11,607 ግለሰቦች በስድስት ማዕከላት
በቅርቡ
ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ የተጠረጠሩ 11,607 ግለሰቦች በስድስት ማዕከላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ገለጸ።
ተጠርጣሪዎቹ
በአዋሽ ማዕከል፣ በጦላይ፣ በዝዋይ አላጌ ማእከል፣ በዲላና ይርጋለም፣ እንዲሁም በባህርዳርና በአዲስ አበባ በሚገኙ ማእከላት እንደሚገኙም
ቦርዱ አመልክቷል።
ቦርዱ
የተጠርጣሪዎቹ ስም በየክልሉ አማካኝነት በአካባቢያቸው ለሚገኙ ለዞንና ወረዳዎች ተልኮ የሚለጠፍ መሆኑን ገልጾ ቤተሰቦች የተጠርጣሪዎቹ
ስም ከተገለጸ ጀምሮ ባሉበት ቦታ በመገኘት መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል።
ግለሰቦቹ
ተጠርጥረው የታሰሩበት ዋና ዋና ምክንያቶች ሁከት በመፍጠር፣ ሁከት ማስነሳት ሽብር በመንዛትና አለመረጋጋት በመፍጠር የግለሰቦችን
ቤት፣ ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማቃጠል፣ ኢንቨስትመንትን ማውደም፣ ማሕበራዊ አገልግሎቶች
እንዲቋረጡ ማድረግ፣ ግብይት፣ መንገድ በመዝጋትና ተሽከርካሪዎች በማውደም፣ በቦምብና በጦር መሳሪያዎች
በጸጥታ ሀይሎች ላይ ጥቃት ማድረስና መግደል፣ መሆናቸውን አመልክቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በአዋሽ ማዕከል፣ በጦላይ፣ በዝዋይ
አላጌ ማእከል፣ በዲላና ይርጋለም፣ እንዲሁም በባህርዳርና በአዲስ አበባ በሚገኙ ማእከላት እንደሚገኙም ቦርዱ አመልክቷል።
የተጠርጣሪዎቹ
ስም በየክልሉ አማካኝነት በአካባቢያቸው ለሚገኙ ለዞንና ወረዳዎች ተልኮ የሚለጠፍ መሆኑን ገልጾ ቤተሰቦች የተጠርጣሪዎቹ ስም ከተገለጸ
ጀምሮ ባሉበት ቦታ በመገኘት መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ