የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) 7ኛ ደርጅታዊ ኮንፍራንስ ተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ

የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) 7ኛ ደርጅታዊ ኮንፍራንስ ተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ
የኦሮሞ ሕዝብ የዛሬው ዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ምንጭ ሆኖ የሚታየው የገዳ ስርዓት ባለቤትና በዚህም ራሱን ሲያስተዳድር የቆየ፤ይህንኑ ለአለም ያበረከተ ህዝብ ነው
ይህ ስርዓት በባህሪው አንድነትን የሚያውጅና አብሮ መኖርን የሚያጠናክር ነው ዛሬም ቢሆን የኦሮሞ ሕዝብ በዘመናዊ አስተዳደር ውስጥ  የራሱን መንግስት መስርቶ እየተመራበት በስርዓታችን ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች  የልማት፤የሰላምና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም የኦሮሞን ሕዝብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የአመለካከት አንድነት በመፍጠር የድህነትን ዕድሜ ለማሳጠር ጠንከረን በመስራት ላይ እንገኛለን
እኛ የኦህዴድ 7ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ከጥቅምት 19 እስከ ጥቅምት 23 በአዳማ ገልማ አባ ገዳ ስናካሂድ የቆየነውን ኮንፍራንስ በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቀናል
የጥልቅ ተሃድሶ አካል በየሆነው በዚህ ድርጅታዊ ሰባተኛ ኮንፍራንስ ላይ በተሃድሶ ንቅናቄ ውስጥ ለሕዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አፈፃፀሙን ገምግመን በቀጣዩ የትግል አቅጣጫ ላይ መግባባት ላይ ደርሰናል
የፖለቲካ፤የኢኮኖሚና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው ተስማምተናል
የፌዴራል ስርዓታችንን በማጠናከር ስራ ወስጥ ሕዝብና አመራሩ ሚናውን መወጣት ያለበት መሆኑ ወሳኝ እንደሆነ፤በሕገ መንግስቱ ላይ የተረጋገጡ መብቶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ እንዲሆኑ የድርጅቱ አባላትና አመራሮች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው፤በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ብጥብጥ በሰው ሕይወት በአካልና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ሃዘን የተሰማን ሲሆን የዚህ ችግር ምንጭ የሕዝባችን ፍላጎት እንዳልሆነ ተረድተናል
የተከሰተው ችግር ዳግም እንዳይፈጠር የክልላችንን ሰላም በክልላችን ሕዝብና በፀጥታ ሃይል ቅንጅት አስተማማኝ እንዲሆን ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ከስምምነት ላይ ደርሰናል
በአጠቃላይ በጥልቅ ተሃድሶ ለተለዩ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ድርጅትና መንግስት በማድርግ ላይ ከሚገኙት ጥረት ጎን ለጎን ሕዝባችን የመፍትሄው ዋነኛና ወሳኝ አካል ሆኖ መቀጠል እንዳለበት ከመግባባት ላይ መድረስ ችለናል
ስለዚህ ሰፊ ውይይት ስናካሂድ ከቆየን በኋላ  እኛ የ7ኛ ድርጅታዊ ኮንፍራንስ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ የተቀመጠውን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል

1.እስከ አሁን በተሃድሶ ንቅናቄ የተመዘገቡ ድሎችን መንከባከብና ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ማሸጋገር ወሳኝ ነው በዚሁ መሰረት በኦሮሞ ህዝብ ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን አንድነት በማጠናከር እየታየ ያለውን መተማመንና መደማመጥ እንደ ዕድል በመጠቀም ሕዝብ ከላይ እስከ ታች ባለው የተሃድሶ አመራር ላይ  መጣል የጀመረውን ተስፋ በማጠናከር የኦሮሞን ሕዝብ ወደ አንፀባራቂ ድል ለማሸጋገር እንታገላለን
2.በፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብና ድርጅታችን ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ይታወቃል፤የሕዝባችንን ጥቅሞች ለማስከበር ከፌዴራል ስርዓቱ ውጭ ሌላ ዕድል እንደሌለ በመገንዘብ በፌዴራል ስርዓቱ ወስጥ ያጋጠሙ ችግሮችና ክፍተቶችን በከፍተኛ ትዕግስትና የኃላፊነት ስሜት እየፈታን የኢትዮጵያን አንድነት በማጠናከር ሕገ መንግስቱ ለሕዝባችን ያረጋገጠው መብት ሳይሸራረፍ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ጠንክረን እንታላለን
3.በጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ወስጥ የለየናቸውን ችግሮች በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ የሕዝባችንን እርካታ ለማረጋገጥ ውስጠ ድርጅትን በማጠናከርና የወደፊቱን አመራር በመፍጠር የድርጅት ስራን አመለካከትን መቀየር በሚያስችልና ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ በመምራት የተጀመረውን ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እናሸጋግራለን
4.የሕዝባችንን የኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመርነውን  የኢኮኖሚ አብዮት ንቅናቄ በማጠናከር ከድህነትና እርዛት የወጣ ህብረተሰብ ለመፍጠር የተጀመረውን ትግል አጠናክረን እናስቀጥላለን
5.ሕዝባችን ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር ተያይዞ በማንሳት ላይ ያለውን ቅሬታ ሕዝቡን የመፍትሄው አካል በማድረግ የተጀመሩ ሪፎርሞች በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆኑ ግንባር ቀደም ድርሻችንን እንወጣለን
6.በኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ድርጊት ላይ የተጀመረውን ትግል ሕዝባችንን በተሟላ ሁኔታ በማሳተፍ ወደ ኋላ በማይመለስ የትግል ምዕራፍ ላይ በማድረስ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካ ኢኮኖሚን በማፍረስ ሕዝቡ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንታገላለን
7.የክልላችንን ሕዝብ ሰላም ለማደፍረስ ኪራይ ሰብሳቢዎች ዝርፊያን ለማስቀጠል ሲሉ የሚሸርቡትን ሴራ ሕዝባችንን በመነካካት በሰው ሕይወት በአካልና በንብረት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲቆም፤ በክልላችን ውስጥ የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች ያለምንም ስጋት ሰርተው እንዲኖሩ የትግላችን ጉልበት ሆነው እንዲቀጥሉ ጠንክረን እንታገላለን
8.ድርጅታችን ከደረሰበት የትግል ደረጃ ጋር እንዲመጥን ሆኖ የተዘጋጀው የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በድርጅታችን አባላት ሙሉ ተሳትፎ በማዳበር ተራማጅና አሸናፊ አመለካከት ይዘን ድርጅትና ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችንን በዘመናዊ መንገድ በመገንባት የኦሮሞ ሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ጠንክረን እንሰራለን
9.ትምህርት የሁሉም ነገር ቁልና ዋናኛ የለውጥ መሳሪያ ነው ለዚህም የኦሮሞ ሕዝብ ባለው የትምህርት ጥማት በድንቁርና ላይ ባለው ጥላቻ መራራ ትግል በማካሄድ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል ስለዚህ የዛሬው ትውልድ ለአንድ ሰከንድም ቢሆን ከትምህርቱ ሳይዘናጋ ተምሮ የወደፊቱ የኦሮሞ ሕዝብ ጥቅምና ፍላጎት ከግቡ እንዲደርስ የኦሮሞ ልጆች ከትምህርታቸው እንዲዘናጉ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንቃወማለን
10.ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድንበር ጥያቄን ተገን ያደረገው የኮንትሮባንዲስቶች ሴራ አብሮ ሲኖር በነበረውና በመኖር ላይ በሚገኘው ሕዝብ መካከል ችግር እንዲፈጠር በማድረግ ላይ ይገኛል፤በድንበር ሽፋን ለመነገድ የሞከሩ ኃይሎች የአገሪቱ ዜጎች የሆኑ በኢትዮጵያ ሱማሌ የሚኖሩ  በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆችን አፈናቅለዋል ስለዚህ የኦህዴድ 7ኛ ድርጅታዊ ኮንፍራንስ ታሳታፊዎች የሕግ የበላይነት እንዲከበር የዜጎቻችን ህይወት እንዲጠፋና ከንብረትና ቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ ያደረጉ ኃይሎች ለሕግ እንዲቀርቡና ከሁሉም በላይ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠው ዜጎች ከቦታ ወደ ቦታ ተዘዋውረው እንዲሰሩና አንዲኖሩ የተደነገገው ያለምንም ድንበርና እንቅፋት እንዲተገበር እንታገላለን
ጥቅምት 23/2010

ገልማ አባ ገዳ አዳማ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman