የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱት የ85 ዓመት አዛውንት




ዓላማዬ መማርና ለሀገር በእውቀቴ ውለታ መዋል ነው -12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱት የ85 ዓመት አዛውንት

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመውሰድ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ከትናንት ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እየገቡ ይገኛሉ።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም ከሀድያና ከወላይታ ዞኖች የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ የ12ኛ ተፈታኞች በመቀበል ላይ ነው።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ብሔራዊ ፈተናውን ከሚወስዱት ተፈታኞች መካከል ከወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የመጡት የ85 ዓመቱ አቶ ባፋ ባጋጃ ይገኙበታል።
የስምንት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ባፋ ኑሮ ባደረሳባቸው ጫና እና ልጆቻውን አስተምረው ቁም ነገር ለማድረስ ሲሉ በ1949 ዓ.ም የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይናገራሉ።
የ85 ዓመቱ አዛውንት በ2009 ዓ.ም ከ66 ዓመት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በድጋሚ በመጀመር በባይራ ኮይሻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
"እውቀት መቅሰም በእድሜ አይገደብም" የሚሉት አቶ ባፋ ያቋረጡትን ትምህርት ከአምስት ዓመት በፊት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
የጀግንነት መገለጫ የሆነው የአደንና ፈረስ ግልቢያ ልምድ አለኝ የሚሉት አዛውንቱ ዓላማዬ ግን መማርና ለአገር በእውቀቴ ውለታ መዋል ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በፈተና ወቅትም በግቢው የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማከናወን ዝግጁ ሆነን መጥተናል ያሉት አቶ ባፋ÷ ክልከላ የተደረገባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መረዳታቸውን አመልክተዋል።

@FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa