አሃዱ ለራስህ ስትል ጣፍጥ!

አሃዱ ለራስህ ስትል ጣፍጥ! #Ethiopia #Oromiyaa #Finfinnee
(ቶለዋቅ ዋሪ ፊንፊኔ የካቲት 04/2011)-አሃዱ የተባለው ኤፍ ኤም ሬዲዮ ፊንፊኔ-ሸገር ላይ ቁጭ ብሎ ማቅራራቱን ቢያቆም ይበጀዋል።
"ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ተብለህ ትጣላለህ" እንዲሉ አሃዱም ለራሱ ሲል ጥፍጥ ብሎ ቢቀጥል ይበጀዋል።ማቅራራት ለዛሚም እንዳልበጀ መዘንጋት ተገቢ አይሆንም!
ፊንፊኔ/አዲስ አበባ የአገራችን ኢትዮጵያ መዲና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫና መዲና የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ እንዲሁም የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ናት።አራት ነጥብ
ይህ ጣቢያ ዛሬ ማምሻውን በፊንፊኔ/አዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ በፌስ ቡክ ላይ የሚሰጡ የተሳከሩ አስተያየቶችን መነሻ በማድረግ የተንሻፈፈ ትንታኔ ለአድማጮቹ አቅርቧል
የጣቢያው ትንታኔ "ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል" የሚለውን ብሂል አስታወሰኝ።

ማይክራፎን በእጄ ነው ያለው ብሎ መዘባረቅ የውድቀትን መንገድ ከማመቻቸት ውጭ ሌላ ምንም ፋይዳ አይኖረውም።የአሃዱ የእብሪት ትንታኔ የለውጡ አመራር በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ እየተባለ ያለውን እየሰማ ጆሮ ዳባ ብሏል ሲልም ይከሳል።
የአሃዱ ተንታኝ ተብዬ ሰዎች አልገባቸውም እንጂ የለውጡ አመራርማ የፊንፊኔን ጉዳይ በአግባቡ ይዞ በዕውቀትና በከፍተኛ ትዕግስት እየመራው ነው።
የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ጉዳይን ከፍ አድርጎ በማንሳትና በማግለብለብ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በሰላምና በመቻቻል እንዳይኖር ሌተቀን የሚጥሩ ሃይሎች እንዳሉ ይታወቃል።አሃዱ የእነዚህ ሃይሎች ደጋፊ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ነገር ግን ጣቢያው ጉዳዩን ግብግብ ብሎ ያነሳበት ሁኔታ ሲታይ የፀረ ለውጥ ሃይሎች አራጋቢ መሆኑን አሳብቆበታል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa