ከአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የድርጅታችን አዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/ቀን 2011 ዓ.ም በክልላችን መንግስት ላይ ተሞክሮ ሙሉ በሙሉ በከሸፈው መፈንቅለ-መንግስት እና በከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ በተፈፀመው የግፍ ግድያ ምክንያት የማዕከላዊ ኮሚቴያችን ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ተመስርቶ በወቅታዊ ጉዳይ እና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ግምገማ ለማድረግ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም እየመከረ ባለበት፣ የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከጥልቅ ሃዘናችን ባልተላቀቅንበት በዚህ ነባራዊና ህሊናዊ ሁኔታ ውስጥ ሆነን “በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት” እንዲሉ፣ የትህነግ/ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሐምሌ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትህነግ/ህወሓትን የነበረና እየቀጠለ ያለ አሳፋሪ የሴራ ፖለቲካ እርቃኑን በአደባባይ ያጋለጠ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ “ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንዲሉ” አገራችን አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት እራሱ ዋና ተጠያቂ ሆኖ ሳለ፣ የአማራን ህዝብ ህልውናና ክብር የማይመጥን መግለጫ አውጥቷል፡፡ ምንም እንኳን የድርጅታችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለስብሰባ የተቀመጠው ካጋጠመን ወቅታዊ ችግር በፍጥነት እንዴት መውጣት እንዳለብን እና የለውጡን ቀጣይነት ጠብቀን መዝለቅ እንደሚገባን ለመምከር ቢሆንም፣ የትህነግ/ሕወሓት መግለጫ ከሐዘን ባልወጣንበት ሁኔታ ከአንድ እህት ፓርቲ የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት በመሆኑ፣ ድርጊቱን ለማውገዝና ለአብሮነትና ለትግራይ ህዝብ ባለን ክብር እያየን እንዳለየን የታገስነውና እና ያለፍነውን ነገር ሁሉ፣ ትህነግ/ሕወሓት በመግለጫው “እራሱ ነካሽ፣ እራሱ ከሳሽ” ሆኖ በመቅረቡ ይህ የአዴፓ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ አስፈላጊና ወቅታዊ ሆኖ አገኝተነዋ...