩ የቀድሞ ስርዓቶች ሲጠቀሙባቸው የቆዩ ሰንደቅ ዓላማዎች፤ የድርጅቶች አርማዎችና ሰንደቅ ዓላማዎች በይፋ ታይተዋል፤ይህም አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል
ነገር ግን አሁን ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ዋነኛው ጉዳይ ስለ አንደነታችን ቀጣይነት መሆን አለበት አንድነት፤ፍቅርና መከባበር ከምንም ነገር በላይ መሆኑን እናውቃለን አንድ ስንሆን የማናልፈው ፈተና የለም አንድነት ኃይል ነዋ!
በአገር ደረጃም ሆነ በየአካባቢያችን አንድ ሆነን ከተንቀሳቀስን ከእኛ ተቃራኒ የሆኑትን ሁሉ ማሸነፍ እንደምንችል በደንብ እናውቃለን ተቃራኒዎቻችንም ይህን በደንብ ያውቃሉና አንድ እንዳንሆን በመስራት ላይ ይገኛሉ

ስለዚህ አሁን መጨነቅ ያለብን ስለ ሰንድቅ ኣላማ ሳይሆን ስለ

ሰላም ፍቅር ይቅርታ
አንድነታችን ቀጣይነት መሆን አለበት የሰንደቁ ጉዳይ ይቆየን እንደርስበታለን ወደፊት የትኛው ይሻለናል ብለን ተወያይተን የተግባባንበትን መጠቀም እንችላለን አንድነታችን፤ቀጣይ መሆን ካልቻለ በእጃችን የገባውን ድል ሁሉ ልንነጠቅ እንደምንችል አውቀን አስቀድምን ስለ አንድነታችን እንስራ ሰላማችንን እንጠብቅ ፀጉረ ልውጦችን እንከታተል መደበኛ ስራችንን እናጧጡፍ! ዜግነታዊ ምክሬ ነው

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa