የኦህዴድ ጠንካራና ታሪካዊ ውሳኔዎች አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል


የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በዚህ ሳምንት ለሶስት ቀናት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በወሳኝ የክልሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ እጅገ በጣም ጠቃሚ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።


የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት ባካሄደው ስብሰባው ላይ ያስተላለፋቸውን የተለያዩ ውሳኔዎች አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል።በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ መሰረት:

1.በቅርቡ በተከሰተው ብጥብጥ ህይወታቸው ለጠፋ ወገኖችና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች የሰተማውን ሃዘን የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ገልጧል

2.የአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ሙሉ በመሉ እንዲቀር ተደርጓል
3.የአሮሚያ  ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ማግኘት ያለበት ልዩ ጥቅም በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲያገኝ እየተሰራ ነው ብሏል

4. በቅርቡ ጨፌ ኦሮሚያ ባፀደቀው የከተሞች አዋጅ አንዳንድ አንቀፆች ላይ ህዝቡ የጥርጣሬ ጥያቄዎች ስለአቀረበ አዋጁ ወደ ጨፌ ተመልሶ በድጋሚ እንዲታይ ተወስኗል

5.የመልካም አስተዳድር ችግሮች ቀደም ሲል በድርጅቱ 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከህዝብ ጋር መፍትሄ እንዲገኝ በቀጣይነት እንደሚሰራ ተወስኗል

6.የጥፋት ኃይሎች ወደ ህግ ቀርበው እንዲጠየቁ ከብህረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚደረገው ጥረት እንዲቀጥል የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ መወሰኑን አረጋግጠል።

7.የማስተር ፕላኑን ጉዳይ ተገን በማድረግ በተነሳው ሁከት ንብረታቸው የወደመባቸው ወገኖች ከህዝብ ጋር በመተባበር እንዲ ቋሙ ይደረጋል።

8.ግጭቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል ያልተቆጠበ ጥረት ላደረጉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፤የድርጅቱ አባላት፤የኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች ምስጋና በማቅረብ ለህዳሴው  ጎዞ ስኬት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

9.ኦህዴድ ለህዝብ ፍላጎት ተገዥ ሆኖ የህዝብን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና ለዚህም የተለመደው ትብብር ከህዝብ እንዲደረግለት ጠይቋል።

10 የክልሉ ህዝብ ያነሳቸው ጥያቄዎች ድርጅቱ እየገነባ ያለው ስርዓት ውጤት በመሆኑ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር አንዳለውም የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አረጋግጧል።

አህዴድ የህዝብ ወገተኝነቱን ያለ ምንም ማቅማማት በተግባር አሳይቷል።የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በተለይ በማስተር ፕላኑ ጉዳይ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ምንም አይነት አሻሚ ትርጉም የለው።የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ  ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በሙሉ በሙሉ ቆማል መባሉን ተከትሎ ማስተር ፕላኑ ቀርቷል? ወይስ ተሰርዟል?በሚል የሚናፈሰው ወሬና የጥፋት ኃይሎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለማንም የሚጠቅም አይደለም ማስተር ፕላኑ በኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት መሰረት ቀርቷል።ይህን ውሳኔ  መቀልበስ የሚችል ማንም ኃይል  የለም፤ሊኖርም አይችለም።በዚህ ጠንካራና ታሪካዊ ውሳኔ ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ከመፍጨርጨር ይልቅ ጠቃሚው ነገር የኦህዴድን ጠንካራና ታሪካዊ ውሳኔዎች ማድነቅ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman