ልጥፎች

ከሴፕቴምበር, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የመገለባበጥ አጀንዳ ግብ

አሁን ያለው ለውጥ የተገኘው በምንም ሳይሆን በትግል ነው፤የትግሉ ተዋናዮች ደግሞ ብዙ ናቸው ከውስጥም ከውጭም ያሉ የትግሉ ተሳታፊዎች አሁን በተጨባጭ ለሚታየው ለውጥ የማይናቅ አስተዋፅኦ አበርከተዋል።የመራራው ትግል ተሳታፊዎች በርካታ ስለሆኑ ለውጡን ያመጣሁት እኔ ነኝ የሚለው አካሄድ በምንም አይነት ምክንያት ተቀባይነት የለውም።ሁሉም እንደ አቅሙ ለለውጡ መገኘት የበኩሉን ሚና ስለተጫወተ ለውጡ በሁላችን ጥረት የመጣ ነው ብሎ ማመን ተገቢ ነው። ከለውጡ መገኘት በኋላ የመጣው ሂደት ይታወቃል፤አንዳንድ ኃይሎች ለውጡን የሚደግፉ መስለቀው በመቅረብ ህዝባዊውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚችሉትን ሁሉ ማድረጋቸው በተጨባጭ ታይቷል፤ነገር ግን ሙከራው ሁሉ ሳይሳካ ቀርቷል። የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች ዘርፈው   ባካበቱት የገንዘብ ኃይል ቅጥረኞችን በማሰማራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ ባለፈው ሰኔ ወር የግድያ ሙከራ ከማድረግ ጀምሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር በፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች ለማጣጣል ሰፊ ጥረት አድርገዋል፤ጥረታቸው ከንቱ ሆኖ ቢቀርም አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ። በለመዱት የማሸበር ልምድ ተጠቅመው ህብረተሰቡ አዲሱን አመራር አንዲጠራጠር፤እንዳይደግፍ፤እዲሱ አመራር ዳግም አንዳይመረጥ አጀንዳዎችን በመቀያየር አሁንም በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ፤ዋነኛው የመገለባበጥ አጀንዳው ግብ ይህ ነው። አዲሱ አመራር ህዝብ ታፍኖ ለአመታት የቆ በመሆኑ በዴሞክራሲያዊ አካሄዶች ፈታ ይበል ብሎ ሆደ ሰፊ ሲሆን ምቹ ሁኔታውን በመጠቀም በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም አንዲደፈርስ፤የሰዎች ሕይወት እንዲጠፋና ንብረት አንዲወድም አድርገዋል።የለውጡ አደናቃፊዎች መክረውና አሰልጥነው ያሰማሯቸው ሰዎች ለፖሊስ በሰጡት ቃል በገንዘብ ተቀጥረው የተሰማሩ መሆና...

‹‹ለረዥም ጊዜ አልመንና አስበን የጀመርነው ትግል በትንንሽ ሙከራዎች እንደማይደናቀፍ በጉባዔያችን ተረጋግጧል››

ምስል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የኦዴፓ ሊቀመንበር ከመስከረም 8 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በጅማ ከተማ ዘጠነኛው ጉባዔውን ያደረገው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በመሸጋገር፣ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ በኦዴፓ ጉባዔ ማጠናቀቂያ ላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት ያስተላለፉት የኦዴፓ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የፓርቲው ጉባዔ ለረዥም ጊዜ ታስቦበትና ታልሞበት የተጀመረው ትግል በትንንሽ ሙከራዎች እንደማይደናቀፍ ማረጋገጡን አስታውቀዋል፡፡   የድርጅቱ ሊቀመንበር ባስተላለፉት መልዕክት፣ ‹‹የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ድርጅታችን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ስሙን፣ ዓርማውን፣ ሕገ ደንቡን፣ አመራሩን፣ አመለካከቱንና አደረጃጀቱን 21ኛው ክፍለ ዘመን የሚጠይቀውን አመራር ለመስጠት በሚያስችለው ደረጃ ላለፉት አራት ቀናት በውቢቷ ከተማ ጅማ ያደረገው ዘጠነኛው ጉባዔ በድል ተጠናቋል፤›› ብለዋል፡፡ ድርጅቱ ስሙንና ዓርማውን ቀይሮ ብቻ ከዚህ ጉባዔ የሚወጣ የመሰላቸው በርካታ ሰዎች ቢኖሩም፣ በሚያስደንቅ ሁኔታ ላለፉት ሦስት ዓመታት የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ከነበሩ 81 ሰዎች መካከል አዲሱን አመራር እንዲቀላቀሉ ጉባዔው የጠቆማቸው 19 አባላት ብቻ እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለአዲሱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለማለፍ የቻሉት 16 ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ድርጅቱ የተማሩ፣ ለመምራት የተዘጋጁና ብቃት ያላቸው ወጣቶች ወደፊት በማምጣት ስያሜውን ብቻ ሳይሆን፣ የአመራር ብቃቱን ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለመውሰድ በሚያስችል ቁመና ራሱን ያዘጋጀና ያደራጀ በመሆኑ፣ ሌሎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታ...

Ibsa Ijjannoo Yaa’ii dhaabbatummaa ODP

ምስል
Ibsa Ijjannoo Yaa’ii dhaabbatummaa ODP Hirmaattota Yaa’ii dhaabbatummaa 9ffaan qophaa’e ---- Barri isaa fagoodha yaadannoon isaa ammoo dhiyoodha DhDUO kaleessaa, ODP hardhaa imala waggoota darbanii keessatti daandiin irra darbe kan injifannoon baayyeen itti galmaawan tahullee gufuuwwan isa mudataniis salphaa miti. Yaa ta’u malee duudhaan dhaloota isaarraa qabee Oromummaan dagaagfataatiifii qajeeltoo jireenya isaa godhachaa dhufe kufanii ka’uuf halaalatti quba qabuun dura quba ofitti qabanii of dhaggeeffatanii ofitti deebi’uun of ceepheessaa of haaroomsaa deemuudha. Seenaa kufanii ka’uutiif kan akka dubbii hanqaaquu yookiin killee caphaan alaa dhuftu du’a, caphaan keessaa futtaatu lubbuu akka taatee rakkoofii gaaga’ama hamaa hamma Ummanni Qabsoofnuuf duugda nutti gara galuu gahee turee yaadannoo yeroo dhiyooti. Paartiin keenya Qabsoo keessoo isaatti karaarraa maqnee karatti yaa deebinuu taasiseen bu’aan harra naannoo keenya bira dabree biyyaaf ifuu ...

በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ሳምንት ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል- ፖሊስ

ምስል
በአዲስ አበባ ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በመዲናዋ ባንዲራ ከመስቀል እንዲሁም ከሌሎች ህገ ወጥ ተግባራት ጋር ተያይዘው በተነሱ ግጭቶች የሰው ህይወት ማለፉን ተናግረዋል። ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ፥ በከተማዋ ከመስከረም 5 በፊት ማንኛውንም አይነት የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ አልተሰጠም፤ ሆኖም ግን ሁከት እስካልተፈጠረ ድረስ ማንኛውም ሰው ባንዲራ ሲሰቅል ነበር፤ የፀጥታ ሀይሉም ይህንን በንቃት ሲከታተል ነበር ብለዋል። ሆኖም ግን ባንዲራ ከመስቀልና የመንገድ ጠርዞችን ቀለም ከመቀባት ጋር ተያይዞ የመፍቀድና የመከልከል ስራው የፖሊስ ሆኖ ሳለ፤ ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት ከየመንደሩ በመውጣት ስርዓት አልበኝነት በሰፈነበት መንገድ ለማስቆም ሲሉ ግርግር ተፈጥሯል ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከመስከረም 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 7 2011 ዓ.ም በከተማዋ ሁከት እና ግርግር ተፈጥሯል ብለዋል ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ። ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ግርግርም በኮልፌ ክፍለ ከተማ የ14፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 5፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 3፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 5 በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል። ከእነዚህም ውስጥ የአብዛኛዎቹ ህይወት ያለፈው በድብደባ፣ በድንጋይ እና በዱላ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የሰባት ሰዎች ህይወት ደግሞ በፀጥታ ሀይሉ ነው ብለዋል። በፀጥታ ሀይሉ ህይወታቸው ካለፈው ውስጥ አንድ ሰው በፖሊስ ስህተት ነው ህይወቱ ያለፈው ያሉ ሲሆን፥ ይህን የፈፀመው ፖሊስም በ...

ኢንጂነር ስመኘው ራሳቸውን እንዳጠፉ የምርመራ ውጤቱ እንደሚያመላክት ፖሊስ ገለፀ

ምስል
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በሰው በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው እንዳላለፈና ራሳቸውን እንዳጠፉ የምርመራ ውጤቱ እንደሚያመላክት ፖሊስ ገለፀ። ፖሊስ የኢንጂነር ስመኘውን አሟሟት በተመለከተ በሰጠው መግለጫ፥ ኢንጅነር ስመኘው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የተደረገው የምርመራ ውጤት ያመላክታል ብሏል። ፖሊስ በመግለጫው ሞተው የተገኙበት መኪና ውስጥ የተገኘው ሽጉጥም በእርሳቸው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል። በፎረንሲክ ምርመራ በተገኘው ውጤት መሰረትም የሽጉጡ ቀልሃና የተገኘው እርሳስም የዚሁ ሽጉጥ መሆኑን ፖሊስ እንዳረጋገጠ አስታውቋል። ኢንጅነሩ ከመሞታቸው ቀደም ብሎ ባለው ቀን ባደረጉት የስልክ ልውውጥ፥ በአብዛኛው የስንብት ይዘት ያለው መልዕክትን ከልጃቸውና ፀሃፊያቸው ጋር ተለዋውጠዋልም ነው ያለው ፖሊስ። ከዚህ ጋር ተያይዞም ለፀሃፊያቸው ልጀን አደራ የሚል መልክዕክት ማስተላለፋቸውን የፌደራል ፖሊስ ጀኔራል ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ተናግረዋል። በሞቱበት ዕለት ማለዳ ላይም ለአንደኛው ሾፌራቸው ፖስታ በመስጠት ለማን እንደሚያደርስላቸው እነግርሃለው ማለታቸውን እና ለሌላኛው ሾፌር ደግሞ ፖስታ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዲያደርስላቸው መስጠታቸውም በመግለጫው ተነስቷል። በዕለቱ ማለዳ 2 ሰዓት ከ30 ላይ ለፖሊስ የኢንጅነሩ መሞት መረጃ ደርሶት ከ10 ደቂቃ በኋላ በስፍራው ደርሷል። በወቅቱም ፖሊስ ስፍራው ሲደርስ መኪናው ሞተሩ እንዳልጠፋና አራት በሮቹ ተቆልፈው ማግኘቱን አስታውቋል። ኢንጅነሩ በህይዎት መኖር አለመኖራቸውን ለማረጋገጥም የእጅ ጓንት በመጠቀምና የመኪናውን መስታዎት በመስበር በሩን መክፈት ተችሏልም ነው ያለው። መኪናው ከተከፈተ በኋላም ኢንጅነር ስመኘው ጥይቱ በቀኝ ጆሮ ግንዳቸው ገብቶ በግራ በኩል እንደወጣ ...

Yaada Moo’ataa Injifannoo Caalmaaf!

Yaa’ii Dhaabbatummaa 9ffaa Dh.D.U.O. geggeeffamuuf guyyaan dhihaachaa jira. Yaa’iin kun yaa’iwwan kana dura geggeef famaniin adda akka ta’e hubachuun barbaachisaadha. Murtoowwan sadarkaa qabsoon Oromoo yeroo ammaa irra gahee kan itti darbanii fi jijjiirama dhufaa jiruuf kallattii ce’umsaa kan kaa’udha jedhamee eegama. Yaa’iin kun ergaa ijoo” YAADA MOO’ATAA INJIFANNOO CAALMAAF” jedhuun Magaalaa Jimmaatti geggeeffama.  Yeroo ammaa Yaa’ii kana dura haala dureewwan yaa’ichaaf bu’uura ta’an raawwatamaa jiru. Mariin sadarkaa sadarkaan geggeeffamaa jira. Namoonni yaa’icharratti hirmaatan iftoominaa fi qulqullinaan filatamu. Namoonni yaa’ii kanarratti filatamuu qaban kanneen jijjiirama haaraa waliin tarkaanfachuu danda’aniifi qabsoo Oromoo sadarkaa olaanaatti ceesisuuf humna, beekumsaa fi dandeettii qabanidha. Filatamtoonni yaa’icharratti hirmaachuu qaban lagummaan, firoomaan, loogummaa fi hojimaata badaa kkfn filataman akka hintaane ofeeggannoo cimaa gochuu gaafata. Kun akka ta'uuf...

በኢኮኖሚ ፖሊሲው ላይ ማሻሻያዎች ሊደረጉ ነው

ምስል
የኢኮኖሚ ባለሙያዎችና ነጋዴዎች ቅሬታና ወቀሳቸውን አሰምተዋል ማክሮ ኢኮኖሚውን የሚያጠና ገለልተኛ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ተጠይቋል መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለማድረግ የፖሊሲ ሐሳቦችን የሚያመላክቱ ጥናቶች ማካሄድ እንደጀመረ በማስታወቅ፣ በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ከሚታዩ መሠረታዊ ችግሮች ውስጥ የአገሪቱ ተወዳዳሪነት ዋናው ችግር እንደሆነ ያመላከተ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ ነጋዴዎችና ባለሙያዎች ከፋይናንስ ዘርፉ እስከ ወጪ ንግዱ ባሉት መስኮች ላይ ቅሬታና ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡  የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን፣ ‹‹የኢትዮጵያ የልማት ግቦችና የመዋቅራዊ ሽግግር ፍላጎቶች የአጭርና የረዥም ጊዜ ተግዳሮቶችና ዕድሎች›› በሚል ርዕስ ማክሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው የመጀመርያው የከፍተኛ ኃላፊዎች የኢኮኖሚ ፎረም ላይ፣ የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ የመነሻ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ባመላከተው ጽሑፍ፣ የአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ እ.ኤ.አ. ከ2017 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን አቋም የሚተነብይና፣ ለኢኮኖሚው መፍትሔ ይሆናሉ ያሏቸውን መላምቶችን ያካተተ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያው ዮሐንስ (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ ባለፉት ሁለት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ምዕራፎች ውስጥ ለውጥ እያስመዘገበ የመጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንትና በቁጠባ መካከል እየሰፋ የመጣ ልዩነት ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡ ይህም ሆኖ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገበው የተወዳዳሪነት ችግር ዕድገቱን እየጎተተው መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ ለአብነትም የቻይና፣ የማሌዥያ፣ የታይላንድ፣ የደቡብ ኮሪያና የሌሎች አገሮችን...

Injifannoo naannawa gaanfa Afrikaa!

ምስል
Hooggantoonni Itiyoophiyaa Eertiraafi Soomaaliyaa dhimmoolee gara garaa irratti waliin hojjechuuf waliigalaniiru.Kun injifannoo guddaadha.Waan darbe hunda xinxallee yoo ilaalle waliigalteen hooggantoonni biyyaalee sadeenii Asmaraa Eertiraatti mallatteessan kun injifannoo ol’aanaadha. Waliigalteen hooggantoonni sadeen waliif mallatteessan tumsa naannichaa finiinsuuf shoora ol’aanaa gumaacha.Biyyaaleen sadeen waliigalteen mallatteessan kanaan Nagaafi tasgabbii naannichaa amansiisaa taasisuuf kan gargaarudha.Kana malees dhimmoolee hawaas-diinagdee ummattoota biyyaalee sadeenii misoomsuuf dagaasuuf itti fayyadamuuf balbala bal’aa bana. Ministirri muummichi keenya Dr.Abiy Ahmad,pireezidaantiin Eertiraa Isaayyaas Afawarqiifi pireezidaantiin Soomaaliyaa Mohaammad Abdullaahii(Foormaajoon) haala kanaan waliigaluu danda’uun isaanii naannichaaf hiika guddaa akka qabu hubachuun barbaachisaadha.Waliigalteen kun guddina diinagdee biyyaalee sadeenii gara fuulduraatti tarkanafachiisuufis h...

በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ስም በባንክ የተቀመጠ 16 ሚሊዮን ብር ታገደ

ምስል
የፖሊስ ኮሚሽነሩን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ በወላይታና በሲዳማ ግጭት የተጠረጠሩ ከንቲባውን ጨምሮ 100 ሰዎች ተከሰሱ በነፍስ ግድያ፣ ከቀዬ በማፈናቀል፣ በአስገድዶ ማስደፈር፣ የሃይማኖትና የንግድ ተቋማትን በማቃጠል፣ በዝርፊያና በሌሎች በርካታ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው የታሰሩት የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስቀመጡት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ታገደ፡፡ ዕግዱ የተጣለባቸው በተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ከሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በቁም እስር ቆይተው፣ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ)፣ አቶ መሐመድ አሸር፣ ሰባን ሙአድና ጀማል ፈርሃ መሐመድ ናቸው፡፡ ገንዘቡ በተለያዩ የሒሳብ ቁጥሮች የተቀመጠ መሆኑን፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት አሳውቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ገንዘቡ በማንኛውም መንገድ እንዳይወጣና ለሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ የዕግድ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በአቶ አብዲ፣ በክልሉ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ራህማ መሐመድና በዳያስፖራ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱራህዛቅ አሚን ላይ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤት ፈቅዷል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎትን የጠየቀው፣ ረቡዕ ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡ ነገር ግን በዕለቱ ተጠርጣሪ ሆነው ቀርበው የነበሩ የክልሉ የመስኖ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሡልጣን መሐመድ...

Namoonni 9 shakkaman to'annoo jala oolfan

ምስል
Namoonni to'attoota tiraafika qilleensaa Itoophiyaa hojii akka dhaabaniif gorsuufi balaliinsa idil- addunyaa gufachiisuuf yaalaniiru jedhaman sagal to'annaa jala oolfamaniiru. Namoonni Sivil Aviyeeshinii Itoophiyaa balaliinsa idil-addunyaa akka gufatu yaalanii fi oggeessoonni to'attoonni tiraafika qilleensaa hojii akka dhaabaniif gorsaa fi ogganaa turan jechuun shakkaman sagal to'annoo jala olfamaniiru. Ittaanaan Komishinara Poolisii Federaalaa Janaraalaa Takollaa Ayikokiru akka ibsaniitti, namoonni kunneen balaliinsa keessattu xiyyaaroonni biyya alaatii dhufan akka hin qubannee yaalii taasisaa turan jedhaniiru. Namoonni too'annoo jal oolfaman kun fincila hojii dhaabuu tarkaanfii kana dura hojjettoonni damee kanaa taasisaa turan qindeessaafi wal taasisaa akka turan himamuun ni yaadaatama. Maddi:FBC

የዜጎችን መብትና ነፃነት አፋኝ ነው የተባለው የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ........

ምስል
የዜጎችን መብትና ነፃነት አፋኝ ነው የተባለው የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ እንደገና እንዲቀረፅ ጥያቄ ቀረበ በሕጉ ላይ ጥናት እያደረገ ያለው ቡድን ረቂቅ አላዘጋጀም በምርጫ 97 ማግሥት የወጣው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ የዜጎችን መብት፣ ነፃነትና አጠቃላይ እንቅስቃሴን አፋኝና ገዳቢ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ተሰርዞ ውይይት ተደርጎበት መቀረፅ እንዳለበት ተገለጸ፡፡ ከሁለት ወራት በፊት የተቋቋመው የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ረቡዕ ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ እንደተገለጸው፣ የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ የተቀረፀውና በሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው በዓለም ላይ ምርጥ ተሞክሮ ካላቸው አገሮች ቃል በቃል ተወስዶ መሆኑ የተነገረ ቢሆንም፣ የአገሪቱን ሕዝቦች ሁኔታ ያላገናዘበ ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዬ ደንደአ እንደገለጹት፣ የአገሪቱ ሕዝቦች ስለሕጉ አስፈላጊነት፣ ጥቅምና ጉዳት ማወቅ አለባቸው፡፡ ግንዛቤ ወስደውም ሐሳባቸውን ማንፀባረቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ ሕጉ ምርጥ ተሞክሮ ካላቸው አገሮች እንደተወሰደ ቢነገርም፣ ሕዝቡ ውይይት ስላላደረገበት እንደገና ውይይት ተደርጎበት መቀረፅ፣ አተገባበሩንና አፈጻጸሙም መታወቅ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ የአፈጻጸም ችግር እንዳለበት የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ፖሊስ፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ጠበቆችና ዳኞች ውይይት አድርገውበት ችግሩ መቀረፍ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ሕጎች ሲቀረፁ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ በመሆን መብቶችን የሚያሰፉ፣ ችግሮችን የሚቀርፉ፣ በጥናት ላይ የተመሠረቱ፣ የዓለም ምርጥ ተሞክሮዎችን ያካተቱና የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው አክለዋል፡፡ ይኼንንም ለማድረግ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና ብቃት ያላቸው የሕግ ምሁራን የ...

ከአቶ በረከት ስሞን ውትውታ በስተጃርባ

ምስል
ከሰሞኑ አቶ በረከት ስሞን የአገር ውስጦቹን ጨምሮ የውጭ ሚዲያዎችን በመግለጫ አጥለቅልቀዋል፤በመግለጫዎቹም አርቲ ቡርቲውንም ነግረውናል እኛም ሰምተናል መልካም ነው።ነገር ግን አቶ በረከት ስሞን ምን እያሉን እንደሆነ አስተውለን ይሆን? ቀደም ሲል ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት መግለጫ ለመስጠት ሚዲያዎችን የሚያማርጡ ግለሰብ አሁን ምን ተገኝቶ ይሆን በዘመቻ መልክ መግለጫዎችን ደራርበው በላይ በላዩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች ለመስጠት የተገደዱት? እመኑኝ ባልልም እኔ ይህን አምናለሁ አቶ በረከት አይወድቁ አወዳደቅ ወድቆ ከተፈጠፈጠውና ለውጡን ለመቀልበስ እየተፍጨረጨረ ካለው ኃይል ብርቱ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል ምክንያት፡አቶ በረከት ከቅርብ አመታት ወዲህ የጠቅላይ ሚኒስትር የፖሊሲ አማካሪ ሆነው ቢቆዩም ቀደም ባሉት ዓመታት ከማስታወቂያ ሚኒስትር ጀምሮ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፤የሁሉም ነገር ዘዋሪ አንደሆኑም ይታወቃል ሰውዬው በእነዚህ የኃላፊነት ቆይታቸው ወደ ተለያዩ ሚዲያዎች ቀርበው የመናገርና የማሳመን ችሎታ አዳብረው የቆዩ በመሆናቸው በቀን ጅቦቹ ተመርጠው ተልዕኮውን ተቀብለው ኃለፊነታቸወን በመወጣት ላይ ይገኛሉ “ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋ ል  ድስት ጥዶ ማልቀስ”እንዲሉ አቶ በረከት ነገር ሁሉ ካለቀ በኋላ አሁን የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተው እየቆሰቆሱ ያለቃቅሱብናል፤በርካታ የኢህአዴግ አባላት በተለይም ከታች የሚገኙት በየመድረኩ ድርጅታችን ተበላሽቷል እረ ተው እንስተካከል ብለው ሲወተውቱ አቶ በረከት በማን አለብኝነት ዝም ብለው ለምን ቆዩ? አቶ በረከት አሁን እያደረጉ ያሉት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” የሚለውን ብሂል ያስታውሰናል።አይ በርዬ ደግሞ ዘና ብለ...