አሁንም የወጣትነት መልክን የያዙት የ108 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው የጅማ ነዋሪ

አሁንም የወጣትነት መልክን የያዙት የ108 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው የጅማ ነዋሪ
 ወጣት የሚመስሉት የ108 ዓመት የጅማው አዛውንት ኮለኔል ርጃል ኡመር ይባላሉ፡፡
የ108 ዓመቱ ኮለኔል ርጃል በ1903 ዓ.ም እንደተወለዱም ነው የሚናገሩት፡፡
ይሁን እንጂ እድሜቸው 108 መሆኑን ሲናገሩ ብዙዎቹ እንደማያምኗቸው ነው የተናገሩት፡፡
ለዚህም ጡረታቸውን ለማስከበር ወደ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባቀኑበት ወቅት አጭበርብረሃል በሚል ለአንድ ሳምንት መታሰራቸውን ያስታውሳሉ።
ከጥሬ ስጋ በስተቀር የበሰለ ስጋ እንደመይመገቡ የሚናገሩት ኮለኔሉ ስፖርትን የሚያዘወትሩና የሲጋራም ሆነ ሌሎች ደባል ሱሶች እንደሌሉባቸው ነው የገለጹት፡፡
ከአጼ ኃይለስላሴ ስርዓተ መንግስት ጀምሮ በውትድርና ያገለገሉ ሲሆን÷ በኮርያና በሩዋንዳ ለተለያዩ ወታደራዊ ተልኮዕዎችዎች ተልከው የነበረ መሆኑንም ይናገራሉ።
የመጀመርያ ልጃቸው በ85 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት እንደተለዩ የሚናገሩት ኮለኔል ርጃል ከ12 ትላልቅ ልጆቻቸው በስተቀር ትናንሾቹን በቁጥር እንደማያውቋቸው ነው የገለጹት።
አባታቸውም በ130 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሚናገሩት ኮለኔል ርጃል፥ ከዚህ በኋላም በሰውነታቸው አቋም ላይ የቅርፅ ለውጥ ሳይከሰት ለ10 ዓመት የመቆየት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

Source:FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa