’ እያነቡ እስክስታ‘’
ጥላቻና እብሪት በመጨረሻ የት ሊያደረስ እንደሚችል በራያ ግንባር ዳግም ታይቷል፡፤ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሲሰኦል ቲኬት የቆረጠው ትህነግ በራያ ሜዳዎችና ተራራዎች እንደፌንጣ ተበትኗል፡፡በአካባቢው የሚገኙ ወዳጆቸ እንደነገሩኝ በእብሪተኛው ትህነግ ወራሪ ኃይል ላይ የደረሰው ሽንፈት ከባድ ነው፡፡ወዳጆቸ ከቆቦ እንደነገሩኝ ለትህነግ ወራሪና ዘራፊ ኃይል መፍረስና መፈርጠጥ ዋናው ምክንያት ቁልፍ አመራሩ አራዶም በተባለ ቦታ ተሰብስቦ እንዴት እንደገና ተደራጅቶ መዋጋት እንዳለበት ዕቅድ ለማውጣት በስብሰባ ላይ እንዳለ የሰማዩ ጌታ አየር ኃይላችን በድንገት ያወረደው ናዳ ነው፡፡በዚህ የአየር ኃይላችን (ድሮን) ጥቃት ቁልፍ የትህነግ የግንባሩ ወታደራዊ አመራሮች ከነግንኙነት መሳሪያቸው ተደምስሰዋል፡፡በዚህ ምክንያትም የትህነግ ወራሪ ኃይል አመራርና ግንኙነት ተበጣጠሰ ይላሉ ወዳጆቸ፡፡በጎብየ፣በተኩለሽ፣በጎላቦ፣በሮቢት፣በቆቦ፣በወርቄና በመሳሰሉት የውጊያ ግንባሮች በጥምር ኃይላችን ይቀጠቀጥ የነበረው የትህነግ ግሳንግስ አመራርና ግንኙነት አጥቶና አርስ በእርስ መረዳዳት አልችል ብሎ ፈረሰ፡፡ነፍሱን ለማዳንም ተበትኖ እሬሳውንና ቁስለኛውን አዝረክርኮ ወደ ትግራይ ፈረጠጠ፡፡እንደወዳጆች ገለጻ በራያ ሜዳዎችና ተራራዎች የተረፈረፈው የወራሪው ኃይል ሬሳ ብዛት ይዘገንናል፡፡ተስፋ ቆርጦ የተማረከውና እጁን ለጥምር ኃይላችን የሰጠው ቁጥርም ከፍተኛ ነው፡፡እጅግ አሳዛኙ ነገር ለጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትና ለኢትዮጵያ መፍረስ ሲል የትግራይን ወጣቶችና ህጻናት በማዕበል ለጦርነት እየማገደ የሚገኘው ትህነግ መግለጫ ነው፡፡የዚህ የውጭ ጠላት ቅጥረኛ ቡድን አፈ ሌባ ጌታቸው ረዳ ውሸትና እብሪት በማይታክተው አንደበቱ ‘’ከአማራ ክልል የወጣነው ጠላትን ደምስሰን በራሳችን ውሳኔ ነወ ‘’በማለት በትግራይ ልጆች ሬሳ ላይ እስክስታ እየወረደ ይገኛል-‘’እያነቡ እስክስታ ‘’!!ይህ የጌታቸው ረዳ ሀሰተኛ ወሬ ሳያዩ የሚያምኑትን የትህነግ ብጹአን የተሰበረ ሞራልና መንፈስ ለመጠገን የታሰበ ነው፡፡ትህነግን የሚያሳስበው የትግራይ ወጣቶች እልቂትና በራያ ግንባር የወደቀው ሬሳ ሳይሆን በውጭ ሆነው ከበሮ የሚደልቁለትና አስፋልት ላይ የሚንከባለሉለት ብጹአኖቹ ናቸው፡፡
የትህነግ ቀብር መቃረቡን በእርግጠኝነት የሚናገሩት ወዳጆቸ የሚያሳስባቸው ጉዳይ ግን አለ-በጦርነቱ የተጎዳው ህዝብ ጉዳይ፡፡እርግጥ ነው የራያዎችን ቁልፍ ከተማ ቆቦን ጨምሮ በትህነግ ወረራ ስር የነበሩ ሌሎች ከተማዎችና የገጠር አካባቢዎች በጀግናው የጥምር ኃይላችን ተጋድሎ ነጻ ወጥተዋል፡፡ተፈናቅሎ የነበረው ህዝብ ሳይቀር በፍጥነት ወደመኖሪያው በመመለስ የተረጋጋ ኑሮውን ለመጀመር እየጣረ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ በአካባቢዎቹ ላይ ወረራና ዝርፊያ ያካሄደው ትህነግ አሁንም የህዝቡን ህይወት የሚያከብድ የጭካኔ ጥፋት ፈጽሟል፡፡ቆቦን ከወልዲያና ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ጋር የሚያገናኘው ዋነኛ መንገድ የአላውሃ ድልድይ በተደጋጋሚ በመሰበሩ ትራንስፖርቱን አክብዶታል፡፡የስልክ፣የጤና፣የመብራት፣የውሃ፣የባንክ….አገልግሎቶች በመቋረጣቸው የህዝቡን መልሶ የመቋቋም ጥረት አክብዶታል፡፡እነዚህ መሰረታዊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ ይጀመሩ ዘንድም ትኩረት ያስፈልጋል፡፡በአጭሩ በትህነግ ወረራ ስር የነበሩ ከተማና ገጠሮች አስቸኳይ እርዳታና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ይህን ከባድ ሀላፊነት ደግሞ መንግስት ብቻውን ሊወጣው አይችልም፡፡በውስጥም በውጭም ያለው ኢትዮጵያዊ፣ባለሀብቶችና የበጎ አድራጎት/እርዳታ ድርጅቶች ሁሉ በትህነግ ጭካኔ ለተጎዳው ወገናቸው መድረስ አለባቸው ብለውኛል ወዳጆች፡፡በተደጋጋሚ የጨካኙ ትህነግ ወረራና ዝርፊያ ኑሮ ለከበደበት ወገናችን በአስቸኳይ እንድረስለት፡፡
(ለመረጃው -ለወዳጀ ኮማንደር ይበልጣል ባህሩና ሌሎች ጀግና ፋኖ ወንድሞች ምስጋና ይድረስልኝ)
በዓለምነው አበበ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ