ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ

የክልላችንንህዝብ ፍላጎትና ጥቅም በማክበርና በማስከበር በኩል የመንግስት ዝግጁነት ተጠናክሮ ይቀጥላል
መንግስትና ህዝብ የብዙሀነት፤ የብህር ብሄረሰቦችና፤ የሀይማኖት እኩልነት እንዲሁም የአመለካከት ልዩነትን ማስተናገድ የሚችል የፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ስርአት በትግላቸዉ መገንባት ችለዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና ሰፊው ህዝባችን ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ባለፉት አመታት  ፈጣን ልማት፤ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና አስተማማኝ ሰላም እየተረጋገጠ መጥቷል፡፡


የክልላችን ሰፊው ህዝብና መንግስት በአንድ  ሀሳብና በተባበረ ክንድ ትልቁ ጠላታችን በሆነው በድህነትና በኋላቀርነት ላይ ባካሄዱት ዘመቻ  በማያባራ ጦርነትና በድህነት የሚታወቀው ህዝብና መንግስት ታሪክ ተቀይሮ የለውጥና የተስፋ ተምሳሌት በመሆን ማንም ሊክደው የማይችል ድል ተመዝግቧል፡፡ እስካሁን በተደረገው የህዳሴ ጉዞም በኢኮኖሚው ዘርፍ በታሪካችን ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

ባለፉት አመታት   የአይቻልም መንፈስን በመስበር ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቧል፡፡ በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በቅርቡ የገጠመንን የዝናብ እጥረትን መቋቋም የሚችል አቅምም እየተፈጠረ ነው፡፡

በማህበራዊ ልማትና በመሰረተ ልማትም በብዙ የሚቆጠሩ ዜጎቻችን የትምህርት እድል፤ የጤና አገልግሎትና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋትና በማግኘት ህዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ አልፎ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ ሀገራችንና ክልላችን ለወጠኑት ራዕይ ጉዞ ተስፋ መስጠት ጀምሯል፡፡

የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና መልካም አስተዳደር ማስፈንን አስመልክቶ ከነፍጠኛው ስርአት ውድቀት ማግስት አንስቶ ብዙ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ስልጣን የሚመነጨው ከህዝብ ድምጽ ብቻ እንዲሆነ ያረጋገጡ  አምስት ሰላማዊ፤ ፍትሀዊ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ተካሂደዋል፡፡ ሁሉም የፖለቲካ አማራጮች ለህዝብ ቀርበው ህዝቡም ይሆነኛል የሚለውን በድምጹ ብቻ እየወሰነ መጥቷል፡፡ ይህም ህዝብና መንግስታችን የመድበለ ፓርቲ ስርአት ለመገንባት ፍላጎትና እምነት እንዳላቸው የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ ነው፡፡

ህዝባችን በለውጥና እድገት ጎዳና ውስጥ በመግባቱ የልማት ፍላጎቱ ጨምሯል፡፡ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም የህዝባችንን ፍላጎት ያላረካና በእድገቱ ላይ እንቅፋት እንደሚሆን መንግስት ይረዳል፡፡ ከህዝቡ ጋር በመሆን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያለው ዝግጁነት ከፍተኛ ነው፡፡

የክልላችን ተጨባጭ ሁኔታ ይሄ ሆኖ ሳለ ሰሞኑን መንግስት የክልላችንን ህዝብ ይጠቅማል ብሎ  የያዘው ረቂቅ እቅድ ላይ ህዝቡ የግልጸኝነት ጥያቄና የተፈጠረበትን ጥርጣሬ ለማጣራት ያነሳውን ጥያቄ የጥፋት ኃይሎች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለፖለቲካ አላማ በማዋላቸው ያልተፈለገ ብጥብጥ ተፈጥሯል፡፡

በዚህ ብጥብጥም የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ ንብረትም ወድሟል፡፡ ስለዚህም ከሁሉም አስቀድሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ሀዘን መግለጽ ይወዳል፡፡ ለኦሮሞ ህዝብና በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችም መጽናናትን ይመኛል፡፡

የህዝብ ጥያቄና የጥፋት ኃይሎች አላማ የተለያየ መሆኑን የተገነዘበው ሰፊው ህዝባችን ችግሩ እንዳይስፋፋ በዘር፤ በኃይማኖት፤ በጾታና በመሳሰሉት ሳይከፋፈል ላደረገው ርብርብ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ማመስገን ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸዉን ማበረታታትና የመልሶ ማቋቋም ስራ ከህዝቡ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ በማሟላት ከህዝቡ ጎን እንደሚቆም እናረጋግጣለን፡፡

 የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝቡን ጥያቄና ፍላጎት በአክብሮት ይመለከተዋል ከዚህም በመነሳት ትናንት የመረጠውን ህዝብ ስሜት በማዳመጥ የልማትና የሰላም ጥያቄዉን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛል ነገም ከአሁን ቀደሙ በበለጠ የህዝቡን ጥቅምና ፍላጎት በማዳመጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡

በዚሁ መሠረት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ከጥር 1-3/2008 ድረስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የመንግስትን አቋምና የትኩረት አቅጣጫ በቁርጠኝነት የሚፈፅም መሆኑን በድጋሚ ይገልፃል፡፡ በዚሁ መሠረት

1. የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ለህዝብ ልማት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ ጥያቄና ጥርጣሬን ሲፈጥር እንደነበር ይታወሳል፣ መንግስትም በዚህ ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ሰፊ ውይይት ጥያቄው የህዝብ መሆኑን ተረድቷል፡፡ ስለዚህ ይህ የተቀናጀ የጋራ እቅድ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እቅዱ ሙሉ በሙሉ መቅረቱን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያረጋግጣል፡፡ 

2. የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማግኘት ያለበትን ልዩ ጥቅም በህገመንግስቱ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንደሚታወቀው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ትላልቅ የህዝብ ጥያቄዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ከህዝቡ ጋር በመሆን ሲስራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ መስተዳደር ማግኘት ያለበት ልዩ ጥቅም ላይ ከህዝብ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ሲነሱ እንደነበር የክልሉ መንግስት ተረድቷል ሰለዚህ ኦህዴድ ባሰቀመጠው አቅጣጫ ላይ ይሰራል፣ የሚጠበቅበትን ሁሉ በቁርጠኝነት ይወስናል፡፡

3.  የኦሮሚያ ከተሞች አዋጅን አስመልክቶም በ5ኛው የጨፌ ኦሮሚያ የስራ ዘመን አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሳባ ላይ የፀደቀውን የከተሞች አዋጅ አሰመልክቶ በአንዳንድ አንቀፆች ላይ ይታይ ተብሎ ከህዝቡ የቀረበው ጥያቄ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የኦሮሚያ ብሔራዊ መንግስት ለጨፌ በማቅረብ ጥርጣሬና ቅሬታ የቀረበባቸውን አንቀፆች በድጋሚ አይቶ የሚያስተካክል መሆኑን ማረጋገጥ ይፈልጋል፡፡

4. በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ከህዝቡ ጋር ባደረገው ውይይት  መሠረት በተጨማሪም ከሰሞኑ ባደረግነው የሰላም ወይይት በየጊዜው እየተመዘገቡ ካሉ ልማቶች ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ መሆኑን አንስቶ ልማት የበለጠ እንዲያድግ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች እንቅፋት እንደሆኑ እንደሁም የመልካም አስተዳደር  ጥያቄዎች መፍትሄ ባለማግኘታቸው ሰሞኑን ከህዝብ ጋር ባደረግነው ውይይት የበለጠ መረዳት ተችሏል፡፡ መንግስትም እነዚህ ችግሮች እንዳሉ በተለያየ ጊዜ ሲገልፅ እንደነበርና አሁንም ለጥያቄዎች ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መመልከት መነሻቸውንና መገለጫቸውን በመለየት ከስር መሠረቱ መፍትሄ እንዲያገኙ ጊዜ ሳንሰጠው ከህዝባችን ጋር ሆነን ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን ይገልፃል፡፡

በተለይም በከተማና በገጠር ወጣቶች ዘንድ የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር፣ የተጨማሪ የልማት ጥያቄዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የፍትህ ሥርዓቱ ላይ ህዝቡ የሚያነሳውን ቅሬታዎች ከመሰረታቸው መፍትሄ እንዲያገኙ ከህዝቡ ጋር ሆኖ በጥንካሬ ይሰራል፡፡ ህዝቡም ቅሬታ እንዳነሳ ሁሉ ለመፍትሄውም ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡

5.  የህዝብ ጥያቄን ተገን በማድረግ ለጥፋት ሴራቸው ተጠቅመው ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ የተንቀሳቀሱ ኃይሎች በምንም መልኩ ህዝብና መንግስት ጋር ተቀባይነት አያገኙም ሥለዚህ ይህንን የጥፋት ሴራ ለማስቆምና የህዝቡ ሰላም እንዲጠበቅ ህዝብና መንግስት ትልቅ ተሳትፎ በማድረጋቸው መሪጋጋት ተፈጥሯል፡፡ ሥለዚህ በተፈረው አለመረጋጋት የሰውን ህይወት በማጥፋት፣ አካል በማጉደል ንብረት በማውደም የተሳተፉ፣ በማቀነባበርና በመምራት በተግባርም በመሳተፍ ንብረትን ያወደሙ አካላት ላይ በተጨባጭ ማስረጃ በማስደገፋ በህግ እንደጠየቁ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ህዝቡ በማጋለጥ ትናንት ሲያበረክት የነበረውን አስተዋፅኦ እንደቀጥልበት መንግስት ጥሪዉን ያሰተላልፋል፡፡

በሌላ በኩል በስህተትም ሆነ ሳያዉቁ ወደ ብጥብጡ የተቀላለቀሉ አካላትን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሆደ ሰፊ በመሆን በምክርና በተግሳፅ የሚያልፋቸው መሆኑን በዚህ አጋጣም መግለፅ  ይፈልጋል፡፡  ከዚህ ሌላ የኃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች የሐገር ሽማግሌዎችና ወላጆች በኦሮሞ ባህልና እሴት መሠረት ብጥብጥ እንዳይነሳና ሰላም እንዳይደፈርስ የነበራችሁን ድርሻ የበለጠ እንድታጠናክሩ መልዕክቱን ያሰተላልፋል፡፡

ከዚህ ውጪ በተለያዩ መንገዶች ከእውነት የራቀ የሐሰት ፖርጋንዳ በመንዛት ህዝቡን ለማደናገር የሚደረገዉን ሴራ ህዝቡ ተረድቶ የተጀመረውን የህዳሴ ጎዞ ለማስቀጠል በእልህና በቁርጠኝነት እንዲሰራ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡
  
   የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሚኒኬሽን  ጉዳዮች ቢሮ
ጥር 8/2009




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman