ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ሙሉ መግለጫ
የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው አመት በድርጅታችን የተጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ አፈፃፀም በዝርዝር መገምገም ጀምሯል፡፡
በድርጅታችን ኢሕአዴግ የቆየ ባሕል መሰረት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያካሂደው የትግል ሂደት የሚያጋጥሙትንጉድለቶች ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ በጥልቀት ይገመግማል። ግምገማውን መሰረት በማድረግም ራሱን በራሱ ያርማል። እነሆም የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቀደምሲል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የነበሩና የተተኩ ነባር ታጋዮችን ባከተተ አግባብ ከታህሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ኢሕአዴግ የህብረተሰቡን ለውጥ የሚመራ ድርጅት ሲሆን አስተማማኝ የለውጥ መሪ የሚሆነውም ራሱንም እየለወጠ መሆኑን በፅኑ ያምናል፡፡
እናም ሁሌምራሱን እየገመገመ ከነባራዊው ሁኔታ የሚመጥን ድርጅታዊ ቁመና ለመያዝ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋልበአሁኑ ወቅት አገራችን በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገትአቅጣጫ ወደፊት እየገሰገሰች እንደምትገኝ መላ የአገራችን ሕዝቦችና አለም አቀፍ ማህበረሰብ ጭምር በገሃድ የመሰከሩት ሃቅ ነው።
በአሁኑ ወቅት በአገራችን በመታየት ላይ የሚገኙት በዋነኛነት ከልማት፣ ከመልካም አስተዳደርና ከሰላም ጋር የተያያዙ ችግሮች የማያዳግምና መሰረታዊ የሆነመፍትሄ የሚሰጡ ይሆናል። እስካሁን በተደረጉት ግምገማዎችም የችግሮቹን አይነተኛ ባህሪዎችና ዋነኛ መንስዔዎች አስመልክቶ ዝርዝር ውይይት የተደረገሲሆን በአመራሩ ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላቀ አኳኃን የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር ተችሏል። የአስተሳሰብ አንድነት ለተግባር አንድነት መሰረት በመሆኑምኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰጡትን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንደወትሮው በላቀ ደረጃ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት በፈጠረው ተስፋና የተከመሩ ፖለቲካዊ ችግሮች ፊታችን ላይ በደቀኑት ስጋት መካከል አጣብቂኝ ውስጥ የገባችበት ሁኔታ እንዳለ በትክክል ይገነዘባል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የተጀመረውን ፈጣን እድገትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታእስካሁን የመጣበትን ርቀት ለማሳካትም ሆነ ወደፊትም ለማስቀጠል በኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ካሁን በፊት የነበረው አኩሪ በመተጋገል ላይየተመሰረተ አንድነት በቦታው ላይ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ያምናል። ስራ አስፈፃሚው እስካሁን ባደረገው ግምገማ በአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶችመካከል ያለው ግንኙነት በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የርስ በርስ መጠራጠር ያመዘነበት፣ አለመተማመን ቀስ በቀስ እየገነነ የመጣበት መሆኑን በጥብቅተገንዝቧል። በዚህ ላይ ተመስርቶ በተደረገው ሰፊና ጥልቅ ውይይት በዚህ ረገድ የታዩ ችግሮችን በስፋት መርምሮ የቆየውን የሃሳብና የተግባር አንድነትለማምጣት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል።
ስራ አስፈፃሚው በተጨማሪም ባለፉት ሁለት አመታት ድርጅታችን ኢሕአዴግ ያደረገው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በርካታ አበረታች ውጤቶች የተገኙበትቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ጥልቀት ያልነበረው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተመልሰን ወደ አዘቅቱ መመለስ መጀመራችንን በትክክል አስቀምጧል። በሃገራችንየተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በዋነኛነት የድርጅታችን አመራር ያሳየው ድክመት የፈጠራቸው መሆናቸውን በሚገባ ይገነዘባል።ሃገራችን በአሁኑ ሰዓት ለምትገኝበት አስጊ ሁኔታ ድክመቱ ያደረገው አስተዋፆ ከፍተኛ ነው።
የድርጅታችን በየደረጃው ያለው አመራር ከሞላ ጎደል የዚሁ ድክመት ተጋሪ ቢሆንም ስራ አስፈፃሚው የዚህ ችግር ዋነኛ ባለቤት መሆኑንና ሕዝባዊ ወገንተኝነቱእየተሸረሸረ ችግሮችን በቁጭት መንፈስ ከመፍታት ይልቅ የእርስ በርስ ንትርክ ላይ እንደሚያተኩር መግባባት ላይ ተደርሷል።
የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ በድርጅታችን ውስጥ ያለበት ደረጃ ከፍተኛ ድክመት የሚስተዋልበት መሆኑንና ህብረተሰባችን ውስጥ ጤናማ ዴሞክራሲያዊሕይወት በመፍጠር ረገድ ያደረሰውን ተፅዕኖ ስራ አስፈፃሚው በሚገባ ይረዳል።
እስካሁን በተደረገው ጥልቅ ግምገማ ከስኬት ጎዳና እያራቁን የሚገኙ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት መታጣት፣ የርስ በርስ መጠራጠር፣ የውስጠ ድርጅትዴሞክራሲ እጦትና የሕዝባዊ ወገንተኝነት መሸርሸር ተገቢ ውይይት ተደርጎባቸው የሕዝባችንን የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ፣ የልማትና የሰላምጥያቄዎችን በሚገባ ለመመለስ በሚያስችሉን አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ተደርሷል። ከምንም ነገር በላይ በሃገራችን በየቦታው የሚከሰቱ ግጭቶችንከመፍታትና የፌዴራል ስርዓታችንን ከአደጋ ከመታደግ አንፃር የህግ የበላይነትና ተጠያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለብን የስራአስፈፃሚ ኮሚቴው የጋራ አቋም ይዟል።
የድርጅታችን ስራ አስፈፃሚ ለሃገራችን ሕዝቦች ጥያቄ በተሟላ መልኩ መመለስና ለፌዴራል ስርዓታችን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥና ለዚህ ግብ ዝግጅት አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችለውን የተሳካ ውይይትና መተጋገል በፅናት ቀጥሎበትበቅርብ ጊዜ በድል የሚጠናቀቅ ይሆናል ሂደቱንም ለመላው የሀገራችን ሕዝቦችና ለኢሕአዴግ አባላት በተከታታይ የሚገልፅ መሆኑን ያስገነዝባል
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ