የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ አብይ አህመድ የመልካም ምኞት መግለጫ ኢድ ሙባረክ!!
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ አብይ አህመድ የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ።
የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ አብይ አህመድ ለኢድ አልፈጥር በአል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ
መልእክት ቅዱሱን የረመዳን ወር በተለመደው የመረዳዳት፣ የመጠያየቅ፣ የመደጋገፍ እና የመከባበር ስሜት አገባዳችሁ
እንኳን ለታላቁ የኢድ- አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ- አደረሰን፡፡
ኢድ ሙባረክ፡፡ ኢትየጵያውያን ሙስሊሞች 1.9 ቢሊዮን ከሚደርሱ የአለማችን ሙስሊም ወገኖቻችን ጋር በድምቀት የሚያከብሩት ይህ በአል በሀገራችን ኢትዮጵያ ሲከበር የሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያውያን ወደመሆን የፍቅር ሰገነት ከፍ ይላል፡፡
በኢትዮጵያችን በሙስሊሙ በአል ክርስቲያኑ፤ በክርስቲያኑ በአል ዋቄፈታው፤ በኢድ- በፋሲካው- በገና በእሬቻው የእንኳን አደረሰህ፣ እንኳን አደረሰሽ ቅብብሉ መልካም ምኞት እስከታከለበት ዝይይር በሚዘልቅ የፍቅር ሸማ ተከብክቦ ይሄው ዛሬ ደርሷል፡፡
ቅዱሱ የረመዳን ወር፣ የጾም፣ የጸሎት እና ከፈጣሪ ጋር የመገናኛ ልዩ ወር እንደመሆኑ መጠን፣ ኢድ አልፈጥርም፣ የፍቅር እና የበረከት፤ የይቅርታ እና የአብሮነት ድንቅ በአል ነው፡፡
ኢድ ሙባረክ! የኢድ አልፈጥር በአል የሚውለው፣ በሸዋል ወር የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡የሸዋል ወር ደግሞ፣ የታወቀ የበጎ ስራ እና የልገሳ ወር ነው፡፡
በፍቅሩና መተሳሰቡ ላይ በጎ ስራው ሲታከል፣ ጊዜው ይበልጥ የተባረከ ይሆናል፡፡
ለሙስሊም የሀገሬ ልጆችም ሆነ ለመላ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የምመኘውም ሙሉ ዘመናችን የሸዋል ወር እንዲሆንልን ነው፡፡
የአብሮነት እድሜያችን ሁሉ በሸዋል ወር በሚከቡን በረከቶች የተሞላ ከሆነ የዚህችን ሀገር ከፍታ የምናረጋግጥበት እና ወደ ታላቅነታችንም የምንመለስበት ጊዜ ፈታኝ ቢሆንም ቅርብ ነው፡፡
በተግባርም ወሩ ምድራችንን በሰማይ ጠል አረስርሶሰማያችንን በዳመና ጃኖ አልብሶ በሰላም ተሸኝቷል፡፡ መላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የረመዳን ወርን በሰላም አጠናቆ “ኢድ ሙባረክ…!” ከተባባለና የጾሙን ወቅት ከሸኘ በኋላ አፉን በማለዳ ምግብ አሟሽቶ አፍታም ሳይቆይ የከርሞውን ረመዳን መናፈቅ ይጀምራል፡፡
“የዘንድሮው አልቆብናል- ለመጪው ሰላም ያድርሰን…” እየተባባለ የሩቅ ተስፋን ይቀንናል፡፡
እንዲህ የሚያጓጉን፣ የምንሳሳላቸው፣ የምናከብራቸው፣ የምንወዳቸው እና መስከረም ጠብቶ አዲስ ወር በባተ ቁጥር “ሊመጡልን ነው…” በሚል ጉጉት በስስት የምንናፍቃቸው መንፈሳዊ እሴቶቻችን ሁሌም የደስታችን ምንጭ የሚሆኑት እና በአብሮነታችን ውስጥ እያደር የሚፈኩትበፍቅር የሚደምቁት ይህች ሀገር ሰላም ስትሆን ብቻ ነው፡፡
በመሆኑም መላ የሀገራችን ሙስሊሞች እና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንደሁልጊዜው ሁሉ በረመዳን ወር የነበሩንን የሰላም፣ የመረዳዳት፣ የመከባበር እና የመጠያየቅ
ባህል በማስቀጠል የሀገራችንን ሁለንተናዊ ለውጥ እና ህዳሴ ለማረጋገጥ የበኩላችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
በመጨረሻም በአሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ እና የአንድነት በአል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ፡፡
ኢድ ሙባረክ!!

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ