የተጠረጠረ ግለሰብ እንዲያመልጥ ያደረጉ መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውው የተጠረጠረ ግለሰብ እንዲያመልጥ ያደረጉ መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 1 ሺህ 300 ጥይቶችና 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ከትላንት በስቲያ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆ ነበር፡፡
ከጋምቤላ አካባቢ ወደ ጎንደር በኤፍ ኤስ አር መኪና ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ እና 1 ሺህ 300 የክላሽ ጥይቶች ከነአሽከርካሪው መያዛቸውንም በዘገባው አመላክተናል፡፡
በወንጀል ተጠርጣሪ አሽከርካሪው በፖሊስ ተይዞ ምርመራ ሲደረግበት ‹ዋናውን የጦር መሳሪያ አሰራጭ› ጠቁሞ ጎንደር ከተማ ላይ አስይዞታል፡፡ ጉዳዪን ለመከታተል ወደ ጎንደር የሄዱት ሁለት መርማሪ ፖሊሶች ዋናውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አሰራጭ በቁጥጥር ሥር በማዋል ላይ እያሉም አሽከርካሪው (መጀመሪያ ላይ የተያዘው ተጠርጣሪ) አምልጧል፡፡
ተጠርጣሪ እንዲያመልጥ ማድረግ ደግሞ ወንጀል በመሆኑ ሁለቱም መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አትንኩት ከበደ ነግረውናል፡፡
ሁለት መርማሪ ፖሊሶችና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አከፋፋይ በሚል ተጠርጥሮ ጎንደር ላይ የተያዘው ግለሰብ አሁን ላይ በባሕር ዳር ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑንም ኮማንደር አትንኩት ተናግረዋል፡፡
(ምንጭ፡- የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa