Naannoleen sadi birrii miliyoona 30 gumaachan

Naannoleen Itiyoophiyaa sadi lammiiwwan keenya Naannoo sumaalee irraa buqqaafamaniif birrii miliyoona 30 gumaachan.
Deeggarsa maallaqaa kana kan taasisan Naannoo Tigraay,Naannoo Amaaraafi Naannoo Ummattoota kibbaati
Ministir di'eetaan waajjira dhimmoota koomunikeeshinii Federaalaa Fireehiwoot Ayyaaleew akka himanitti naannoleen sadeen tokkoon tokkoonsaanii birrii kuma 10 kennan.
Kanneen lammiiwwan keenya haala suukaneessaadhaan buqqa'aniif birmatan hundaan galatoomaa jenna! 
Read more from Amharic version

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያ የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አያሌው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ የትግራይ፣ አማራና የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ድጋፍ አድርገዋል።
ክልሎቹ እያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ ድጋፉ በብሄራዊ አደጋና ስራ አመራር ኮሚሽን አማካኝነት ለተጎጂዎች እንደሚደርስም አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቃዮች መቋቋሚያ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለያየ መልኩ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቋቋምና ለማቃለል ክልሎች እርስ በእርስ የሚያደርጉት መደጋገፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።
ሁሉም የአገሪቷ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በግጭቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም እያከናወኑ ያሉትን ተግባርም አድንቀዋል።
መንግስት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ከአገር ሽማግሌዎች፣ ሃይማኖት አባቶችና የጎሳ መሪዎች ጋር በጋራ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
መንግስት ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችል መልኩ የሰላም ጉባዔዎችን እንደሚያካሄድ ጠቁመው፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለሰላም መስፈንና የተጀመረውን ልማት በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ርብርብ ማድረግ እንደሚገባው ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያውያን እንደቀደመው ሁሉ ለአካባቢ ሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

Maddi Tajaajila Oduu Itiyoophiyaa(ኢዜአ)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman