የኦህዴድ ጠንካራና ታሪካዊ ውሳኔዎች


የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በዚህ ሳምንት ለሶስት ቀናት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በወሳኝ የክልሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ እጅገ በጣም ጠቃሚ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።


የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት ባካሄደው ስብሰባው ላይ ያስተላለፋቸውን የተለያዩ ውሳኔዎች አስመልክቶ ትናንት ምሽት ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል።በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ መሰረት:

1.በቅርቡ በተከሰተው ብጥብጥ ህይወታቸው ለጠፋ ወገኖችና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች የሰተማውን ሃዘን የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ገልጧል

2.የአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ሙሉ በመሉ እንዲቀር ተደርጓል

3.የአሮሚያ  ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ማስተዳድር ማግኘት ያለበት ልዩ ጥቅም በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲያገኝ እየተሰራ ነው ብሏል

4. በቅርቡ ጨፌ ኦሮሚያ ባፀደቀው የከተሞች አዋጅ አንዳንድ አንቀፆች ላይ ህዝቡ የጥርጣሬ ጥያቄዎች ስለአቀረበ አዋጁ ወደ ጨፌ ተመልሶ በድጋሚ እንዲታይ ተወስኗል

5.የመልካም አስተዳድር ችግሮች ቀደም ሲል በድርጅቱ 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከህዝብ ጋር መፍትሄ እንዲገኝ በቀጣይነት እንደሚሰራ ተወስኗል

6.የጥፋት ኃይሎች ወደ ህግ ቀርበው እንዲጠየቁ ከብህረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚደረገው ጥረት እንዲቀጥል የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ መወሰኑን አረጋግጠል።

7.የማስተር ፕላኑን ጉዳይ ተገን በማድረግ በተነሳው ሁከት ንብረታቸው የወደመባቸው ወገኖች ከህዝብ ጋር በመተባበር እንዲቃቋሙ ይደረጋል።

8.ግጭቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል ያልተቆጠበ ጥረት ላደረጉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፤የድርጅቱ አባላት፤የኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች ምስጋና ቀርቧል።

9.ኦህዴድ ለህዝብ ፍላጎት ተገዥ ሆኖ የህዝብን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና ለዚህም የተለመወድ ትብብር ከህዝብ እንዲደረግለት ጠይቋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman