ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚሰነዘር ማስፈራራት ትክክለኛ ውሳኔ አይቀለበስም!


(ቶለዋቅ ዋሪ ፊንፊኔ የካቲት 13/2011) መንግስት ህገ ወጥነትን መከላከል አለበት!ተግባሩ ነው፤ግዴታው ነው ህገ ወጦች ላይ በመንግስት የሚወሰድ እርምጃ ሊደገፍ እንጂ ሊወገዝና ሊያንጫጫ አይገባም።ህገ ወጦች በፈፀሙት ህገ ወጥ ድርጊት የሚጎዱትና እየተጎዱ ያሉት ብዙሃን ናቸው ለብዙሃን መብት መከበር ሲባል በጥቂት ህገ ወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ህግና ስርዓቱን ተከትሎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
መንግስትን በምርጫና በመሳሰሉት አገራዊ ጉዳዮች በማስፈራራት በማን አለብኝነት የተፈፀመ ህገ ወጥ ድርጊት እንዲስፋፋና የተፈፀመውም ተጠያቂነት እንዳይኖረው መሯሯጥ መፍጨርጨር ተገቢ አይደለም አይገባም!
በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ከህገ ወጥ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ የመንግስት አካላት መውሰድ የጀመሩት ህጋዊ እርምጃ እንዲቀለበስ፤የህገ ወጦች ልብ እንዲያብጥ የሚደረገው ጥረት የተጀመረውን ህጋዊ እርምጃ በቁርጠኝነት በማጠናከር በእንጭጩ መቀጨት አለበት
ትናንት በለገ ጣፎ ለገ ዳዲ በህገ ወጥ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላይ የተወሰደውን እርምጃ መነሻ በማድረግ በመራገብ ላይ የሚገኙ አሉባልታዎች፤ጉዳዩን ወደ ብሄር ወስዶ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው የሚደረገው ጥረት በትኩረት ሲታይ ያስቃል ያስገርማል ያንገበግባል!
እርምጃው በሁሉም የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችና አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።በፊንፊኔ/አዲስ አበባና አካባቢዋ ላይ  የተጀመረው እርምጃ በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችና አካባቢዎች ላይም በተሞክሮነት ተወስዶ ተግባረዊ መሆን ይገባዋል።

ትናንት በለገጣፎ ለገ ዳዲ በፈረሱ ህገ ወጥ ግንባታዎች መገረም የለብንም፤በፊንፊኔ ዙሪያ በሚገኙ አብዛኞቹ ከተሞች የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ህጋዊ ካርታ ያላቸው በጣት የሚቆጠሩ እንደሆነ እየተነገረ ነው።ለምሳሌ በቡራዩ ከተማ በቅርብ ዓመታት ከተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ህጋዊ ካርታ ያላቸው ከአስር አይበልጡም የሚል መረጃ አለ ይህ አስገራሚ ነው፤ታዲያ አዲሱ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ምን ይጠብቃል?ከለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ከተማ መስተዳድር ልምድ በመውሰድ ወይም በራሱ አካሄድ ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ የያዳግም እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል
የቡራዩም ሆነ ሌሎች የህገ ወጥ ግንባታ ያለባቸው ከተሞች ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ካልቻሉ እየተሰነዘረ ባለው ማስፈራሪያ ዝም ካሉ ሁሉም ነገር ልክ አይመጣም!
ህጋዊው ዜጋ በህገ ወጦች ላይ የሚወሰደውን ህጋዊ እርምጃ መደገፍ ይጠበቅበታል በተዘዋዋሪም ቢሆን የእርምጃው ጥቅም ለእርሱም ይተርፋልና! በተረፈ እናንት አስፈራሪዎች!በማስፈራሪያ የሚያፈገፍግ አመራር ከድሮው ኢህአዴግ ጋር ተቀብሮአልና የፌስ ቡክ ማስፈራሪያችሁ አዋጭ አይመስለኝም።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa