ሃና ጎሜዝና ኢትዮጵያ

ወይዘሮ አና ጎሜዝ የ1997 ምርጫ ሂደትን በኢትዮጵያ ተገኝቶ የታዘበው የአውሮፓ ታዛቢ ቡድን መሪ ሆና ሰርታለች የወቅቱን ምርጫ ሂደት በተመለከተም የምርጫው አሸናፊ ተቃዋሚዎች ናቸው በሚል ሪፖርት ብታቀርብም ሪፖርቷን የአውሮፓ ህብረት አጣጥሎ ውድቅ አድርጎባታል

ወይዘሮዋ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በያዘችው ቂም እኝኝ እያለች ይኸው እስከ አሁን ጥርሷን እንደነከሰችብን አለች፤እረ ወይዘሮ ሃና እባክሽ ተይን እኛ ኢትዮጵያዊያን የሰው አንፈልግም የራሳችንንም አንሰጥም።
ነገርን ነገር ያነሳዋል አለ ያገሬ ሰው፤ የወቅቱ ምርጫ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ሴትዮዋን የተመለከተ አንድ ረዥም ፅሁፍ በኢንግሊዝኛ ቋንቋ አሳትመው ማውጣታቸውን አስታውሳለሁ፤ፅሁፉ የወይዘሮ አና ጎሜዝን መሰሪ አካሄድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሴትዮዋ ብርቱ የኢትዮጵያ ጠላት ሆና  ቁጭ አለች።
አሁን ባለው ሁኔታም ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነገር ከመስራት አርፋ እንደማትቀመጥ ተናግራለች መባሉን ሰምቼ ሳቄን ለቀቅሁት፤እውነት ከጣሪያ በላይ ነው የሳቅሁት።እና ይህቺ ሴት አዲሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዘመዴ ስለሆነ እንደምንም ብዬ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥል አደርጋለሁ አለች አሉ ወይ ሃና ጎሜዝ።
ወይዘሮ ሃና የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ አውሮፓ ጠርታ የምትወሰውሰው አንሶ አሁን ደግሞ በተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣን ልትመጣብን ነው ማለት ነው፤እረ ይህቺን ሴትዮ ምን እናድርጋት?


እኛ ኢትዮጵያዊያን መቼም ቢሆን እጅ አንሰጥም ወይዘሮ አና ጎሜዝ ይህን የምታውቅ አይመስለኝም።ስለዚህ እዚያ ብራስልስ የምትገኙ የእኛ ሰዎች በምታውቀው ቋንቋ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን አስረዷት እኛን ለቀቅ የራሷን ጠበቅ ታድርግ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa