ልጥፎች

ከጁን, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

Dr.Abiy guyyaa 87’tti Samaraa jiru “Ajaa’ibsiisaadha”

Muummichi ministiraa Dr.Abiy Ahmad erga muudamanii har’a guyyaa 87ffaa lakkoofsisaniiru.Hayyuun keenya kun taayitaa biyya bulchuu erga qabatanii asitti boqonnaa tokko malee hojjechaa akka jiran argaa jirra.Carraaqqiin isaanii kun akka waan ajaa’ibsiisaatti ilaalamaa akka jiru yaada namoonni kennan irraa hubachuun nama hin dhibu. Borumtii taayitaa qabatanitti gara naannolee adda addaa deemuudhaan dhimmoota adda addaa irratti bakka bu’oota qaamolee hawaasaa gara garaa wajjin mari’atan.Kanaanis fudhaatamummaa ummata biratti qaban daran dabalan Itti aansee gara biyyaalee ollaa imaluudhaan dhimmoota waliin wajjinii irratti mari’achuun lammiiwwan biyya keenyaa sababa yakkoota adda addaatiin biyyaalee ollaatti hidhaman gadi lakkisiisan.Kanaanis jaalatamummaan ummata bal’aa biratti qaban akka dabaluuf balballi bal’aan baname. Biyyaalee bahaa jiddu galeessaa keessaa gara Sa’udii Arabiyaafi Immireetoota Araba gamtoomanii dhaqanii daawwachuudhaan bu’aan biyyaaf argamsiisan maalfa’i a...

ምኞታችን እንዲሳካ ከቸልተኝነት የፀዳ ጥንቃቄ ያስፈልገናል!

ምስል
‹‹ሌብነትን እምቢኝ አሻፈረኝ ያላችሁ ዕለት እኔን እንዳመሠገናችሁ ይቆጠራል፡፡ ይኼ ክልል የእኔ፣ ይኼ ወሰን የእኔ ነው ውጡልኝ መባባልን አቁመን፣ በፍቅር ተግተን ለአገራችን መሥራት የጀመርን ዕለት ያኔ ምሥጋናችሁ በሌላችሁበት እንደደረሰን ቁጠሩት፡፡ ልጆቻችሁን ከፊደል እኩል የአገር ፍቅር አስተምራችሁ ኢትዮጵያዊነትን ያላበሳችኋቸው ዕለት ያኔ ምሥጋናችሁ በፍሬ ይደርሰናል» ያሉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ሕዝብ አደራ የሰጡት ቃል ሆኖ ይታወሳል፡፡ ‹‹ለውጥን እንደግፍ ዴሞክራሲን እናበርታ›› በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ሕዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ‹‹ኢትዮጵያን ሊተካ የሚችል አንዳች ነገር አልተሰጠንም፤ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ገናናነቷ እንደምትመለስ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ አይኑራችሁ፡፡ ‹‹ገና ኃላፊነት ከተረከብን መንፈቅ ሳይሞላን ፊት ለፊታችን እንደ ተራራ የተቆለለውን ግርዶሽ ሳንገፍፍ ፊት ለፊታችሁ ቆመን ምሥጋና ለመቀበል የሚያስችል አቅም አላደረጀንም፡፡ ነገር ግን ጥላቻ አክስሮናል፣ አጉድሎናል፣ ፍቅር ግን ያተርፋል፤ ያሻግራል ብላችሁ በተስፋ ተሞልታችሁ በምሥጋና ጀምራችኋልና በፍቅርና በአንድነት ጀምሮ መጨረስ የተሳነው ስለሌለ ለዛሬው የፍቅርና የምሥጋና ቀን መድረስ ከሚገባን ማማ የሚያደርሰን የመጀመርያው ጡብ መቀመጡን ያሳያል›› ካሉ በኋላ ‹‹የዛሬዋን ቀን እንድናይ የዛሬዋን ቀን ያላዩ፣ እንድንኖር ሲሉ የሞቱ፣ እንድንከበር ሲሉ የተዋረዱ፣ እንድንፈታ ሲሉ የታሰሩ፣ ለሕይወታችን ሕይወታቸውን የገበሩ ሰማዕታትን በዚህ የከበረ ቦታ ቆመን ልናመሠግናቸው ይገባል፤ እነርሱ ያለ እኛ ሊኖሩ ይችሉ ነበር፡፡ እኛ ግን ያለ እነርሱ መኖር አይቻለንም›› ...

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ አብይ አህመድ የመልካም ምኞት መግለጫ ኢድ ሙባረክ!!

ምስል
ኢድ ሙባረክ!! የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ አብይ አህመድ የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ። የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ አብይ አህመድ ለኢድ አልፈጥር በአል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ቅዱሱን የረመዳን ወር በተለመደው የመረዳዳት፣ የመጠያየቅ፣ የመደጋገፍ እና የመከባበር ስሜት አገባዳችሁ እንኳን ለታላቁ የኢድ- አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ- አደረሰን፡፡ ኢድ ሙባረክ፡፡ ኢትየጵያውያን ሙስሊሞች 1.9 ቢሊዮን ከሚደርሱ የአለማችን ሙስሊም ወገኖቻችን ጋር በድምቀት የሚያከብሩት ይህ በአል በሀገራችን ኢትዮጵያ ሲከበር የሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያውያን ወደመሆን የፍቅር ሰገነት ከፍ ይላል፡፡ በኢትዮጵያችን በሙስሊሙ በአል ክርስቲያኑ፤ በክርስቲያኑ በአል ዋቄፈታው፤ በኢድ- በፋሲካው- በገና በእሬቻው የእንኳን አደረሰህ፣ እንኳን አደረሰሽ ቅብብሉ መልካም ምኞት እስከታከለበት ዝይይር በሚዘልቅ የፍቅር ሸማ ተከብክቦ ይሄው ዛሬ ደርሷል፡፡ ቅዱሱ የረመዳን ወር፣ የጾም፣ የጸሎት እና ከፈጣሪ ጋር የመገናኛ ልዩ ወር እንደመሆኑ መጠን፣ ኢድ አልፈጥርም፣ የፍቅር እና የበረከት፤ የይቅርታ እና የአብሮነት ድንቅ በአል ነው፡፡ ኢድ ሙባረክ! የኢድ አልፈጥር በአል የሚውለው፣ በሸዋል ወር የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡የሸዋል ወር ደግሞ፣ የታወቀ የበጎ ስራ እና የልገሳ ወር ነው፡፡ በፍቅሩና መተሳሰቡ ላይ በጎ ስራው ሲታከል፣ ጊዜው ይበልጥ የተባረከ ይሆናል፡፡ ለሙስሊም የሀገሬ ልጆችም ሆነ ለመላ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የምመኘውም ሙሉ ዘመናችን የሸዋል ወር እንዲሆንልን ነው፡፡ የአብሮነት እድሜያችን ሁሉ በሸዋል ወር በሚከቡን...

የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ አውጥቷል

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ አውጥቷል። የመንግስት መግለጫ በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እና አገራዊ ድባብ ጠብቆ ማስቀጠል የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆን አለበት ብሏል:: በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሰላምና መረጋጋት ብሎም እየታየ ያለው አገራዊ መግባባትና የህዝቦች አንድነት የአገራችንን ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በአፍሪካ ደረጃ ብሎም በዓለም አቀፍ መድረኮች ውጤት እያስገኘ ያለ ስኬት ነው ብሏል መግለጫው። በዚህም ሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን የምንገኝበትን የአፍሪካ ቀንድ እና የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ ከመሰረቱ የሚለውጥ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናችን ይታወቃል። በዚህም ዓለምን ያስደመመ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በማሰመዝገብ ላይ እንገኛለን ያለው መግለጫው፥ ይህም አገራዊ ጥቅማችንን ከማስጠበቅ አልፎ ቀጠናዊ ትስስር በመፍጠር ረገድ ያጋጠሙንን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመቅረፍ የህዝቦቻችንን የተከማመሩ ችግሮች ለመፍታት መንግሥት ሌት ተቀን እየተጋ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች ጊዜያዊ ግጭቶች ሲከሰቱ እየተስተዋለ ነው ብሏል። አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለዘመናት አብሮ በኖረው ህዝቦች መካከል ጥርጣሬን የሚፈጥሩ እና ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች መስተዋላቸውን አስታውቋል። የተፈጠረው ግጭት በምንም መስፈርት ህብረተሰቡን የማይወክልና የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ እንደሆነ ከወዲሁ መገንዘብ ይቻላል ነው ያለው። ስለሆነም መንግሥት በግጭቱ ምክንያት ለደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ፥ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል። በድርጊቱ የተሳተፉትን አካላት መርምሮ አስተማሪ እ...

Shira mufattootaa fashaleessuuf haatumsinu!

ምስል
Shira mufattootaa fashaleessuuf haatumsinu! Mufattoonni waan gochaaa jiran argaa jirra,dhaga’aa jira.Kanaan dura dhoksaadhaan waan barbaadan hunda gochaa turan amma ifatti ba’aniiru,kun waan gaariidha.Sochiin jijjiirama hawwataa mul’achaa jiru gufachiisuuf gargaaru sadarkaa guutuu biyyaatiin akka finiinuuf qaanii tokko malee ibsa baasuudhaan. waamicha dabarsaniiru. Miseensa Adda Demookraatawa Warraaqsa Ummata Itiyoophiyaa(ADWUI) kan ta’e Addi Bilisa Baasaa Ummata Tigraay(ABBUT) ibsi dheengadda baase mufattoonni dhaabbaticha keessatti argaman mari’achuudhaan jijjiirama hooggansa haaromsaatiin mul’achaa jiru karaatti hanbisuuf jecha kan baasan akka ta’e hubatamuu qaba. Shira mufattootaa kana dura dhaabbachuudhaan jijjiirama biyya keenyatti mul’achaa jiru mamii tokko malee itti fufsiisuuf qophaa’ummaa keenya mul’isuuf kutannoodhaan dhaabbachuun yeroonsaa ammadha. Miseensoonni hooggansaa Adda Bilisa Baasaa Ummata Tigraay(ABBUT) jijjiirama hooggansa Dh.D.U.Ofi dhaabbilee obbol...

Ibsa koree jiddu galeessa adda bilisa baasaa Ummata Tigraay irraa kenname

ምስል
Ibsa koree jiddu galeessa adda bilisa baasaa Ummata Tigraay irraa kenname 1.seensa Koreen jiddu galeessa adda bilisa baasaa Ummata Tigraay waxabajjii 3 hanga 5tti walga’ii hatattamaa adeemsisaa ture xumureera.ABBUT/ADWUI’n qabsoo hidhannoo waggaa 17s ta’e boqonnaa qabsoo misooma nagaafi demookraasii jaarraa nuusa lakkoofsiseen dhaabbilee obbolaa wajjin ta’uun qabsoo taasifneen injifannoowwan hedduu goonfachaa sadarkaa har’aa irraa ga’uu dandeenyee jirra.Maddi milkaa’ina Imala keenya obsaafi ijifannoo waggoota 43 toora qulqulluu warraaqaa qabachuun deemuu keenyadha.Abbaa dhaaba toora kana kutannoon qabatee qabsaa’uun qabseessisuu waan taaneefisi.Waggoota 27 darban walii galatti waggoota 17 ammoo haaromsa waliigalaatiin jijjiiramoota bu’uraa galmeessisuu dandeenyee jirra.Biyyi teenya Itiyoophiyaan imala gadi deemuufi bibittinnaa’uu heddu yaaddessaa ta’e keessaa baatee gara boqonna haarawaatti akka ceetuufi maqaafi kabajinishee akka waamamuuf ADWUI qabsoo obsa fixachiisaa adeemsi...

“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ምስል
“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ I. መግቢያ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3 እስከ 5 ያካሄደዉን አስቸኳይ ሰብሰባ አጠናቋል። ህወሓት / ኢህአዴግ በ 17 ዓመቱ የትጥቅ ትግልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባስቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፍን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ 43 ዓመታት የድልና የፅናት ጉዟችን ስኬት ምንጭ የጠራና ብቁ አብዮታዊ መስመር ይዘን የዘለቅን መሆኑ ነው። ይህንን መስመር በፅናት ጨብጦ በፅናት ታግሎ የሚያታግል ድርጅት ባለቤት ስለሆንም ነው። ባለፉት 27 ዓመታት በአጠቃላይ፣ ባለፉት የ 17 የተሐድሶ ዓመታት ደግሞ በተለይ ዙርያ መለስ መሰረታዊ ለውጥ ማስመዝገብ ችለናል። ሃገራችን ኢትዮዽያ የነበረችበት እጅግ አስፈሪ የመበታተንና የማሽቆልቆል ጉዞ ተገቶ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንድትሸጋገርና ስምና ክብር ከፍ ብሎ እንዲጠራ ኢህኣዲግ እልህ አስጨራሸ ትግል አካሂዷል። በተደረገዉ ትግል የሃገራችን ህዝቦች የመልማት እኩል ዕድል ያረጋገጠ ስርዓት ተገንብቶ ህዝቦችን በኢኮኖሚና በማሕበራዊ ረገድ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ዉጤት ለማረጋገጥ ተችሏል። በእርግጥም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ሃገራችንን ከጥፋት የታደገ፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠበት አዲሲቷ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ያደረገና ለወዲፊትም የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ ...