ልጥፎች

ከአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ምስል
የድርጅታችን አዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/ቀን 2011 ዓ.ም በክልላችን መንግስት ላይ ተሞክሮ ሙሉ በሙሉ በከሸፈው መፈንቅለ-መንግስት እና በከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ በተፈፀመው የግፍ ግድያ ምክንያት የማዕከላዊ ኮሚቴያችን ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ተመስርቶ በወቅታዊ ጉዳይ እና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ግምገማ ለማድረግ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም እየመከረ ባለበት፣ የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከጥልቅ ሃዘናችን ባልተላቀቅንበት በዚህ ነባራዊና ህሊናዊ ሁኔታ ውስጥ ሆነን “በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት” እንዲሉ፣ የትህነግ/ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሐምሌ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትህነግ/ህወሓትን የነበረና እየቀጠለ ያለ አሳፋሪ የሴራ ፖለቲካ እርቃኑን በአደባባይ ያጋለጠ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ “ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንዲሉ” አገራችን አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት እራሱ ዋና ተጠያቂ ሆኖ ሳለ፣ የአማራን ህዝብ ህልውናና ክብር የማይመጥን መግለጫ አውጥቷል፡፡  ምንም እንኳን የድርጅታችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለስብሰባ የተቀመጠው ካጋጠመን ወቅታዊ ችግር በፍጥነት እንዴት መውጣት እንዳለብን እና የለውጡን ቀጣይነት ጠብቀን መዝለቅ እንደሚገባን ለመምከር ቢሆንም፣ የትህነግ/ሕወሓት መግለጫ ከሐዘን ባልወጣንበት ሁኔታ ከአንድ እህት ፓርቲ የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት በመሆኑ፣ ድርጊቱን ለማውገዝና ለአብሮነትና ለትግራይ ህዝብ ባለን ክብር እያየን እንዳለየን የታገስነውና እና ያለፍነውን ነገር ሁሉ፣ ትህነግ/ሕወሓት በመግለጫው “እራሱ ነካሽ፣ እራሱ ከሳሽ” ሆኖ በመቅረቡ ይህ የአዴፓ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ አስፈላጊና ወቅታዊ ሆኖ አገኝተነዋ...

በአማራ ክልል የተሻለ እና አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ምስል
በአማራ ክልል የተሻለ እና አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ሕጋዊ ትጥቅን ‹‹የማስፈታት ሥራ እንደተጀመረ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ›› ተብሏል፡፡ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን እና ሚዲያ ልማት ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ሰኢድ አህመድ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት በተለይ በተያዘው ሳምንት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ይፈፀም የነበረው መደበኛ ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ የፀጥታ መዋቅሩ ሕግና ሥርዓትን በማስከበር አስተማማኝ ሠላም ለማስፈን በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከሰሞኑ የተፈጠረውን ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ወንጀል አድራጊዎች ሊበራከቱ እንደሚችሉ ሕብረተሰቡ ቀድሞ በመረዳት በየአካባቢው ጠንካራ ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ እና ለፖሊስ ጥቆማ በማድረስ በክልሉ አስተማማኝ ሠላም እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን ነው ምክትል ኮሚሽነር ሰኢድ ያስታወቁት፡፡ በፀጥታ መዋቅሩ እና በሕብረተሰቡ ትብብር የተገኘውን የተሻለ የፀጥታ ሁኔታ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በመናገር ኅብረተሰቡም የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በክልሉ የጦር መሣሪያ የማስፈታት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ በመሆኑ ሕብረተሰቡ ውዥምብር ውስጥ እንዳይገባም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡ መመሪያዉ በሚፈቅደው መሠረት በ2011 ዓ.ም ሕብረተሰቡ የግል ትጥቁን ሕጋዊ አድርጎ እንዲንቀሳቀስ መደረጉ ይታወሳል፡፡ ‹‹ሕጋዊ ትጥቅ እንዲኖር የፈቀደ መንግሥት ትጥቅን የሚያስፈታበት ምንም ምክንያት የለውም›› ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ በሕገ-ወጥ ትጥቅ እና የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ ግን የክልሉ መንግሥ...

Hegereef har’a Biqiltuu dhaabuu qabna!

ምስል
Finfinnee Waxabajjii 27/2011(Tolawaaq Waarii) Dhimmi biqilqtuu dhaabuu xiyyeeffannoo guddaa argachuu qaba.Waa’een Biqiltuu dhaabuu bara jijjiirraa jaarraa amma keessa jirru kana irraa eegalee akka xiyyeeffannoo argatuuf carraaqqiin taasifameera.Garuu hamma barbaadametti bu’aan hin argamne. Duulli Bar-kumee haarawaatti Biqiltuu lama dhaabuu adeemsifamee ture.Bu’aan duula sanaan argame rakkoo manca’ina qabeenya bosonaa biyya keenyaa wajjin wal qabatee jiru wajjin yoo wal bira qabamee ilaalamu kan wal gitu miti. Biqiltuun duulaan dhaabame sunis meeqatu late?meeqatu bade? jedhamee yoo xiinxalamu deebiin quubsaan waan jiru hin fakkaatu. Kanaaf kan darbe dhiisuudhaan kan fuulduraa yaaduutu wayya waan ta’eef waa’ee duula Biqiltuu dhaabuu baranaatiif xiyyeeffannoo barbaachisu kenninee socho’uu qabna. Muummichi ministiraa keenya jabaan fakkeenya ta’anii biqiltuu dhaabaa jiru.Kutannoofi xiiqiin Dr.Abiy Ahmad hunda kakaasuu kan danda’udha.Carraaqii guddaa kana kanneen gadi qican jiraat...

ብርጋዲዬር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መልዕክት እንዲተላለፍ ስለማዘዛቸው፡፡

ምስል

ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

ምስል
ፊንፊኔ ግንቦት 28፣2011 (ቶለዋቅ ዋሪ) ዶክተር ንጉሴ ምትኩ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ፡፡ ዶክተር ንጉሴ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ ነው በዋና ስራ አስፈፃሚነት የተሾሙት፡፡ የቀድሞው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ስዩም መኮንን በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ሹመቱ የተካሄደው፡፡ ሹመቱ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየት ተሰጥቶበት በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡ ምንጭ:FBC

Ergaa Ayyaana Iid alfaxiir I/A/Pi/M/N/Oromiyaa

ምስል
Hawaasa musliimaa maraan baga ayyaana sooma hiikkaa/ id al faxiiriin nagayaan isin gahe. Idal fixriin guyyaa ga mmachuu guyyaa maatii ollaa fi firaa wajjiin akkasumaas guyyaa waan qabanirraa qoodanii hiyyeessaa waliin jaalalaaf gammachuun dabarsan, guyyaa kan rakkateef dhaqqaban,kan dhibameef aafiyaa, dhala namaa maraaf waan gaarii hawwuudhaan baga ittiin nu gahe waliin jedhaniidha. Ji’aan Ramadaanaa baranaa ammo Ji’aa Jaalalli diiniin islaamummaa itti dhugoome miidhaginni, rakkoon majilisaa hiikkatee karaa qabatee tokkummaa fi gamtaan obbolaa keenya itti mirkanaawe, islaamummaan nageenya, islaamummaan kan walitti muufale afooyitulellaah jadhee ittiin walitti araaramu, islaamummaan qabbanaa fi miidhagina, jaalalaa fi kabajni dhala namaaf qabnu, jaalalli obbolummaa firaa fi ollaa qabnu gochaan miidhagee itti mullatee darbeedha. Keessattuu Jaalalaa fi hammachuun obbolaa keenya naannoolee Ollaa waliin qabnu akkaataa diiniin islaamummaa ajajuun waliin hafxiraa tokkoon keenya isa...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1440ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት:

ምስል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1440ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ለ1440ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ዒድ አል ፈጥር - የጾም ወር ማጠናቀቂያና መሸኛ በዓል ነው። በረመዳን ወር መጨረሻ እና በሸዋል ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ የሚውል በዓል ነው ዒድ-አልፈጥር። በቅዱሱ የረመዳን ወር ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ሙስሊሙ ራሱን ከመብልና መጠጥ ከማቀብ ባለፈ በመልካም እና በጎ ተግባርም መትጋት ይጠበቅበታል። በዚህ ረገድ፣ ነቢዩ መሐመድ (ሠለላ አለይህ ወሠለም) “አስከፊ ንግግር እና ተግባራትን ያልተወ ሠው ከምግብና ከመጠጥ መታቀቡ ብቻ በአላህ ዘንድ ከቁምነገር የሚገባ አይደለም” በማለት ትክክለኛውን መንገድ ማመላከታቸው በሐዲስ ሰፍሮ ይገኛል። በመሆኑም በጾምና ሰላቱ፣ በምስጋናና በልግስና ታጅቦ ሠላሳ ቀናትን የሚዘልቀው የረመዳን ወር ነፍስን አለምላሚ ሥጋን ግን ጎሳሚ፣ ከዚያም በተጨማሪ ፈታኞቹ ቀናት ካለፉ በኋላ የሚመጣው አዲስ ቀን፣ የኢድ በረከትን የታደለና ድካምንም የሚያስረሳ ተደርጎ ይወሰዳል። በእምነታችን የተነሳ ትዕዛዛቱን ለመፈፀም በጽናት የምንቀበለው መከራ ሁሉ ከባድ ቢሆንም ማለፉ ግን አይቀሬ ነው። ያልፋል። አስተላለፉ ግን ‹ሲምር ያስተምር› እንደሚባለው ምሕረትም ትምህርትም አግኝተንበት ነው። የረመዳን ወርና መሸኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል ከመነሻ እስከመድረሻ ያለው ሥርዓት በእንዲህ ዓይነቱ በረከት የታደለ ነው። የረመዳን ወር የጾምና የመታዘዝ፣ የድካምና የመፈተንም ወቅት ነው። ነገር ግን ከሚበላባ...