የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ አውጥቷል
በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ አውጥቷል።
የመንግስት መግለጫ በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እና አገራዊ ድባብ ጠብቆ ማስቀጠል የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆን አለበት ብሏል::
በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሰላምና መረጋጋት ብሎም እየታየ ያለው አገራዊ መግባባትና የህዝቦች አንድነት
የአገራችንን ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በአፍሪካ ደረጃ ብሎም በዓለም አቀፍ መድረኮች ውጤት እያስገኘ ያለ ስኬት
ነው ብሏል መግለጫው።
በዚህም ሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን የምንገኝበትን የአፍሪካ ቀንድ እና የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ ከመሰረቱ የሚለውጥ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናችን ይታወቃል።
በዚህም ዓለምን ያስደመመ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በማሰመዝገብ ላይ እንገኛለን ያለው መግለጫው፥ ይህም አገራዊ ጥቅማችንን ከማስጠበቅ አልፎ ቀጠናዊ ትስስር በመፍጠር ረገድ ያጋጠሙንን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመቅረፍ የህዝቦቻችንን የተከማመሩ ችግሮች ለመፍታት መንግሥት ሌት ተቀን እየተጋ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች ጊዜያዊ ግጭቶች ሲከሰቱ እየተስተዋለ ነው ብሏል።
አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለዘመናት አብሮ በኖረው ህዝቦች መካከል ጥርጣሬን የሚፈጥሩ እና ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች መስተዋላቸውን አስታውቋል።
የተፈጠረው ግጭት በምንም መስፈርት ህብረተሰቡን የማይወክልና የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ እንደሆነ ከወዲሁ መገንዘብ ይቻላል ነው ያለው።
ስለሆነም መንግሥት በግጭቱ ምክንያት ለደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ፥ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።
በድርጊቱ የተሳተፉትን አካላት መርምሮ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድም አረጋግጧል።
ይህን መሰል ጥፋትና ግጭት ያቀነባበሩት እና ሁከቱን ያባበሱት አካላት ዓላማ አሁን በአገራችን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ማወክ፣ መንግሥት እየገነባው ያለውን አገራዊ አንድነት መናድና በአጠቃላይ አገራችን የጀመረችውን ውጤታማና ፈጣን የሪፎርም እንቅስቃሴ ማደናቀፍ መሆኑ አያጠያይቅም ብሏል መንግስት በመግለጫው።
በመሆኑም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አምርሮ ሊታገለው የሚገባ አደገኛ አዝማሚያ እና ተግባር መሆኑን ተገንዝቦ በጽናት ሊታገልና ሰላሙን መጠበቅ ይገባዋል ብሏል።
በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በክፉውም ይሁን በደግ አብረው በኖሩ ህዝቦቻችን መካከል ግጭት ሊፈጠር አይችልም ያለው መግጫው፥ ይህ በረጅሙ የታሪክ ጉዟችን የተረጋገጠ ሃቅ ከመሆኑም ባሻገር የህዝቦች ፍላጎት ምንግዜም ሰላም፣ ልማትና ብልጽግና እንጅ ብጥብጥና ውድመትአይደለም።
በመንግሥት የለውጥ መሪነት ከቀውስ ለመውጣት የተጀመረው ጥረት እየሰመረ፣ ነፍጥ አንስተው ሲፋለሙ የነበሩ ወገኖቻችን ሳይቀሩ የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለአገር ግንባታ መሰለፍ በጀመሩበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት የግል ጥቅምን ታሳቢ አድርገው ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ሩጫ መግታት ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ወቅታዊ ተግባር ነው ብሏል።
በመሆኑም መላው ህዝባችን ለዘመናት ሲንከባከባቸው የኖሩትን የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመከባበርና የመረዳዳት እትዮጵያውያን እሴቶች በጥቂቶች ሴራ እንዳይሸረሸሩ ነቅተን እየጠበቅን በአገራችን ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ አንድነት፣ ልማትና ብልጽግና እንድሰፍንና የተጀመረው አገራዊ ትግል ለውጤት ይበቃ ዘንድ የጥፋት ሃይሎችን ዕኩይ ተግባር ነቅተን እናምክን የሚል ጥሪውን መንግስት በመግለጫው አስተላልፏል። #Ethiopia #Oromia
source:FBC(Fana Broadcasting Corporate)

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ