የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ እሳቤዎችና አፈፃፀማቸው
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባውን ካካሄደ በኋላ በአበይት ጉዳዮች
ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። ከእነዚህም ውስጥ አንደኛው የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ
የአክስዮን ድርሻ እንዲኖራቸውና በመንግስት ይዞታ ሥር ያሉ ድርጅቶች (የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣
የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች) ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግሉ ዘርፍ
እንዲዘዋወሩ ያስተላለፈው ውሳኔ ይገኝበታል።
ይህን ውሳኔ ተከትሎ በአንድ በኩል በኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ካለመያዝ በሌላ በኩል ደግሞ የኮሚቴውን ውሳኔ በተዛባ እይታ ከመመልከት የሚነሱ አንዳንድ አሉታዊ አስተያየቶች ይሰማሉ። እነዚህ አስተያየቶች የአጠቃላይ ውሳኔውን አረዳድ የሚያዛቡና ትልቁን ምስል የሚከልሉን በመሆናቸው በውሳኔው ላይ የተቀመጡ ጉዳዮችን ደግሞ ማሳየትና ማብራሪያ መስጠት ተገቢ ይሆናል።
በመጀመሪያ ደረጃ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይህን መሰረታዊ የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዞር (privatization) ውሳኔ ሲያስቀምጥ መነሻ ያደረጋቸው ሶስት አበይት እሳቤዎች አሉ።
አንደኛው እሳቤ እስካሁን የመጣንበትን ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይበልጥ ማስፋትና ማጠናከር ነው። ይህ እድገትን የማስቀጠል እሳቤ የሚፈፀምበት አቅጣጫም ሀገራዊ የወጪ ንግድ አፈፃፀማችንን በላቀ ደረጃ በማሳደግ እንዲሆን አስምሮበታል።
በሁለተኛ ደረጃ ሀገራዊው እድገት ዜጎችን አካታች (inclusive growth) በሆነ መልኩ እንዲቀጥል የማድረግ ሁኔታ ነው። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባለሃብቶቻችን በየጊዜው
እያጎለበቱት የመጣውን የሃብትና የመፈፀም አቅማቸውን በተገቢው ሁኔታ አሟጠው መጠቀም የሚችሉበትን እድል የሚፈጥር ነው። በተመሳሳይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜያት በሀገራቸው ልማት ለመሰማራት ያላቸውን ምኞት ከያሉበት ያካበቱትን ሃብትና እውቀት አስተባብረው እውን የሚያደርጉበት ይሆናል።
በሶስተኛ ደረጃ መታየት ያለበት የሀገራዊ የልማት ድርጅቶቻችንን በምርታማነትና በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራታቸውና አቅማቸው ውጤታማ እንዲሆኑና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንደሆኑ የማድረግ ፋይዳው ነው። በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትም ሆነ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ መተላለፋቸው ይህን ለማሳካት የሚያስችል ሲሆን እውቀትና የውጭ ምንዛሪ ካፒታል ያላቸው የውጭ ባለሃብቶች ጭምር በዕድገታችን ላይ ተገቢውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል ነው። ከእነዚህ ተቋሞች የሚገኘውን ሃብት፣ እውቀትና ቴክኖሎጂ ወደ ሌሎች የኢኮኖሚውና አጠቃላይ የልማት ዘርፍ በማሸጋገር ሀገራዊ እድገታችንን ለማስቀጠል የሚያስችለን ነው።
ከኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዞር (privatization) ውሳኔ ጋር በተያያዘ ግልፅ ግንዛቤ ሊያዝበት የሚገባው ሌላው ጉዳይ የውሳኔው አፈፃፀም ነው። ስራ አስፈፃሚው እንዳስቀመጠው ውሳኔው የሚተገበረው የልማታዊ መንግስታችንን ባህሪያት በጠበቀ መልኩ ብቻ ይሆናል።
በፈጣን እድገት ውስጥ ከመግባታችን በፊት እንደ ሀገርም ሆነ በሀገራዊ ባለሃብቱ ደረጃ የነበረን አቅም እጅግ ዝቅተኛና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የማይችል እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑም ሀገራዊ አቅማችን እስከሚገነባ ድረስና የግል ባለሃብታችን አቅሙን አጠናክሮ እስከሚወጣ ድረስ በተመረጡ የገበያ ክፍተቶች ላይ መንግስት ጣልቃ በመግባት ለሀገራዊው ኢኮኖሚ መነቃቃትና ለባለሃብቱም አቅም መጎልበት ሚናውን ተጫውቷል። ሀገራዊ ባለሃብቱ ገና ጀማሪ በሆነበት ደረጃ ለውጭ ውድድር ቢጋለጥ ተሸንፎ ከውድድር መውጣቱ አይቀሬ በመሆኑም የተወሰኑ የኢኮኖሚ መስኮች ለሀገር ውስጥ ባለሃብቱ ብቻ ተገድበው እንዲቆዩም ተደርገዋል። የእነዚህ ድምር ውጤት አሁን ላይ ለደረስንበት የተሻለ ቁመና አብቅቶናል።
ልማታዊ መንግስት ይህን የእድገት አቅጣጫ የሚመለከተው እንደ አንድ የስትራቴጂ ማስፈፀሚያ ታክቲክ እንጂ በራሱ የማይቀየር ስትራቴጂ አድርጎ አይደለም። በሂደት የገበያ ክፍተቱ በግል ባለሃብቱ እየተሞላ ሲመጣና ሀገራዊ የውድድር አቅም ሲጎለብት የመንግስት እጅ የሚሰበሰብበት፣ በሌላ በኩል ወቅቱ በሚጠይቃቸው ሌሎች የኢንተርቬንሽን መስኮች ላይ ደግሞ የሚሰማራበት ታክቲክን ይዞ የሚቀጥል ይሆናል። ስለሆነም አሁን ላይ ሆነን ከደረስንበት የኢኮኖሚ ደረጃና ዜጎቻችን በሀገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ያፈሩትን ጥሪት ታሳቢ ያደረገ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረግ ተገቢ ነው። አሁን በሀገራችን የጀመርነው ይህ አካሄድ ከእኛ በፊትም በሌሎች የልማታዊ መንግስታት ተደጋግሞ የተስተዋለና ለስኬት ያበቃቸው ነው።
በመሆኑም የአሁኑ የስራ አስፈፃሚው ውሳኔ በአንዳንድ አስተያየቶች ላይ እንደምናየው የልማታዊ መንግስት ባህሪን የሚያስተው ሳይሆን የራሱ የልማታዊ መንግስቱ መሰረታዊ ባህሪዎችና ፍላጎቶች ተፈፃሚ የሚሆኑበት ነው። ይህም መንግስት አሁንም የገበያ ክፍተት ባለባቸው የተመረጡ ጉድለቶች ላይ የተቀናጀ ጣልቃ ገብነት (state intervention) ማድረጉን ይቀጥላል ማለት ነው። ለዚህም ሲባል የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ወደ ግሉ ዘርፍ በሚዘዋወሩበት ወቅት እንኳን መንግስት ትልቁን የአክስዮን ድርሻ ይዞ ይቀጥላል።
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔዎች የመጨረሻ መዳረሻ የኢትዮጵያን ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ማስቀጠልና የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ማረጋገጥ እንደመሆኑ መጠን የመንግስት ድርጅቶችንና ኩባንያዎችን ወደ ግል ይዞታ የማዞሩ ሂደት በጥናት ላይ በተመሰረተ፣ ግልፀኝነት በተሞላበት፣ በጥንቃቄና በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚፈፀም ይሆናል።
Source:EPRDF Official

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ