ልጥፎች

ከማርች, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ

ምስል
ፊንፊኔ መጋቢት 17/2011(ቶለዋቅ ዋሪ)  የኦዲፒን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት አሉ የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ። የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) 29ኛ የምስረታ በዓል እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኦዲፒ ሊቀ መንበርና የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል። ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁበት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፥ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል። ኢትዮጵያ ከራሷ ዜጎች በዘለለ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የምትበቃ በመሆኗ ይህንን ከግምት ማስገባት መልካም ነው ሲሉም ገልፀዋል። የኦዲፒ አላማ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩል ድምጽ በነጻነት የሚኖሩባትን ሀገር መፍጠር ነው፤ በዚህ ረገድም ከሁሉም ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል። ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክትም መለያየትን የሚሰብኩ አስተያየቶችን ወደ ጎን በመተው በጋራ መቆም አለብን ሲሉም ተናግረዋል። ለኦዲፒ አባላት ባስተላለፉት መልክት ደግሞ፥ ኦዲፒ በማንኛውም ሁኔታ ድምፆች መታፈን የለባቸ

የኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ODP) 29ኛው የምስረታ በዓል እና የአንደኛው ዓመት የለውጥ ጉዞን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ምስል
የኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ODP) 29ኛው የምስረታ በዓል እና የአንደኛው ዓመት የለውጥ ጉዞን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ “መደማማጥ ለቀጣይ የስኬት ጉዞ ” ! የኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ODP) ታሪክ እንደሚያስታውሰው በማናቸውም የትግል ምዕራፎች ውስጥ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲደርስ በነበረው ጭቆናና አድሎ ሕዝቡ የሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ብዙ ውጣ ውረዶች ዉስጥ አልፎ ዛሬ ላይ የደረሰ ፓርቲ ነዉ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብና የኦሮሞ ታጋዮች የታገሉላቸውና ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበት የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት መብቶች ፍሬያማ እንዲሆኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ODP) ባካሄደው መራራ ትግል በታሪክ የሚወሱ በርካታ ድሎችን ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በአገር ግንባታ ውስጥ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከመደበቅ አልፎም መሰረታዊ ጥያቄዎቹ ሰሚ በማጣታቸው ከአርሶ አደሩ ትግል ጀምሮ ትውልዶች መስዋዕትነት የከፈሉባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እንዲሁም የሕዝቡን ትግል ፈር ማስያዝና ማሻገርን ማዕከል አድርጎ በችግር ውስጥ የተመሰረተ፣በችግር የተፈተነና ሕዝቡን ከሰቆቃ ያዳነ ፓርቲ ለመሆኑ ትዉልድ የሚያስታዉሰዉ ነዉ፡፡  የኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ODP) በአገሪቱ ውስጥ ሕዝቡ የታገለላቸው የመብት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙና የኦሮሞ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሱን መንግስት የመመስረትና ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት እንዲጎናጸፍ ያስቻለ ነው፡፡ ትዉልድ በራሱ ቋንቋ እንዲማር፣ብሎም የክልሉ መንግስት የስራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ሆኖ እንዲያገለግል በፓርቲያችን ትግል በተቀየሰው መንገድ በቋንቋችን ህገ መንግስት ጽፈን፣ ጨፌ ተቀምጠን፣ ምዕተ ዓመታትን የሚሻገር አኩሪ ተግባር አከናዉነናል፡፡ በትግሉ ሂደትም የማህ

Ibsa ejjannoo Ayyaana Hundeeffama ODP waggaa 29ffaa

ምስል
Ibsa ejjannoo Ayyaana Hundeeffama ODP waggaa 29ffaafi kabaja adeemsa jijjiiramaa waggaa 1ffaa ilaalchisee kenname “Ilaafi ilaameen milkaa’ina Egereetiif”! ODPn Boqonnaa qabsoo seenaan yaadatu kamuu keessattuu loogummaa fi cunqursaa taasifamaa ture keessatti gaaffiiwwan bu’uuraa Ummata Oromoo deebisuuf paartii bu’aa ba’ii hedduu keessa cehee as gaheedha. Falmiin mirga siyaasaa,diinagdee fi hawaasummaa Ummanni Oromoo fi Qabsaawoonni Oromoo,Oromoo fi Oromummaaf gidiraa itti argan akka milkaawee firii godhatuuf qabsoo hadhaawaa taasiseen hojiiwwan boonsaan seenaan yaadatu galmeessuun danda’amera. Sabni akka sabaatti ijaarsa biyyaa keessatti ga’ee gumaachaa bahe seenaan isaa dhookfamuu bira darbee gaaffiiwwan bu’uraa isaa dhageettii dhabuu isaan qabsoo dhufaa darba seenaa qonnaan bultootaarraa jalqabee wareegamameef akka deebii argatuuf darbees qabsoo sabaa mataa walitti qabuun ceesisuu giddu galeessa godhatee paartii rakkoo keessatti hundaawee, rakkoon qoramee saba rakkoo baas

Dhimma Finfinnee irratti hawaasni nagaan jiraatu yaadda'uu hin qabu!

ምስል
Finfinnee, Bitootessa 04,2011(Tolawaaq Waarii) Dhimma Magaalaa Finfinnee irratti falmiin abbummaa wajjin wal qabatee jiru sabaafi sab-lammootaafi hawaasa nagaadhaan jiraachuu barbaadu yaaddoo keessa akka hin galchineef of eeggannoon taasifamuu qaba. Sabaafi sab-lammiin Finfinnee keessa jiraachaa tureefi ammas jiraachaa jiru Nagaadhaan jiraachuu danda'uu qaba.Nagaan ba'ee nagaan galuu,hojjetatee jiraachuu akk a danda'u taasisuu qabna. Kana yoo goonu humnoota waa'ee Finfinnee guyyuutti olkaasanii lallabuudhaan awwaara kaasuu barbaadan hawaasa nagaadhaan jiraachuu fedhu irraa adda baasuu dandeenya. Humnoota wacan kana bu'aa dhabsiisuun kan danda'amu hawaasa nagaan jiraachuu barbaaduuf aantummaa qabnu mul'isuudhaan yoo sochoonedha."Malaan Bishaan Waaddan" Humnoonni akka dhabanii akka malee wacaa jiran qullaatti hafuu kan danda'an deeggarsi hawaasa nagaan jiraachuu barbaaduuf taasifnu qabatamaan yoo mul'atedha. Kanaaf nama dhuunfaa

Dimokraasii dhugoomsuuf daangaa seeraa keessatti yaada bilisaan ibsachuun sirriidha -ODP

ምስል
Finfinnee, Bitootessa 3/2011(Tolawaaq Waarii) Dimokraasii dhugoomsuuf waan qabsoofnef, daangaa seeraa keessatti namuu yaada isaa bilisaan ibsachuun sirriidha jedhe Oromoo Demokraatiik Paartiin(ODP). ODPn haala yeroorratti ibsa baasen, tibbana ajandaa jajjabaan lama xiyyeeffannaa argachuu ibseera. Akka ibsa paartichaatti waa guguddaa lamatu deemaa jira. Tokko mirga Oromoon Finfinnee irraa qabu; inni lammataa ammoo hooggansa ODP abaaruu ta'uu eerera. Lachuu deemsa ummata gufachiisuuf karoora bahetti hidhata kan qaban ta'uus ibseera ODP. Kanaaf gufuu buqqisaa fi hiree baldhisaa lafa yaanne gahuun dubbii kana hiddaan hubachuu gaafata jedheera. Mirga Oromoon Finfinnee irraa qabu ilaalchisee sagaleen sadi dhag'amaa jiraachuu ibseera. Gareen tokko tuuta Oromoo saboota biraatin walitti buusuuf baajata guddaan halkanii guyyaa kan hojjatu ta'uu eeree, kunis gama tokkoon "Oromoon isin balleessuu heda" jechuun ummata nagayaa yaaddessa. Cinaa bir

አትሸወድ በፊንፊኔ ጉዳይ የመላው የኦሮሞ ህዝብ አንድነት እንደ ብረት የጠነከረ ነው!

ምስል
ፊንፊኔ መጋቢት 032011(ቶለዋቅ ዋሪ) የፊንፊኔ/አዲስ አበባን ጉዳይ ማጧጧፍ ስትፈልግ በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በኩል መግለጫ እንዲሰጥ ታደርጋለህ፤ ያዝ እንግዲህ! ፊንፊኔ የኔ ናት እያለ ያለው ታላቁ ህዝብ ደግሞ ትግሉን በእጥፍ አጠናክሮ ይቀጥላል። የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ ዛሬ አስቂኝ መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ትዕግስቱ ፓርቲያቸው በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ ኦዴፓ ያወጣውን መግለጫ በፍፁም እንደማይቀበል ተናግረዋል፤በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ጋር ፓርቲያቸው ተቀናጅቶ   እንድሚታገሉ ሰውዬው ተናግረዋል።ዴሞክራሲያዊ ያሏቸው ፓርቲዎች የትኞቹ እንደሆኑ ባይገልፁም።አቶ ትዕግስቱ አሁንም የወያኔ ተላላኪ መሆናቸውን እንዳልተዉ ታይቷል የምን ማስፈራራት ነው?ፊንፊኔ የኦሮሞ ምድር ናት።ሺህ ጊዜ ፀጉርህን ስትነጭ ብትውሉ ብትሳደብ ሰዳቢዎችን ሰብስበህ ስታቅራራ ብትውልም ተፈጥሮን መቀየር አትችልም። በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ መላው የኦሮሞ ህዝብ አንድነቱን   እንድ ብረት ያጠናከረ መሆኑ አልገባህም።”ልፋ ያለው ቆቡን ቀዶ ይሰፋል”።

ጎታች የሆኑ አስተሳሰቦችን ወደኋላ በመተው ወደፊት እንገስግስ

ምስል
አንድ በትንሽ ገጠር መንደር የሚኖሩ ህፃናት ከመንደራቸው ፊት ለፊት ካብ ስር ሆነው ይጫወታሉ፡፡ አንድ ዝምተኛ ህፃን በመካከላቸው አለ፡፡ ህፃናቱ በሚቦርቁበት ሜዳ ፊት ለፊት እንደሰንሰለት የተሳሰሩ ተራራዎች ይገኛሉ፡፡ ከህፃናቱ መካከል አንዱ በጨዋታቸው መሃል ለምን ያንን ተራራ መውጣት አንወዳደርም የሚል ሃሳብ አቀረበ፡፡ በሀሳቡ የተስማሙት ህፃናቱ ወደተራራው አቀኑ፡፡ ሌሎች ከመወዳደር ይልቅ ዳኛ መሆንን የመረጡና መመልከት ብቻ የፈለጉ ልጆች ከስር ሆነው ሁኔታውን ለመከታተል ተስማሙ፡፡ ውድድሩ ተጀመረ፡፡ ሃሳቡን ያቀረበው ህፃን ወደተራራው ለመውጣት የማሰላሰያ ጊዜም አልፈጀም፡፡ ወደላይ መውጣት ጀመሩ፡፡ ከታች የተደረደሩት ህፃናትም ወደቀ ወደቀች እየተባባሉ ይንጫጫሉ፡፡ ገና ሳይጀምሩ ከመንገድ ያቋረጡ ህፃናትም ከታች ሆነው ሌሎች ወደፊት ሲገሰግሱ የነበሩ ህፃናትን ከማበረታታት ይልቅ ውረዱ እንዳትወድቁ እያሉ ያስፈራሯቸው ጀመር፡፡ ህፃናቱ ተራራ መውጣት አዲሳቸው ባይሆንም ከስር ያሉት ልጆች ጫጫታና ማስፈራራት አቅም ስላሳጣቸው ውድድሩን መጨረስ ሳይችሉ ቀሩ፡፡ ከአንዱ ልጅ በስተቀር የእንወዳደር ሃሳብ ያቀረበው ልጅም ሳይቀር ከውድድሩ ውጭ ሆነ፡፡ በልጆቹ መሃል ዝምተኛው ልጅ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ የልጆቹ ጫጫታም ማስፈራራትም ተራራውን ከመውጣት አላገደውም፡፡ ወደፊት ብቻ፡፡ በመጨረሻም የተራራው ጫፍ ላይ የደረሰው ህፃን ቁልቁል ልጆቹን እያየ በደስታ ተፍነከነከ፡፡ በአሸናፊነት ስሜት እጁን ዘርግቶ ደስታዋን ገለጠ፡፡ ዝምተኛው ህፃን አሸናፊ ሆነ፡፡ ምክነያቱ ደግሞ ልጁ መስማት የተሳናው ነበርና የልጆቹን ጫጫታና ማስፈራራት ከጆሮው ስለማይደርስና ከመንገዱ ስለማያሰናክለው ነበር፡፡ ወደፊት ብቻ ማየቱ ጓደኞቹ ከመንገድ ያቋረጡትን የተራራ መውጣት ውድድር በድል እን

“ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ”

ምስል
መከባበር ይሻለናል ከተከባበርን አብረን መኖር እንችላለን ከተከባበርን እንደ ቀድሞው በጋራ በመተሳሰብና በመቻቻል አብሮ መኖር ቀላል ይሆናል፤ተራራ መስሎ የሚታየን ሁሉ ሜዳ ይሆናል። በመናናቅ አብሮ መኖር አይቻልም ከባድ ነው የተናናቀ ግለሰብና ህብረተሰብ እንዴት አድርጎ በጋራ መኖር ይችላል?አሁን በፊንፊኔ ጉዳይ ያለው መናናቅ እጅግ በጣም አደገኛ እንደሆነ በሁሉም ዜጋ ሊታወቅ ይገባል! ፊንፊኔ የእኔ ናት ያንተ አይደለችም ጨዋታ እጅግ በጣም አደገኛ ጨዋታ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፤ታሪክን በማጣመም ለፊንፊኔ የተለያዩ የፈጠራ ስሞችን መስጠት የትም አያደርስም “በረራ” ብትልም ባትልም ፊንፊኔ ፊንፊኔነቷን መቀየር አትችልም ወደድክም ጠላህም ፊንፊኔ የኦሮሞ ምድርነቷን መቀየር አትችልም። ይህ ማለት ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ወቅቶችና ዘመናት ወደ ፊንፊኔ መጥተው የኖሩ ነግደው ያተረፉ ሃብት ያፈሩ የወለዱ የከበዱ ብሄር ብሄረሰቦች ከአሁን በኋላ ፊንፊኔ ውስጥ መኖር አይችሉም ማለት አይደለም።ልክ እንደበፊቱ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ፊንፊኔ ውስጥ በህጋዊ መንገድ እስከ ሆነ ድረስ መኖርና ነግደው ማትረፍ ሃብት ማፍራት ይችላሉ፤ይገባል ይህን የሚከለክል ኃይል መኖር የለበትም። ያለፉ ገዢ ስርዓቶች የራሳቸውንና የተከታዮቻቸውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ ብቻ ብዙ ነገር አበላሽተው አልፈዋል፤አሁን እነርሱን መውቀስ ተገቢ አይሆንም አይገባም።እነርሱ በወቅታቸው ባላቸው የግንዛቤ ደረጃ የሰሩትን ሰርተው አልፈዋል ለሰሩት መልካም ነገር ሁሉ ምን ጊዜም እናመሰግናቸዋለን፤ለፈፀሙት ጥፋት ግን እነርሱን መውቀስ ምንም የሚያመጣው ነገር የለም ዋጋ የለውም። ዋናው ነገር የተበላሸውን ነገር ለቀጣዩ ትውልድ በሚመች መንገድ ማረምና ማመቻቸት ነው።አሁን ያለው ትውልድ በየዘርፉ የተበላሹ ነ

ስለ ፊንፊኔ ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃዎች

ምስል
የአገራችን ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት የኦሮሞ ክልል ( ኦሮሚያ ) አንድ አካል እና እምብርት የሆነችው ፊንፊኔ መጠሪያ ስሟን ያገኘችው በከተማዋ ማዕከላዊ ሥፍራ ከምድሯ ማህፀን የሚያፈልቀውን የተፈጥሮ ፍል ውሀ ምንጭን መሰረት በማድረግ ነው። በወቅቱ ፊንፊኔ ተብሎ የሚታወቀው አካባቢና ዙሪያው ከኦሮሞ ጎሳዎች አንዱ የሆነው የቱለማ ጎሣ ከሶስቱ ዐቢይ ጎሳዎች (“Balbala”) አንዱ የሆነው የዳጪ ንዑሳን ጎሳዎች የሆኑት የጉለሌ፣ የኤካ፣ የገላን እና የአቢቹ ጐሳዎች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል። እነዚህ ጎሳዎች በ 12 መንደሮች በመከፋፈልና በየራሳቸው የጎሳ መሪዎች ይተዳደሩ እንደነበር በወቅቱ የነበሩትን የጎሳ መሪዎች ስም በመዘርዘር ያስረዳሉ። ከእነዚህ የአካባቢ ጎሳ መሪዎች መካከል እነ ቱፋ ሙና፣ ዱላ ሃራ፣ ጂማ ጃተኒ፣ ጉቶ ወሰርቢ፣ ጂማ ጢቂሴ፣ አቤቤ ቱፋ፣ ዋሪ ጎሎሌ፣ ቱፋ አረዶ እና ሞጆ ቦንሳራ ጥቂቶቹ ናቸው። በተለይም ፊንፊኔ የጉለሌ ኦሮሞ ጎሳዎች የሚበዙበት እንደነበረች በ 1868 አካባቢ በካቶሊክ ሚሲዮኖች የተፃፉ ድርሳናት ያስረዳሉ። በሌላ በኩል አፄ ሚኒሊክ ቤተ መንግስታቸውን በእንጦጦ ላይ ከማድረጋቸው በፊት በመስከረም 1868 ዓ . ም በፊንፊኔ አካባቢ ካቶሊክ ሚሲዮኖች " የፊንፊኔ ሚሲዮን " በሚል መጠሪያ ቤተክርስቲያንና የዕምነት ማስፋፊያ ጣቢያዎች ከፍተው ሲንቀሳቀሱ እንደነበርና በዚህም ፊንፊኔ በመልማትዋ ምንሊክ መቀመጫውን ወደ አከባቢው እንዲያዛውር በዋነኝነት