ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

Dhimma Finfinnee Oduudhaan utuu hin taane hojiidhaan mul'isuu qabna!

ምስል
Finfinnee Gurraandhala 20/2011(Tolawaaw waarii) Dhimma Finfinnee wajjin wal qabatee bara baay'eedhaaf waan hedduutu jedhame ammaan tanas waan hedduutu jedhamaa jira.Inni bu'aa siyaasaa hammaarrachuu barbaadu gara ofiif tolutti harkisuudhaan waan barbaade jechaa oola. Nuti Oromoon ammoo dhugaa qabnu qabachuudhaan falmaa jirra.Falmiin Finfinneef taasifnu gara fuulduraattis itti fufa.Dhimma Finfinnee irratti boqonnaa hin qabnu,kutannoodhaan itti fufiinsaan hojjenna. Pireezidaantiin Mootummaa  Naannoo Oromiyaa Obbo Lammaa Magarsaa dhimma Finfinnee irratti hirmaattoota yaa'ii idilee 9ffaa Caffee Oromiyaatiin gaafatamanii deebii kennaniin Mootummaan Naannoo Oromiyaa dhimma Finfinnee irratti ejjennoo Ummanni Oromoo qabuun ala ejjennoo biraa hin qabu,Finfinneen kaleessas har'as borus kan Oromooti jedhaniiru.Gaariidha! Hanga har'aatti dhimma Finfinnee irratti waan baay'ee odeessineerra.Amma Oduun ni ga'a.Qabatamaan hojjechuu qabna!Hojiin kutaawwan magaalaa Fi...

የ14 ቢሊየን ብር የታክስ ስወራና ማጭበርበር የፈፀሙ 105 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ምስል
ፊንፊኔ የካቲት 20/2011(ቶለዋቀ ዋሪ) የ 14 ቢሊየን ብር የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር የፈፀሙ 105 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴ ር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሰጡት መግለጫ የህዝብን ሀብት በመበዝበር እና የታክስ ማጭበርበር በመፈፀም የተለዩ 135 ድርጅቶች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የታክስ ማጭበርበር ወንጀል መፈፀማቸው በኦዲት የተደረሰባቸው 57 ድርጅቶች በወንጀል ምርመራ በኩል የወንጀል ምርመራ ተደርጐባቸው እንዲከሰሱ ተላልፏል፡፡ ከተያዙ ውስጥ በተደጋገሚ ተመላሽ የሚጠይቁ፣ በተደጋገሚ ባዶ የሚያሳውቁ እና በህዝብ ጥቆማ የተያዙ እንደሆኑ ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡ በታክስ ስወራው ከተጠረጠሩት 105 ግለሰቦች መካከል 64 የሚሆኑት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡ ሚኒስትሯ በመግለጫቸው 9 ቢሊየን ብሩ 100 ቀናቱ የተለዩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ቀሪው 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጥርና የካቲት ወር የተለየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ በዋነኝነት ተሳታፊ ሆነው የተገኙት አከፋፋዮች እና አስመጪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ማለትም 30 በመቶዎቹ ብቻ ቸርቻሪ መሆናቸውን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሯ በታክስ ስወራና ማጭበርበር የተለየውን 14 ቢሊየን ብር ድርጅቶቹ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሚኒስትሯ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡ ...

በመዲናዋ እስከ ሰኔ መጨረሻ 10 ሺህ የሚደርሱ ዜጎችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት ውጥን ተይዟል

ምስል
(ቶለዋቅ ዋሪ ፊንፊኔ የካቲት 19/2011)   በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎችን ከጎዳና ላይ የማንሳቱ ጅምር እሰከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ 10ሺህ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ፡፡ ከዚህ ውስጥም በጎዳና ያሉ 5 ሺህ ሰዎችን የከተማ አስተዳደሩ በመደበው በጀት ሲያነሳ ቀሪዎቹን ደግሞ ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ተፈፃሚ እንደሚሆን በአስተዳደሩ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ችግር ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም ዳይሬክተር አቶ እንዳሻው አበራ   ተናግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩም በጎዳና ላይ ያሉ ዜጎችን በማንሳት መልሶ ለማቋቋም 100 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያ ዙር ከጎዳና ላይ ዜጎችን የመታደግ ስራ 3 ሺህ 147 ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማንሳት በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አቶ እንዳሻው ገልፀዋል፡፡ በአሁን ሰዓትም እነዚህን ዜጎች በጊዜያዊ ማቆያ ተቋም በማስጠለል መሰረታዊ ፍላጎቶች ተሟልቶላቸው የስነልቦና ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ሆኖም በተቋሙ ድጋፍ ለማግኘት የገቡ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ተቋሙን ለቀው የወጡ አንዳንድ ሰዎች እንዳሉና በተቋሙ ድጋፍ ለማግኘት የሚፈልጉ የጎዳና ተዳዳሪዎች መኖራቸውንም ቢሮው አስታውቋል፡፡ በመጀመሪያ ዙር ከጎዳና ከተነሱ ዜጎች መካከል ከ92 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከተለያዩ ክልሎች የመጡ በመሆኑ በነበሩበት አካባቢ እንዲቋቋሙ እንደሚደረግም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም የጎዳና ተዳዳሪዎቹ የግል ፍላጎትና አቅም ተፈትሾ በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በጎዳና ህይወታቸውን የሚመሩ ዜጎችን ለመደገፍ መንግስት ከመደበው በጀት በዘለለ ማህበራዊ ትረስት...

Jiraataan Jimmaa umrii waggaa 108, dargaggeessa fakkaatan.

ምስል
Jiraataan Jimmaa umrii waggaa 108, dargaggeessa fakkaatan. - Maanguddoon dargaggeessa fakkaatan kun Koloneel Rijjaaluu Umar jedhamu. Koloneel Rijjaaluun bara 1903 akka dhalatan himu. Amma umriin isaanii waggaa 108 ta'us, namni isaan amanuu akka dadhabu himu. Soorama isaanii kabachiifachuuf yeroo Ministeera Dhimma Hojjetaa fi Hawaasummaa deemanitti burjaajjii uumtaniittu jedhamuun torbee tokkoof hidhamuu isaanii himu. Foon dheedhin ala bilchaataa akka hin jaalatin, araada kamuu akka hin qabnee fi ispoortii akka hojjetan himu. Bara Atsee Haaylasillaaseerraa kaasee loltummaan kan tajaajilan yammuu ta'u, Kooriyaa fi Ruwaandaatti ergama nagaa kabachiisuuf deemanii akka turanis ni ibsu. Ilmi Koloneel Rijjaaluu hangafti umrii isaanii waggaa 85ffaatti akka boqatan, daa'imman horatan keessaa jajjaboo 12niin ala xixiqqaa lakkoofsan kan hin beekne ta'uu himu. Maddi:FBC

አሁንም የወጣትነት መልክን የያዙት የ108 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው የጅማ ነዋሪ

ምስል
አሁንም የወጣትነት መልክን የያዙት የ108 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው የጅማ ነዋሪ  ወጣት የሚመስሉት የ108 ዓመት የጅማው አዛውንት ኮለኔል ርጃል ኡመር ይባላሉ፡፡ የ108 ዓመቱ ኮለኔል ርጃል በ1903 ዓ.ም እንደተወለዱም ነው የሚናገሩት፡፡ ይሁን እንጂ እድሜቸው 108 መሆኑን ሲናገሩ ብዙዎቹ እንደማያምኗቸው ነው የተናገሩት፡፡ ለዚህም ጡረታቸውን ለማስከበር ወደ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባቀኑበት ወቅት አጭበርብረሃል በሚል ለአንድ ሳምንት መታሰራቸውን ያስታውሳሉ። ከጥሬ ስጋ በስተቀር የበሰለ ስጋ እንደመይመገቡ የሚናገሩት ኮለኔሉ ስፖርትን የሚያዘወትሩና የሲጋራም ሆነ ሌሎች ደባል ሱሶች እንደሌሉባቸው ነው የገለጹት፡፡ ከአጼ ኃይለስላሴ ስርዓተ መንግስት ጀምሮ በውትድርና ያገለገሉ ሲሆን÷ በኮርያና በሩዋንዳ ለተለያዩ ወታደራዊ ተልኮዕዎችዎች ተልከው የነበረ መሆኑንም ይናገራሉ። የመጀመርያ ልጃቸው በ85 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት እንደተለዩ የሚናገሩት ኮለኔል ርጃል ከ12 ትላልቅ ልጆቻቸው በስተቀር ትናንሾቹን በቁጥር እንደማያውቋቸው ነው የገለጹት። አባታቸውም በ130 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሚናገሩት ኮለኔል ርጃል፥ ከዚህ በኋላም በሰውነታቸው አቋም ላይ የቅርፅ ለውጥ ሳይከሰት ለ10 ዓመት የመቆየት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ Source:FBC

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚሰነዘር ማስፈራራት ትክክለኛ ውሳኔ አይቀለበስም!

ምስል
(ቶለዋቅ ዋሪ ፊንፊኔ የካቲት 13/2011) መንግስት ህገ ወጥነትን መከላከል አለበት!ተግባሩ ነው፤ግዴታው ነው ህገ ወጦች ላይ በመንግስት የሚወሰድ እርምጃ ሊደገፍ እንጂ ሊወገዝና ሊያንጫጫ አይገባም።ህገ ወጦች በፈፀሙት ህገ ወጥ ድርጊት የሚጎዱትና እየተጎዱ ያሉት ብዙሃን ናቸው ለብዙሃን መብት መከበር ሲባል በጥቂት ህገ ወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ህግና ስርዓቱን ተከትሎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። መንግስትን በምርጫና በመሳሰሉት አገራዊ ጉዳዮች በማስፈራራት በማን አለብኝነት የተፈፀመ ህገ ወጥ ድርጊት እንዲስፋፋና የተፈፀመውም ተጠያቂነት እንዳይኖረው መሯሯጥ መፍጨርጨር ተገቢ አይደለም አይገባም! በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ከህገ ወጥ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ የመንግስት አካላት መውሰድ የጀመሩት ህጋዊ እርምጃ እንዲቀለበስ፤የህገ ወጦች ልብ እንዲያብጥ የሚደረገው ጥረት የተጀመረውን ህጋዊ እርምጃ በቁርጠኝነት በማጠናከር በእንጭጩ መቀጨት አለበት ትናንት በለገ ጣፎ ለገ ዳዲ በህገ ወጥ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላይ የተወሰደውን እርምጃ መነሻ በማድረግ በመራገብ ላይ የሚገኙ አሉባልታዎች፤ጉዳዩን ወደ ብሄር ወስዶ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው የሚደረገው ጥረት በትኩረት ሲታይ ያስቃል ያስገርማል ያንገበግባል! እርምጃው በሁሉም የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችና አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።በፊንፊኔ/አዲስ አበባና አካባቢዋ ላይ   የተጀመረው እርምጃ በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችና አካባቢዎች ላይም በተሞክሮነት ተወስዶ ተግባረዊ መሆን ይገባዋል። ትናንት በለገጣፎ ለገ ዳዲ በፈረሱ ህገ ወጥ ግንባታዎች መገረም የለብንም፤በፊንፊኔ ዙሪያ በሚገኙ አብዛኞቹ ከተሞች የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ህጋዊ ካርታ ያላቸው በጣት የሚቆጠሩ እንደሆነ እየተነገረ ነው...

Humni Elektiriikaa Ityoophiyaa hojiilee Hidha Haaromsaarratti hojjetamaniif,waliigaltee mallatteesse

ምስል
(Tolawaaq Waarii Finfinnee Guraandhala 11/2011)-Humni Elektiriikaa Ityoophiyaa Hidha Haaromsaarratti hojiilee madda anniisaa maddisiisuun dura hojjetamaniif, dhaabbata Chaayinaa CGGC waliin waliigaltee koontiraata fooyyessuu mallatteesse. Waliigaltichis hojiilee sibiilaa, dabarsa bishaanii, kaalvartiif meeshaalee hir'atan dhiyeessuu, rakkoo qulqullinaarratti muul'atan sirreessuu, oomish aa fi meeshaalee dhaabuu, hojiilee karroota to'annaa dabalata. Waliigaltichas hoji gaggeessaa olaanaa Humna Elektiriika Ityoophiyaa Dooktar Abrahaam Balaayii fi Ityoophiyaatti bakka bu'aa dhaabbata CGGC miistar Yaangitu mallatteesse. Waliigalteen har'a mallattaa'e ijaarsa hidhichaa ariifachiisuu keessatti ga'ee kan qabu ta'uu Dooktar Abrahaam ibsaniiru. Miistar Yaang gama isaanitiin dhaabbanni isaanii hojicha qulqullinaa fi ariitiin hojjechuuf, muuxannoo qabuun dhaabbilee biroo waliin akka tumsu eeraniiru. Hoji gaggeessaan Hidha Haaromsaa Injiinar Kiflee...

አሜሪካ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ላለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኗን አስታወቀች

ምስል
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር እንደተናገሩት፣ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለው ለውጥ ረዥም በሆነው የኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡ አምባሳደር ራይነር ይህን የተናገሩት የአሜሪካ ኤምባሲ፣ አይሬክስና የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በጋራ በአዳማ ከተማ ለአንድ ሳምንት ያዘጋጁት የጋዜጠኞች ሥልጠና ማብቂያ ላይ በክብር እንድግድነት ተገኝተው ለሠልጣኞች ሰርተፊኬት በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ጋዜጠኞች ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት አምባሳደር ራይነር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ግልጽ ራዕይ ይዘው መነሳታቸውንና ፖሊሲዎቻቸውን የአሜሪካ መንግሥት እንደሚደግፍ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ የለውጡ ፍኖተ ካርታ ነዳፊና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ እንዲመረጡ እንዳደረገች የሚነገረውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ባቀረቡበትና  መንግሥት ለውጥ ለማምጣት ወይም ቀደም ሲል በነበረው አስተዳደር ለመቀጠል ምርጫ ባደረገበት ወቅት፣ አሜሪካ በግልጽ እንደተንቀሳቀች ገልጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የተመረጡት በፓርቲያቸው እንጂ በአሜሪካ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ ‹‹አሜሪካ ይህን የማድረግ ሥልጣን የላትም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አሜሪካ ካላት ኃይል በላይ እንዳላት ያስባሉ፤›› ያሉት አምባሳደር ራይነር፣ የአሜሪካ መንግሥት የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን የለውጥ አጀንዳ እንደሚደግፍ ጠቁመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባገኙት ሰፊ ድጋፍ ምክንያት በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ መመረጣቸውን የገለጹት አምባሳደሩ፣ የለውጥ አጀንዳውን ራሳቸው ቀርፀው ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሆኑና የአሜሪካ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ...

ትልቅ ህዝብ ትልቅነቱ የሚለካው አመዛዝኖ በመኖሩ

ምስል
ትልቅ ህዝብ ትልቅነቱ የሚለካው አመዛዝኖ በመኖሩ እና ነገሮችን በእርጋታ መከወን በመቻሉ ነው።ትልቅ ህዝብ ቤተክርስቲያን ተቃጠለችብን ብሎ በምላሹ መስኪድ ላንድድ ብሎ በደቦ አይነሳም።አልያም በእኩይ አላማቸው መስኪድ ያቃጠሉ ሰዎች በሚኖሩ ጊዜ ማጣፊያው ቤ ተክርስቲያን ማቃጠል ነው ብሎ አያምንም። ለውጡ ፍፁም የራስ ምታት የሆነባቸው እና የታለመለትን ግብ እንዳይመታ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሀይሎች ለውጡን ለመቀልበስ እና አሁን ያለው የለውጡ አመራር ሀገር መምራት አልቻለም የሚል አንድምታ በመፍጠር አምባገነንነትን ዳግም በእጅ አዙር ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት ያግዝልናል ብለው የሚያስቡት የተለያዩ አጀንዳዎችን በመቅረፅ ብጥብጦችን ማስነሳት እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ላለፉት 8 ወራት በማንነት፣በወሰን፣በመልካም አስተዳደር፣ጉዳዮች ላይ የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት የብጥብጥ አጀንዳዎችን ቀርፀው በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥፋቶችን አድርሰዋል። በርካቶች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፣የበርካቶች ህይወት ጠፍቷል፣የበርካቶች ንብረት ወድሟል።በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በለውጡ ምክንያት ከ3 ሚሊዮን ዜጎች በላይ ተፈናቅለውባታል ብለው መንግስት ላይ እጃቸውን ይቀስራሉ።ማፈናቀሉን፤ማገዳደሉን አጀንዳችን ነው ብለው ደፍረው አይናገሩም።አላማቸው በሙስና እና በወንጀል በተጨማለቀ እጃቸው ለውጡን ጥላሸት መቀባት ነውና፡፡ እነዚህ እኩያን ኢትዮጵያን ጠንቅቀው ያውቋታል።የትጋር ስትጫር እሳት መፍጠር እንደምትችል ስለሚያውቁ ለአጀንዳቸው ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል። ሱማሌ ክልል ላይ በቀኝ እጃቸው ቤተክርስቲያን ላይ ክብሪት ይጭሩና በግራ እጃቸው የሀይማኖት ነፃነት ይከበር የሚል መፈክር ይዘው ይደመጣሉ፣ጎንደር ላይ መስኪድ ያቃጥሉና ህዝበ ሙስሊሙን መንግስት ላይ ...

ክብር ለመከላከያ ሠራዊታችን!

ምስል
(ቶለዋቅ ዋሪ ፊንፊኔ የካቲት 08/2011) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ከቆየ በኃላ ትናንት የካቲት 07/2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዳማ ከተማ የቀኑ ክብረ በዓል ማጠናቀቂያ ስነ ስርዓት ተከናውኖ አልፏል፤በጣም ደስ ይላል። በክብረ በዓሉ የማጠናቀቂያ ስነስርዓት ላይ የቀረቡ ትርኢቶች በጣም አስደሳች ከመሆናቸውም በላይ የመከላከያ ኃይላችንን ብቃት ያስመሰከሩ መሆናቸውን ያለምንም ማቅማማት መመስከር ይቻላል አሁን በጭፍን ጥላቻ መከላከያ ሰራዊቱን ለማጣጣል መሞከር ተገቢ አይሆንም!የመከላከያ ሰራዊቱን ስም ለማጉደፍ መሯሯጥም ሊቆም ይገባል!ምክንያቱም መከላከያ ሰራዊቱ ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የወጣ አስተማማኝ የአገር አለኝታና መከታ ነውና። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባሰሙት ንግግር ለመከላከያ ኃይላችን ተገቢውን ክብር መስጠት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። የመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ለአንድ ፓርቲ በመወገን የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ አብቅቶለታል፤መከላከያው የህዝብና የአገር መከታና አለኝታ እንደሆነ ተነግሮናል፤ይህን   አምኖ በመቀበል ለመከላከያ ሰራዊታችን ተገቢውን ክብር መስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል ይህ ማለት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ከተቋማቸው አሰራርና ድስፕሊን ወጥተው ጥፋት ሲያጠፉ አይጠየቁም ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው የሰራዊቱ አባላት ካጠፉ ህግን ከተላለፉ በህግ መጠየቃቸው የማይቀር ነው ማንም ከህግ በላይ አይደለምና!

የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት ተመደቡ

ምስል
የሕወሓትና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት መመደባቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ። አቶ አስመላሽ ከኢሕአዴግና ከሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው በተጨማሪ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲሠሩ እንደነበር ይታወሳል። በቅርቡ ተካሂዶ ከነበረው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በኋላ አቶ አስመላሽ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት እንዲያገለግሉ መመደባቸውን፣ በአሁኑ ወቅትም ሥራ መጀመራቸውን እንደሚያውቁ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አስመላሽ ላለፉት በርካታ ዓመታት በፓርላማ በመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትርነት ሲሠሩ የነበረ ቢሆንም፣ ካለፉት አራት በላይ ወራት ይኼንን ኃላፊነታቸውን ሲወጡ አልነበሩም። ምንጮች እንደገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለፓርላማው በላከው ደብዳቤ፣ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ሆነው ሲሠሩ የነበሩትን አቶ አስመላሽ ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታውቋል። በማከልም በአቶ አስመላሽ ምትክ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር እስኪሾም ድረስ፣ ቀደም ሲል በፓርላማው የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሆነው የተሾሙት የኦዴፓ አባል አቶ ጫላ ለሚ የመንግሥት ተጠሪ ኃላፊነትን በውክልና እንዲሠሩ መወሰኑን ምንጮች ተናግረዋል። አቶ አስመላሽ በመንግሥት ተጠሪነት ኃላፊነታቸው ምክንያት በፓርላማው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይጠቀሙበት የነበረውን ...