በሕዝቦች ትስስርና አንድነት እንደሰት!

የኦሮሞና አማራ ሕዝቦች ትስስርን ለማጠናከር በሁለቱ ክልሎች አመራሮች የአገር ሽማግሌዎች፤አባ ገዳዎች፤ምሁራንናና ታዋቂ ሰዎች የተሰራው ስራ እጅግ በጣም ውጤታማ ሆኗል ይህ አመርቂ ውጤት ብዙዎችን አስደስቶ ሲያስፈነድቅ ጥቂቶችን ግን አንገት አስደፍቶ በማስቆዘም ላይ ይገኛል፤በሰሞኑ የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦች ትስስርና አንድነት ማጠናከሪያ መድረክ አነማን ተደሰቱ? እነማንስ ተከፉ? በዝርዝር እንየው….

በዚህ የህዝቦች ትስስር ደስተኛ የሆኑቱ በዴሞክራሲያዊ አንድነት የሚያምኑ ኃይሎች ናቸው፤የዴሞክራሲያዊ አንድነት ደጋፊዎችም የደስታው ተካፋዮች ናቸው በሕዝቦች ትስስርና አንድነት እነርሱም ተጠቃሚ ስለሆኑ መደሰታው ምክንያታዊ ነው
የህዝቦችን ትስስር ለማጠናከር በማንኛውም አካል የሚከናወን ስራ ሊደገፍ እንጂ ሊኮነን አይገባም! እውነት ነው የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች ድንቅ ስራ ነው ያከናወኑት በዚህ ሊመሰገኑ ይገባል የህዝቦችን ትስስርና አንድነት ለማጠናከር በሃቅ የሰሩ ወገኖች ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፤ይህ የህዝቦች ትስስር ማጠናከሪያ ስራ ቀጣይነት ያለው መሆን አለበት  የኦሮሚያ ሕዝብ ወደፊት በተመሳሳይ ከትግራይ ከደቡብ ብሄር ቤሄረሰቦችና ከሌሎችም ክልሎች ሕዝቦች ጋር ያለውን ታሪካዊ ትስስር አጠናክሮ ይቀጥላል
በዚህ የሚከፉ ጥቂት ወገኖች ቢኖሩም የህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች መከናወን አለባቸው በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚመጣው የብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ክብረ በዓል ብቻ በቂ አይሆንም አይደለም፤ሕገ መንገስታችን የፀደቀበትን ወቅት ምክንያት በማድረግ ሕዳር 29 በየዓመቱ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንዳለ ሆኖ በፈጠራ ስራ የታገዙ ሌሎች የሕዝባዊ ትስስሮሽ ማጠናከሪያ መድረኮች በየወቅቱ ሊኖሩ ይገባል
ወደ ታካሪካዊው የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦች የትስስር መድረክ ልመለስና የኦሮሞና የአማራ ጭቁን ሕዝቦች ድሮም አንድ ናቸው አሁን አንድነታቸውን ነው ያጠናከሩት ባህር ዳር ላይ ተካሂዶ በተሳካ ሁኔታ በተጠናቀቀው የጋራ የምክክር መድረክ ላይ የተነሱ ርዕሰ ጉዳዮችም ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ሁነቶችን በመዳሰስ ይህን አረጋግጠዋል ክፍተቱን ፈጥረው የቆዩት የገዢው መደብ ተዋናዮች እንደሆኑ ግልፅ ነው
የቀድሞ ገዢ መደቦች ግራ ሲገባቸው ከፋፍለው ለመግዛት የተከተሉት አፍራሽ ስልት ብዙ ነገሮችን እንዳበላሸብን እናውቃለን፤አሁን እነርሱን አንወቅስም በወቅቱ በነበራቸው የዕውቀትና የግንዛቤ ደረጃ የሰሩትን ሰርተው አልፈዋል ለሰሩት መልካም ነገር ሁሉ እናመሰግናቸዋልን
ትኩረታችን በአሁኑና በወደፊቱ ላይ መሆን አለበት በአሁኑ ወቅትም ሕዝቦችን በመከፋፈልና ቁርሾ በመፍጠር ጥቅማቸውን ለማስከበር በመፍጨርጨር ላይ የሚገኙ ኃይሎች እዚህም እዚያም እንዳሉ ግልፅ ነው ትኩረቱ በሁለቱም ላይ መሆን አለበት ሁለቱም ጅቦች በአፈጠጠራቸው አንድ ናቸው
የውስጡ ጅብ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለችው እንስሳ አይነት ነው የውጭው ጅብ ደግሞ “ባልበላውም ልጫረው” እንዳለችው እንስሳ አይነት ስለመሆኑ ተግባሩ ነው የሚመሰክረው
ሁለቱም ጥገኞች የሕዝቦች የጋራ ጠላት ናቸው ለራሳቸው እንጂ ለሌላው ማሰብ አይችሉም ምክንያቱም ራስ ወዳድ ሆዳሞች ናቸውና፤እነዚህን አረመኔና ይሉኝታ ቢሶች በማሸነፍ ማጥፋት የሚቻለው አውነታውን አውቆ አንድነትን በማጠናከር ብቻ ነው!

የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦች ትስስር መድረክ እነዚህን ኪራይ ሰብሳቢና ጥገኛ ኃይሎች እንደዚሁም እነርሱ የዘረጓቸውን መረቦች አስቆዝሞ ቁጭት ወስጥ እንደከተተ ይታወቃል በቁዘማና ቁጭታቸው ተገፍተው የማይሞከረውን ሊሞክሩ ይችላሉ ነገር ግን አንድ ከሆነው ሕዝብ ጋር ሲነፃፀሩ ቁጥራቸው ጥቂት ስለሆነ ቢፍጨረጨሩም ምንም እንደማያመጡ ግልፅ ነው፤የኢትዮጵያ ሕዝቦች አንድነት ለዘላለም ይኑር!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman