ለራስ ብቻ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ወጥተን ኢትዮጵያን እንመልከት

አንዳንድ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የፖለቲካ ተንታኝ ነኝ ባይ ሰዎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች  አብዮታዊ ዴኖክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) በማካሄድ ላይ ያለውን ጥልቅ ተሃድሶ ለማጣጣልና ዋጋ ለማሳጣት ሲፍጨረጨሩ ይታያል፤እነዚህ ሰዎች በአንድ ወቅት በሰነቁት መልካም ተስፋ ወደ ፖለቲካው መንድር የገቡና ኢህአዴግን በምርጫ ለማሸነፍ ጥረት ያደረጉ፤ነገር ግን በውድድር ሂደት በደረሰባቸው ሽንፈት ጥጋቸውን ለመያዝ የተገደዱ የከሰሩ ፖለቲካኞች ናቸው።አቶ ገብሩ አስራትና አቶ ሙሼ ሰሙ፣ሁለቱ ሰዎች ሰሞኑን አዲስ አድማስ በተባለ የግል ጋዜጣ ላይ የወቅቱን ሁኔታ አስመልከተው የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ለማንበብ እድሉን አገኘሁና የሁለቱንም ሰዎች ሃሳብና አመለካከት በትኩረት ማየት ተገቢ እንደሆነ አሰብኩ
አቶ ገብሩ አስራት በአንድ ወቅት በኢህአዴግ ፖሊሲዎች ላይ ተመስርተው የትግራይን ክልል የመሩና በ1993 ክፍፍል ወቅት በተፈጠረው አንጃ ውስጥ ተቀላቅለው በተሸናፊው አንጃ ውስጥ ተካትተው ከተለዩ በኋላ አረና የተባለ ተቃዋሚ ፓርቲ የመሰረቱና እስከ አሁን ምንም ውጤት ማስመዝገብ ያልቻሉ ሰው ናቸው
አሁን የፖለቲካ ተንታኝ የተባሉት አቶ ሙሼ ሰሙ ደግሞ በአንድ ወቅት የአዴፓ ከፍተኛ አመራር የነበሩና በራሳቸው ፈቃድ ከፓርቲው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገው የነበሩ ናቸው
በዚህ ፅሁፌ በስም የጠቀሱኩዋቸውን ሰዎች ጨምሮ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙ የከሰሩ ፖለቲካኞች በጥልቅ ተሃድሶ ሂደት ላይ በማካሄድ ላይ ያሉትን ዘመቻ በቅደም ተከተል ለማጋለጥ እሞክራለሁ
“ኢህአዴግ በዚህች ሃገር ተቃዋሚ እንዳይኖር እያደረገ ነው፡፡ከራሱ የተለየ ሃሳብ፣ አቋምና አቅጣጫ ያለው ግለሰብ እንዲኖር አይፈልግም፡፡ጠላት ብሎ ነው የሚፈርጀው።ተቃዋሚዎች በዚህ አመለካከት ብዙ በደል ነው የደረሰባቸው”የህውሓት/ኢህአዴግ አንጋፋ ታጋይና አመራር የነበሩት አሁን የተቃዋሚው አረና ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ገብሩ አሥራት ናቸው እንዲህ ባዩ።

አቶ ገብሩ አስራት በዚህ አይነት ሁኔታ ኢህአዴግን የሚያማርሩትና በጥልቅ ተሃድሶ አገርን በማረጋጋት ወደ መደበኛ የልማትና እድገት እንቅስቃሴ ለመመለስ የተጀመረውን ጥረት ለማጣጣል የሚሞክሩት በኢህአዴግ የሚመራው ስርዓት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ነው በኢህአዴግ አመራር የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ባይኖር እንዲህ በነፃነት ለመናገር መብት እንደማይኖራቸው እንኳ መረዳት እንደማይችሉ የሚሰጧቸው አስተያየቶች ያመለክታሉ።አቶ ገብሩ አስራት በአንድ ወቅት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ አማካይነት በተሰጣቸው ሃላፊነት የትግራይን ክልል ለመምራት እድል ያገኙ ቢሆኑም በዲሪቶ አመለካከት ተተብትበው የቆዩ በመሆናቸው ምንም እኩይ አላማ ባለው የአንጃ ቡድን ውስጥ ለመቀላቀል በመገደድ ከኢህአዴግ መስመር ውጭ ሆነዋል።
አቶ ገብሩ”የኢህአዴግ ሰዎች የአፈፃፀም ችግር ስለሆነ በአፈፃፀም እንፈታለን የሚል እንጂ ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ ተገንዝበው ለመፍታት ዝግጁ የነበሩ አይመስለኝም”በማለት በልበ ሙሉነት በትምክህት ይናገራሉ የኢትዮጵያን ችግር ተገንዝቦ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት የሚችለው የኢህአዴግ ትክክለኛ መስመር እንጂ አረና እንዳልሆነ ይታወቃል “ከወደቁ ወዲያ መፍጨርጨር ለመላላጥ” እንዲሉ አቶ ገብሩም ግልፅ የፖለቲካ ክስረት ካጋጠመዎት በኋላ የኢህአዴግን ጥረት በማጣጣል ዋጋ ለማሳጣት መሯሯጥ እርስዎን በሕዝብ ዘንድ ትዝብት ወስጥ ከመክተት ውጭ ምንም ጥቅም እንደሌለው መረዳት አለመቻልዎ አስገራሚ ነው፤በዚህ ሁኔታ እርስዎ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ሆነው መስራትዎን ለመጠራጠር ተገድጃለሁ ምናልባት ከኋላ እየተነዱ ነበር።

የኢዴፓ የቀድሞ አመራርና በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ነኝ ባዩ አቶ ሙሼ ሰሙ ደግሞ እንዲህ ይላሉ።“መጀመሪያ ጥያቄ ያቀረበውን ማህበረሰብ ነበር ማወያየት የሚገባው።ጥያቄ ያቀረበውን ማህበረሰብ ትቶ፣ በራስ ጥያቄ መነሻነት መልስ ሰጥቶ ከወሰኑ በኋላ ህዝብ አወያያለሁ ማለት ፋይዳ ያለው አይመስለኝም”ሲሉ ኢህአዴግ በአባል ድርጅቶቹ ውስጥ በአመራርና አባላት ተሳትፎ ያጠናቀቀውን የጥልቅ ተሃድሶ ውይይት ወደ ሕዝብ እዳያወርድ ለመከላከል ይጥራሉ።የአቶ ሙሼ ሰሙ አስተያየት የተሃድሶ እንቅስቃሴን ለማደናቀፍ ታዋቂ ነን የሚሉ ግለሰቦችና የተደራጁ ቡድኖች የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ያሳያል።
ከአመታት በፊት ኢዴፓ ሶስተኛውን አማራጭ የሚከተል ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ነው በተባለበት ወቅት ከኢህአዴግ ጋር በመፎካከር ለኢትዮጵያ ድሞክራሲያዊ ስርኣት ማበብ የሚያግዝ መሆኑን በመረዳት ብዙዎች እንደመልካም ሁኔታ ወስደው ነበር፤ነገር ግን እርስዎ የድርጅተዎን ውስጠ ጉዳይ ያውቃሉና ነገሩ ከግብ መድረስ እንደማይችል በተገነዘቡበት ወቅት የግል ኑሮዬን በሚል ሰበብ በይፋ ከኢዴፓ መልቀቅዎን በመገናኛ ብዙሃን ማስነገርዎን አስታውሳለሁ፤አሁን ደግሞ የፖለቲካ ተንታኝ በሚል ካባ የኢህአዴግን ህጋዊና በሕዝቦች የተደገፈ እንቅስቃሴ ማጣጣል ተገቢ ሊሆን አይችልም፡፡
አቶ ሙሼ ሰሙ ኢህአዴግ የጀመረውን ዳግም ጥልቅ ተሃድሶ መሰረት በማድረግ ያካሄደው የአመራር ለውጥም ሊዋጥላቸው አልቻልም፤እንዲቀበሉትም አይጠበቅባቸውም ይሁንና ይህ ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው እንዲህ ሲሉ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ አቋማቸውን ይገልፃሉ“የአብዮታዊ ዲሞክራሲን ፖሊሲ የሚያስፈፅሙ ሰዎች ሲመጡ፣ በፖሊሲው አምነውና ተጠምቀው የመጡ ካልሆነ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲን ሊያስፈፅሙ አይችሉም።ስለዚህ ገለልተኛ ናቸው የሚለው አያስኬድም።ሰዎቹ በፖሊሲው አምነው ለማስፈፀም የመጡ እንደ መሆናቸው ስለ ገለልተኝነታቸው ማንሳት ተገቢ አይሆንም፡፡ከፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ በሆነ መልኩ የመወሰን አቅምም ሊኖራቸው አይችልም”፡፡አቶ ሙሼ እዚህ ላይ በጣም ትክክል ነዎት ይህን መገንዘብ መቻልዎ ራሱ ትልቅ ነገር ነው፤የፓርቲ ተጽዕኖ ምናምን ሲሉ ግን የተቀላቀለብዎት ይመስለኛል ኢህአዴግ አዳዲስ አመራሮችን ወደ ኃላፊነት  ሲያመጣ ከኢዴፓና አረና  ወይም ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ሰዎችን በመምረጥ ማምጣት እንደማይችል የፖለቲካ ተንታኝ ለሆኑት ለእርስዎ መንገር እንኳ አስፈላጊ አይሆንም፡፡
እንግዲህ በዚህ አይነት ሁኔታ ግለሰቦችም ሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ፕሮግራሞቻውን  የሚያሰራጩ ሬዲዮ ጣቢዎች በተለይ የአማርኛው ክፍል የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮና የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ዶቼ ቬሌ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ አገራዊ የተሃድሶ ሂደት ለማደናቀፍ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፤ይህ አካሄድ ለራስ ብቻ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከመሯሯጥ ውጭ ሌላ የተጨበጠ ፋይዳ ሊያስገኝ አይችልም፡፡ከግል ፍላጎት በመውጣት ኢትዮጵያን መመልከት ተገቢ ነው፡፡
በቪኦኤና ዶቼ ቬሌ ውስጥ መሽገው የሚገኙ ጋዜጠኛ ተብዬ የኢህአፓ ርዝራዦች እንኳ ቀደም ሲልም የለየለትና የተቀናጀ ዘመቻ በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ አውጀው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ መሆናቸው በይፋ ይታወቃል፡፡



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman