ክብር ለመከላከያ ሠራዊታችን!
(ቶለዋቅ ዋሪ ፊንፊኔ የካቲት 08/2011) የኢትዮጵያ
መከላከያ ሰራዊት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ከቆየ በኃላ ትናንት የካቲት 07/2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ
መንግስት በአዳማ ከተማ የቀኑ ክብረ በዓል ማጠናቀቂያ ስነ ስርዓት ተከናውኖ አልፏል፤በጣም ደስ ይላል።
በክብረ በዓሉ የማጠናቀቂያ ስነስርዓት ላይ የቀረቡ
ትርኢቶች በጣም አስደሳች ከመሆናቸውም በላይ የመከላከያ ኃይላችንን ብቃት ያስመሰከሩ መሆናቸውን ያለምንም ማቅማማት መመስከር
ይቻላል
አሁን በጭፍን ጥላቻ መከላከያ ሰራዊቱን ለማጣጣል መሞከር
ተገቢ አይሆንም!የመከላከያ ሰራዊቱን ስም ለማጉደፍ መሯሯጥም ሊቆም ይገባል!ምክንያቱም መከላከያ ሰራዊቱ ከኢትዮጵያ ብሄር
ብሄረሰቦችና ህዝቦች የወጣ አስተማማኝ የአገር አለኝታና መከታ ነውና።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር
ዶክተር አብይ አህመድ ባሰሙት ንግግር ለመከላከያ ኃይላችን ተገቢውን ክብር መስጠት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት በመስጠት
ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ለአንድ ፓርቲ በመወገን የሚንቀሳቀስበት
ሁኔታ አብቅቶለታል፤መከላከያው የህዝብና የአገር መከታና አለኝታ እንደሆነ ተነግሮናል፤ይህን አምኖ በመቀበል ለመከላከያ ሰራዊታችን ተገቢውን ክብር መስጠትና
አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል
ይህ ማለት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ከተቋማቸው አሰራርና
ድስፕሊን ወጥተው ጥፋት ሲያጠፉ አይጠየቁም ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው የሰራዊቱ አባላት ካጠፉ ህግን ከተላለፉ በህግ
መጠየቃቸው የማይቀር ነው ማንም ከህግ በላይ አይደለምና!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ