መዘግየት ከመቅረት ይሻላል!ለሚጠቁሙ ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ይከፈላል

 



እርምጃው እጅግ በጣም የዘገየ ቢሆንም በዋጋ ንረት ምክንያት በመሰቃየት ላይ ለሚገኙ ወገኖች ትን እፎይታ ሊፈጠር ይችላል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተለያያዩ ውሳኔዎችን ይፋ ዛሬ አድርጓል፡፡

የባንኩ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ጉዳዩን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ÷ 391 የሚደርሱ በህገወጥ የገንዘብ ማዘዋወር ወይም ሀዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው መዘጋቱን ተናግረዋል።

ተባባሪ የባንክ የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞችም እየተጣራ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ጠቅሰው፤ሕገወጦችን ለሚጠቁሙ የህብረተሰብ ክፍሎችም የዎሮታ ክፍያ መመሪያ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ጠቁመዋል

በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን የሚይዙትን ለጠቆሙ የተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣ የውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣ ሕገወጥ ሀዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ዎሮታ እንደሚከፈላቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የወርቅ ኮንትሮባንድ ለሚጠቁሙ 15 በመቶ የወርቁን ዋጋ፣ የሀሰተኛ ኖት ህትመት ለሚጠቁሙ 20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር እንደሚከፈልም ነው የተናገሩት።

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ እቃ የሚያስመጡ በውጭ ሀገር ያላቸውን የዶላር መጠን የሚያሳውቅ የባንክ ስቴትመንት ለብሄራዊ ባንክ የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋልም ነው የተባለው።

ይህም ከሀገር ውስጥ ጥቁር ገበያ የውጭ ሀገር ገንዘብ በመግዛት ከውጭ እቃ እያስገቡ መሆኑ በመታወቁ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የተወሰኑ ከውጭ በዶላር የሚገቡ የሸቀጥ አይነቶች ላይ ክልከላ ሊደረግ መሆኑን ዶክተር ይናገር ደሴ ገልጸዋል፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa