በኢዴፓ አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል

በኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል።
ሁለት የፓርቲው ነባር አመራሮች በየራሳቸው ወገን የፓርቲ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ገልጸዋል።
የፓርቲው ዋና ጸሃፊ አቶ ሳህሉ ባዬ የቀድሞው የድርጅቱ ሊቀ መንበር በመርህ ጥሰት ምክንያት ከስራ መነሳታቸውን ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ተናግረዋል።


ፓርቲው ለበርካታ ዓመታት በሊቀ መንበርነት የመሩት ዶክተር ጫኔ ከበደን በመርህ ጥሰት ምክንያት ከሀላፊነት መነሳታቸውን የፓርቲው ዋና ጸሃፊ አቶ ሳህሉ ባዬ ገልፀዋል።
ዶክተር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው “የፓርቲው ሊቀ መንበር እኔ ነኝ፤ እኔን ያወረደ ስራ አስፈፃሚም ሆነ ጠቅላላ ጉባኤም የተካሄደ የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የፓርቲው ብሄራዊ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ዶክተር ጫኔ ከበደን በማንሳት፥ አቶ አዳነ ታደሰን መሾሙንም ነው አቶ ሳህሉ ባዬ ሲሉ ተናግረዋል።
ከስልጣን ተነስተዋል የተባሉት ዶክተር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፥ እርሳቸው የሚመሩት የኢዴፓ ፓርቲ አሁንም እንዳለ ገልጸዋል።
የተደረገው ነገርም ህገ ወጥ ነው አሁንም የፓርቲው ሊቀ መንበር እኔ ነኝም ብለዋል።
እርሳቸው አቶ ሳህሉ ዋና ጸሃፊነታቸውን ተጠቅመው ህገ ወጥ ድርጊት ፈጽመዋል ያሉ ሲሆን፥ ጉዳዩ በፍርድ እየታየ መሆኑን ነው የጠቀሱት።
በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ብሄራዊ ምክር ቤቱ ከጠቅላላ ጉባኤው የፓርቲውን ስራ አስፈፃሚ የመሾም እና የመሻር ስልጣን ተሰጥቶታል።
ይህን ስልጣኑን ተጠቅሞም ከምክር ቤቱ አባላት መካከል 18 አባላት በተገኙበት ጉባኤ በማካሄድ፥ ዶክተር ጫኔ ከበደ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን አቶ ሳህሉ ባዬ ገልፀዋል።
ከጠቅላላ ስራ አስፈፃሚ መካከል ሶስቱ ከሃላፊነታቸው ተነስተው ወደ ብሄራዊ ምክር ቤት መምጣታቸው እንዲሁም ዶክተር ጫኔ ከበደ ከፕሬዚደንታቸው ተነስተው ወደ ስራ አስፈፃሚነት መምጣታቸውን ነው አቶ ሳህሉ የገለፁት።
ጣቢያችን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጠን ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
Source:FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman