የ14 ቢሊየን ብር የታክስ ስወራና ማጭበርበር የፈፀሙ 105 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ፊንፊኔ የካቲት 20/2011(ቶለዋቀ ዋሪ) የ14 ቢሊየን
ብር የታክስ ስወራ
እና ማጭበርበር የፈፀሙ
105 ግለሰቦች
በቁጥጥር ስር መዋላቸውን
የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሰጡት መግለጫ የህዝብን ሀብት በመበዝበር እና የታክስ ማጭበርበር በመፈፀም የተለዩ 135 ድርጅቶች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
የታክስ ማጭበርበር ወንጀል መፈፀማቸው በኦዲት የተደረሰባቸው 57 ድርጅቶች በወንጀል ምርመራ በኩል የወንጀል ምርመራ ተደርጐባቸው እንዲከሰሱ ተላልፏል፡፡
ከተያዙ ውስጥ በተደጋገሚ ተመላሽ የሚጠይቁ፣ በተደጋገሚ ባዶ የሚያሳውቁ እና በህዝብ ጥቆማ የተያዙ እንደሆኑ ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡
በታክስ ስወራው ከተጠረጠሩት 105 ግለሰቦች መካከል 64 የሚሆኑት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡
ሚኒስትሯ በመግለጫቸው 9 ቢሊየን ብሩ 100 ቀናቱ የተለዩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ቀሪው 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጥርና የካቲት ወር የተለየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ በዋነኝነት ተሳታፊ ሆነው የተገኙት አከፋፋዮች እና አስመጪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ማለትም 30 በመቶዎቹ ብቻ ቸርቻሪ መሆናቸውን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ በታክስ ስወራና ማጭበርበር የተለየውን 14 ቢሊየን ብር ድርጅቶቹ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈ ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሚኒስትሯ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም ይህ 14 ቢሊየን ብር በትምህርት ፣ በጤና ፣ በመንገድ እና በሌሎች ለህዝብ እና ለሀገር የሚጠቅሙ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ቢውል ኖሮ ምን ያክል ይሰራ እንደነበር በቀጣይ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡
Source:FBC
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ