ልጥፎች

ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ

ምስል
ፊንፊኔ ግንቦት 08/2011(ቶለዋቅ ዋሪ)  የኬንያ ፖሊስ በሕገ ወጥ መንገድ በድብቅ ወደናይሮቢ ሊገቡ ነበር ያላቸውን 22 ኢትዮጵያዊያንን መያዙን ገለጸ። በኬንያ የወንጀል መከላከል ልዩ ፖሊስ አባላት የተያዙት ኢትዮጵያዊያን በሁለት መኪኖች ተሳፍረው ሲጓዙ ነበር ተብሏል። ትናንት ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ጋር በተያያዘ ሁለት ሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ገልጿል። የታሰሩት ኢትዮጵያዊያን ለፖሊስ እንደተናገሩት፤ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በኬንያ በኩል ከዛም ታንዛኒያን በማቋረጥ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ አቅደው ነበር። ከተያዙት ስደተኞች መካከል 17ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ ሲያጓጉዟቸው የነበሩት ግለሰቦች ደግሞ ኬንያዊያን ናቸው። ኢትዮጵያዊያኑ በኬንያ በኩል ለማቋረጥ እንዲችሉ ለሚረዷቸው አዘዋዋሪዎች ምን ያህል ገንዘብ እንደከፈሉ የታወቀ ነገር የለም የወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር የሆኑት ጆርጅ ኪኖቲ እንደተናገሩት፤ ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ማዘዋዋር በመጠኑ ከፍ እያለ በመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። የኬንያ ባለስልጣናት እንደሚሉት፤ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ በኩል ለማቋረጥ ሲሞክሩ ተይዘው ወደመጡበት እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆን፤ አብዛኞቹ ሥራ ፍለጋ እና ወደሌላ ሀገር መሻገርን ግብ አድርገው ወደ ሃገሪቱ ይገባሉ። ስደተኞቹ ከድንበር ከተማዋ ሞያሌ አንስቶ እስከ ናይሮቢ ድረስ በሚጓዙበት ጊዜ ከሃያ በላይ የፖሊስ ኬላዎችን አልፈው መሆኑ የደህንነት ባለስልጣናትን ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል። አንዳንድ ባለስልጣናት እንደሚሉት፤ ይህ አይነቱ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚፈጸመው በአዘዋዋሪዎቹና በጸጥታ ሰራተኞች መካከል በሚደረግ መመሳጠር ነው። ትናንት ከተያዙት ስደተኞች ጋር በተያያዘ የፖሊስ...

አቶ ንጉሱ ጥላሁን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል

ምስል
ፊንፊኔ ግንቦት 02/2011(ቶለዋቅ ዋሪ)  ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የተከሰቱ ግጭቶችን ያነሳሱ፣ ያቀናበሩ፣ የመሩ እና እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 2 ሺህ 517 ያህል ተጠርጣሪዎች በህግ እንዲጠየቁ መለየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለፁ። የዜጎች መፈናቀልን በተመለከተ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በሀገሪቱ ሲስተዋል መቆየቱን አቶ ንጉሱ ተናግረዋል። በለውጥ ሂደት ውስጥም ዜጎች በየትኛውም አከባቢ ሰርቶ የመለወጥ መብታቸው እንዲከበር ታሳቢ ተደርጎ መንግስት ሲሰራ ቢቆይም አሁንም ችግር ሆኖ መቆየቱን ነው ያመለከቱት። በአሁኑ ወቅትም በክልሎችም ሆነ ከክልል ተሻግሮ የሚታዩት ግጭቶች መነሻ በማንነት እና ከወሰን ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ መሆናቸውንም ነው አቶ ንጉሱ ያመለከቱት። በተከሰቱ ችግሮችም የሰው ህይወት መጥፋቱ እና ንብረት መውደሙንም አንስተዋል። 875 ሺህ ዜጎች ወደነበሩበት ቦታ ተመልሰዋል ችግሩን ለመቅረፍ ቅድመ ጥንቃቄ የማድረግ እና የመከላከል ስራ መሰራቱን በመግለፅ፥ በህብረተሰቡ እና በመንግስት ርብርብ የመከኑ ችግሮች መኖራቸውን ገልፀዋል። ግጭቶች ከተከሰቱ እና መፈናቀል ካጋጠመ በኋላ ዜጎች የበለጠ ጉዳት እንዳይዳረጉ ባሉበት ቦታ እና ተፈናቅለው በሚገኙበት አካባቢ የምግብ፣ የህክምና እና የቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ይህም ተግባር በመንግስት፣ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች እና በህብረተሰቡ እየተከናወነም ይገኛል ነው ያሉት። ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ከማድረግ አኳያ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለሱበት አካባቢን ምቹነት በማረጋገጥ ከተፈናቃዮቹ ጋር ውይይት እንደሚካሄድ አመልክተዋል። እንዲሁም 875 ሺህ ...

በስህተት ከባንክ የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር:

ምስል
አቶ ዓለሙ ተስፋዬ (ዶ/ር) ባህርዳር በሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ በተንቀሳቃሽ ደብተራቸው የገባውን ገንዘብ ለማውጣት በጣና ቅርንጫፍ የተገኙት ሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓ. ም. ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ማኅበረ ቅዱሳን በሚያስተባብረውና አቶ ዓለሙ በሚሳተፉበት ፕሮግራም የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማትን ለማደራጀት የተሰበሰበ አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሦስት ሺ ብር በስማቸው ገብቶ ነበር። በገበያ አካባቢ በሚገኘውና የሥራ ጫና በሚበዛበት የጣና ቅርንጫፍ ያሉ ሠራተኞች የተለመደ የዕለት ከዕለት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ አቶ ዓለሙ ከፍጠኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለማውጣት መጠየቃቸውን የጣና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢራራ መላኩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ደንበኛው የጠየቁት የገንዘብ መጠን አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሦስት ሺ ብር ነበር። አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ የገንዘቡ መጠን ከፍ ያለ ስለነበረ ፊትለፊት የነበረው ገንዘብ ከፋይ ለደንበኛው 3000 ብሩን ብቻ እንዲሰጣቸው ተደርጎ፤ ቀሪውን 1.2 ሚሊየን ብር ወደ ውስጥ ገብተው እንዲወስዱ ተደርጓል። ''ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ብሩን አብረን ቆጥረን እንዲረከቡ አደረግን። ደንበኛው ከጠየቁት አንድ ሚሊየን ብር ጭማሪ ተሰጥቷቸው ገንዘቡን ገቢ ወደሚያደርጉበት ቦታ ሄዱ።'' አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ ለአቶ ዓለሙ አንድ ሚሊየን ብር ተጨማሪ መሰጠቱንና ከባንኩ ብር መጉደሉን አላወቁም ነበር። አቶ ዓለሙ በስህተት የተሰጣቸውን ገንዘብ በጆንያ ጭነው እስከተመለሱበት ጊዜ ድረስ ምንም እንዳልጠረጠሩ ያስረዳሉ። የተፈጠረውን ነገር "እጅግ አስገራሚ'' ሲሉም ይገልጹታል። ''ደንበኛው በመጀመሪያ ገንዘቡን ይዘው ሲ...

Guddina diinagdeetiif xiyyeeffannoon kennamuun mul'achaa jira

ምስል
Finfinnee Caamsaa 02/2011(Tolawaaq Waarii) Gufuuwwan hedduun jidduutti mulachuun qaawwi waan uumame fakkaate malee hooggansi jijjiiramaa waa'ee guddina diinagdeetiif xiyyeffannoo kennee socho'uu erga eegalee tureera.Warraaqsi Diinagdee Oromiyaatti waggoota dura eegalame kanaaf ragaadha. Sochiin qabatamaan tibbana Oromiyaatti mul'achaa jirus guddina damee diinagdeetiif xiyyeeffannoon addaa kennamee hojjetamaa akka jiru kan mul'isedha jechuun ni danda'ama. Dargaggoota hojii dhabeeyyii ta'aniif carraa hojii uumuun akka danda'amuuf dhiyeessii liqaa birrii biliyoona 3 caalu mijeessuun guddina diinagdee lammiitiif xiyyeeffannoo kennuudha.Dargaggoonni hojii hin qabne carraa mijaa'e kanatti sirritti fayyadamuu qabu.Yoo isaan carraa mijaa'e kanatti fayyadamanii socho'an guddina diinagdeetu saffisa. Saffisni guddina diinagdee lammii dhuunfaa ammoo guddina Naannoo keenyaafi biyyaa saffisiisuuf shoora ol'aanaa gumaacha. Dameen hojii qonnaas xiy...

Ummanni duruu tokkuma,mariin hariiroo obbolummaas waanuma jiru jabeessa

ምስል
Finfinnee Ebila 30/2011(Tolawaaq Waarii) Tibbana Oromiyaa iddoo hundatti sagalee Ummata waliin jiraachaa tureefi waliin jiraachaa jirutu dhaga’ame.Ummata dhaggeeffachuun waan gaariidha.Waliin jireenya Ummattootaa keessatti rakkoo maaltu jira?Ummanni maal jedha laata? Jechuun Ummanni akka mari’atuuf mootummaan haala mijeessuunsaa baay’ee gaariidha. Mootummaan Naannoo Oromiyaa haala tibbana mul’ate Kanaan Ummanni Oromoo sabaafi sab-lammoota waliin jiraatu wajjin iftoominaan akka mari’atu taasisuun isaa Nagaa Naannoo Oromiyaa amansiisaa taasisuuf,shakkii daldaaltoonni siyaasaa Ummattoota jidduutti uuman dhabamsiisuuf shoora ol’aanaa kan gumaachudha. Ummattoota jidduu duruu rakkoon akka hin jirre beekamaadha.Ummanni duruu waliin jiraachaa ture,ammas wal kabajaafi wal jaalalaan waliin jiraachaa jira.Mariin hariiroo obbolummaa tibbana sadarkaa Magaalotaa godinaalee aanaaleefi gandootaatti adeemsifame ammoo waliin jireenya ummattootaa kana daran kan jabeessudha. Akka hubatametti walt...

Mariin hariiroo obbolummaa cimsuu

ምስል
Finfinnee Ebila 29/2011(Tolawaaq Waarii) Mariin hariiroo obbolummaa cimsu guyyaa har’aas sadarkaa aanaaleetti itti fufee jira Mariin hariiroo obbolummaa cimsuu guyyaa kaleessaa sadarkaa godinaa fi maagaalota gurguddootti jalqabe guyyaa har’as sadarkaa aanaaleetti cimee itti fufee jira. Marii guyyaa kaleessaa sadarkaa godinaa fi magaalota gurguddootti gaggeeffameen dudhaa gaggaarii waliin jireenyaa ummattoota walitti hidhee fi tokkoomsee dh alootaa gara dhalootaatti cehaa dhufe cimsachuu fi shira daldaaltoota siyaasaa irraa eeggachuun bu’uura cimaa nageenyaa, misooma, guddinaa fi badhaadhina waliin taasifachuun tokkummaa fi jaalalaan fulduratti tarkaanfachuun akka dandanda’amu ejjennoon qabatameera.  Walitti bu’iinsii fi wal-buqqisuun shira daldaaltota siyaasaa irraa kan madde malee bu’uura ummattootaa kan hin qabne ta’uurrattis waliigalameera.Mootummaan dirree demokraasii bal’isuu sababa jedhuun mirgi midiyaaleedhaaf kenne gaarii ta’ullee, miidiyaaleen tokkoo tokko sada...

አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመሰረተ

ምስል
ፊንፊኔ ሚያዝያ 29/2011(ቶለዋቅ ዋሪ) አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመሰረተ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው፥ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ በጠቅላላው 46 ክሶች ናቸው የተመሰረቱት። በክሶቹ ውስጥ 22ቱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ በሌላ በኩል የቀድሞ የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አቶ አጽብሃ ግደይ፣ አቶ አሠፋ በላይ እና አቶ ሽሻይ ልዑል በተባሉ የቀድሞ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ በሌሉበት ክስ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ ችሎት ይመሰረትባችዋል። በአቶ ጌታቸው ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። በሌሎቹ ሁሉም ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ...