የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ ወሰደ
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ። በዚህ መሰረት የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ አባይ ወልዱ ከድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው ተነስተው በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ዝቅ ብለው እንዲያገለግሉ ወስኗል። በተጨማሪም የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ በየነ ምክሩም ወደ ድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ዝቅ ብለው እንዲሰሩ መወሰኑን ድርጅቱ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል። ከዚህ ባለፈም የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ከስራ አስፈጻሚ አባልነታቸው እና ማዕከላዊ ኮሚቴው ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑንም ገልጿል። ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም ለሌሎች ሁለት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። እርምጃው ማዕከላዊ ኮሚቴው ያካሄደውን ጥልቅ ግምገማ ተከትሎ የተወሰደ ነው። ማዕከላዊ ኮሚቴው ባለፈው ሳምነት ባወጣው መግለጫ በአመራር ስትራቴጂካዊ ፖለቲካዊ ሁነቶች፣ ሁለንተናዊ የልማታዊ ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥ እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ በጥልቅ በመገምገም ያሉትን መሰረታዊ ክፍተቶች በዝርዝር ማየቱን ገልፆ ነበር። በትግልና በመርህ የተመሰረተ አንድነት አለመኖር፣ በመጠቃቃትና መከላከል ዝምድና ላይ መመስረት፣ የፀረ ዴሞክራሲ ጥልቅ አስተሳሰብና ተግባራት መኖራቸውን መገምገሙንም በመግለጫው ማስታወቁ ይታወሳል። በተጨማሪም የወጣቱን ትውልድ እና የምሁሩን አቅም በመገንባት፣ በማሰለፍና ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ መሰረታዊ ጉድለቶች መኖራቸውን ገምግሞ ነበር። በክልሉም ትራንስፎርሜሽን ከማረጋገጥ አኳያ መሰረታዊ ስትራቴጂካዊ የአመራር