ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ለታላቁ የጨምበላላ በአል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ለታላቁ የጨምበላላ በአል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
እንኳን የሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ በአል ለሆነው ለታላቁ የጨምበላላ በአል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፤
አይዴጨምበላላ!!
የሰው ልጆች የስልጣኔ ልክ እና ያለፉበት የታላቅነት የዘመን መልክ የሚለካባቸው አበይት መመዘኛዎች ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህ አበይት የስልጣኔ እና የታላቅነት ማሳያ አብነቶች ውስጥ አንዱ፤ ምናልባትም ዋነኛው -የማህበረሰቡ የዘመን ቀመር እውቀት ነው፡፡
በዚህ ዋና መለኪያ ስንመዝነው ደግሞ የሲዳማ ህዝብ በጸሀይ በጨረቃ እና በከዋክብት ረቂቅ የተፈጥሮ ኡደት ውስጥ ያውን ጥልቅ የአጽናፈአለም (Universe) ሚስጥር በመመርመር ጊዜን እያሰላ ዘመንን የሚቆጥርበት ጥበብ እጅጉን የሚደንቅ እና ለሁላችንም ኩራት የሚሆን ነው፡፡
በሲዳማ የዘመን አቆጣጠር ጥበብ ውስጥ እስከ ማይክሮሰከንድ ሽርፍራፊ የጊዜ ቅንጣት ድረስ የሚወርድ ጊዜን መለኪያ ጥበብ የመኖሩ ነገር ሲታይ ደግሞ ኩራት ክብራችንን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡
በመሆኑም ይሄንን የሲዳማን ህዝብ የአዲስ አመት በአል እና የዘመኑን አዲስነት ለማወጅ ጊዜን የሚቆጥርበትን ግሩም እሴት መላው የደቡብ ክልል ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወገናችን ክብሩንም ሆነ በአሉን በፍቅር ይጋራዋል፡፡
ከዋዜማው የፍቼ ትእይንት እስከ ዋናው የጨምበላላ በአል ድረስ ያለው አስደማሚ የከበራ ሂደት እና በግርምት የሚመስጥ ውብ ስርአት የሲዳማ ህዝብ በዘመናት መሀል በሚደንቅ ጥበብ ከብክቦ ያቆየው በመሆኑ ለዚህ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር እና የአለም ህያው ሀብት ያለኝን ከፍ ያለ ክብር እና አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
በመጨረሻም ዘመኑ የሰላም፣ የይቅርታ ፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
አይዴጨምበላላ
መልካምበአል!!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa