የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ተከስቶ በነበረው ሁከት በስህተትም ሆነ ሳያውቁ የተሳተፉ አካላትን በምክርና ተግሳፅ እንደሚያልፋቸው ገለፀ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የህዝብን ፍላጎትና ጥቅም የማክበርና የማስከበር ሚናው ተጠናክሮ እንደሚቅጥል አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።


ክልሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መንግስት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ያሳለፈውን ውሳኔ በቁርጠኝነት የሚፈፀም መሆኑን አረጋግጧል።

በዚሁ መሠረት የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ለህዝብ ልማት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ ጥያቄና ጥርጣሬን ሲፈጥር እንደነበር ይታወሳል።

መንግስትም በዚህ ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ሰፊ ውይይት ጥያቄው የህዝብ መሆኑን በመረዳቱ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የተቀናጀ የጋራ እቅዱ ሙሉ በሙሉ መቅረቱን የክልሉ መንግስት አረጋግጧል።

የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማግኘት ያለበትን ልዩ ጥቅም በተመለከተ የክልሉ መንግስት ኦህዴድ ባሰቀመጠው አቅጣጫ ላይ እንደሚሰራና የሚጠበቅበትን ሁሉ በቁርጠኝነት እንደሚወስንም በመግለጫው አመላክቷል።

የኦሮሚያ ከተሞች አዋጅን አስመልክቶም የኦሮሚያ ብሔራዊ መንግስት ለጨፌ በማቅረብ ጥርጣሬና ቅሬታ የቀረበባቸውን አንቀፆች በድጋሚ አይቶ የሚያስተካክል መሆኑን ነው ያረጋገጠው።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ ሁሉም ሰፍራዎች በህዝብ እና በመንግስት ትልቅ ተሳትፎ ሙሉ መረጋጋት መፈጠሩን የጠቀሰው መግለጫው፥ የህዝብ ጥያቄን ተገን በማድረግ ለጥፋት ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ የተንቀሳቀሱ አካላት ላይ በተጨባጭ ማስረጃ በማቅረብ በህግ እንደጠየቁ በሚደረገው እንቅስቃሴ ህዝቡ የጀመረውን የማጋለጥ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም የክልሉ መንግሰት ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል በስህተትም ሆነ ሳያውቁ ወደ ብጥብጡ የተቀላለቀሉ አካላትን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሆደ ሰፊ በመሆን በምክርና በተግሳፅ የሚያልፋቸው መሆኑን ነው በመግለጫው ያስታወቀው።

የክልሉ መንግስት በጥቂት አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከት ለደረሰው ህይወት መጥፋት እና ንብረት መውደም የተሰማውን ሃዘንም ገልጿል።

መንግስት ከክልሉ ህዝብ ጋር በመሆን ጉዳት የደረሰባቸውና ንብረት የወደመባቸው ዜጎችን እንደሚደግፍም በመግለጫው ተጠቅሷል።

በመግለጫው የኃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች የሀገር ሽማግሌዎችና ወላጆች በኦሮሞ ባህልና እሴት መሠረት ብጥብጥ እንዳይነሳና ሰላም እንዳይደፈርስ ለነበራችው ድረሻ ምስጋና ያቀረበው የኦሮምያ ክልል መንግስት ይህንን በጎ ተግባራቸውን የበለጠ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርቧል።





አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman