ስለ ፊንፊኔ ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃዎች


የአገራችን ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት የኦሮሞ ክልል (ኦሮሚያ) አንድ አካል እና እምብርት የሆነችው ፊንፊኔ መጠሪያ ስሟን ያገኘችው በከተማዋ ማዕከላዊ ሥፍራ ከምድሯ ማህፀን የሚያፈልቀውን የተፈጥሮ ፍል ውሀ ምንጭን መሰረት በማድረግ ነው። በወቅቱ ፊንፊኔ ተብሎ የሚታወቀው አካባቢና ዙሪያው ከኦሮሞ ጎሳዎች አንዱ የሆነው የቱለማ ጎሣ ከሶስቱ ዐቢይ ጎሳዎች (“Balbala”) አንዱ የሆነው የዳጪ ንዑሳን ጎሳዎች የሆኑት የጉለሌ፣ የኤካ፣ የገላን እና የአቢቹ ጐሳዎች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል። እነዚህ ጎሳዎች 12 መንደሮች በመከፋፈልና በየራሳቸው የጎሳ መሪዎች ይተዳደሩ እንደነበር በወቅቱ የነበሩትን የጎሳ መሪዎች ስም በመዘርዘር ያስረዳሉ። ከእነዚህ የአካባቢ ጎሳ መሪዎች መካከል እነ ቱፋ ሙና፣ ዱላ ሃራ፣ ጂማ ጃተኒ፣ ጉቶ ወሰርቢ፣ ጂማ ጢቂሴ፣ አቤቤ ቱፋ፣ ዋሪ ጎሎሌ፣ ቱፋ አረዶ እና ሞጆ ቦንሳራ ጥቂቶቹ ናቸው። በተለይም ፊንፊኔ የጉለሌ ኦሮሞ ጎሳዎች የሚበዙበት እንደነበረች 1868 አካባቢ በካቶሊክ ሚሲዮኖች የተፃፉ ድርሳናት ያስረዳሉ።
በሌላ በኩል አፄ ሚኒሊክ ቤተ መንግስታቸውን በእንጦጦ ላይ ከማድረጋቸው በፊት በመስከረም 1868 . በፊንፊኔ አካባቢ ካቶሊክ ሚሲዮኖች "የፊንፊኔ ሚሲዮን" በሚል መጠሪያ ቤተክርስቲያንና የዕምነት ማስፋፊያ ጣቢያዎች ከፍተው ሲንቀሳቀሱ እንደነበርና በዚህም ፊንፊኔ በመልማትዋ ምንሊክ መቀመጫውን ወደ አከባቢው እንዲያዛውር በዋነኝነት እንደገፋፋቸው በወቅቱ የነበረ ሉዊፊ ላሴሬ የተባለው ሚሲዮን ፅፏል። ሌላው ምክንያት አፄ ሚኒሊክ አያታቸው "...አንቺ ምድር ዛሬ "..." ሞልተውብሻል፤ ነገር ግን ወደፊት የልጄ ልጅ ቤት ሰርቶብሽ ከተማ ትሆኛለሽ" በማለት ለባለቤታቸው ለእቴጌ ጣይቱ እንደነገራቸውና እቴጌም ባላቤታቸው ደቡብን ለመውረር በመጡበት ጊዜ ከባላቤታቸው ጋር ለጤናቸው ጉዳይ ወደፍል ውሃ ሄደው በነበረበት ወቅት ከነበሩበት ድንኳን ውጭ በመንዝ አካባቢ አይተው የማያውቁትን አበባ አይተው በመደነቅ አዲስ አበባ በማለታቸው 1887 ጀምሮ ፊንፊኔ - አዲስ አበባ መባል ጀመረች። የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የአከባቢዎችም ነባር ስያሜዎች ለውጥ/መቀየር አንድ ተብሎ ተጀመረ።
በሚኒሊክ የጦር አበጋዞች በመላ ኦሮሞ አካባቢና የደቡብ አካባቢዎች ላይ አጠቃላይ ወረራ እስከታወጀበት .. 1870 በነበረው ጊዜ እርሻና ከብት እርባታን የኑሯቸው ዋነኛ መሰረት በማድረግ በፊንፊኔና አካባቢዋ ይኖሩ የነበሩት የኦሮሞ ተወላጆች እንደተቀረው የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉ በገዳ ሥርዓት ይተዳደሩ የነበረ ከመሆኑ በተጨማሪ ፊንፊኔ በኦሮሞ ክልል እምብርት ሥፍራ ላይ የምትገኝ መሆኗም የንግድና የአምልኮ ማዕከልም መሆን አስችሏታል። በገዳ ስርዓት ኦዳ ነቤ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ከሚከናወንባቸው የኦሮሞ መሬት ክፍሎች አንዷም ነበረች። ምንም እንኳን የፊንፊኔ ኦሮሞዎች በባህላቸው መሰረት ከራሳቸው፣ ከተፈጥሮና ከአካባቢያቸው ጋር ተስማምተው በዚህ ማዕከላዊ በሆነ ስፍራ 16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሰላም መኖራቸው የሚያጠያይቅ ባይሆንም በፊንፊኔና በዙሪያዋ በነበሩ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ላይ ከሰሜኑ አጎራባች ደጋማ ክፍል በሚነሱ ማህበረሰብ ተወላጆች ወረራና ዝርፊያ ይካሄድ የነበረው ሚኒሊክ የሸዋ ንጉስ ከመሆናቸውም አስቀድሞ እንደነበር በወቅቱ በስፍራው የነበረው የእንግሊዙ የዲፕሎማቲክ ልዑክ ሻለቃ W.C Harris [የኢትዮጵያ ደጋማ ክፍሎች The Highlands of Ethiopia, (1884)] በሚል ባሳተመው የጉዞ ማስታወሻ መፅሀፉ ሰፍሮ ይገኛል።
በሂደት ወደ አጠቃላይ ወረራ የተቀየረውና በሚኒሊክ ወራሪ ጦር ድል አድራጊነት የተጠናቀቀው ዘመቻ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢውን የኦሮሞ ተወላጆች ለሞት፣ ለአካል መጉደልና ስደት ዳረገ። ከሞትና ስደት የተረፉት የመላ ኦሮሚያና የደቡብ ሕዝቦችም ነፃነታቸው ተገፎ በባርነት ቀንበር ስር ወደቁ። መሬታቸውን ተቀሙ። ሃብት ንብረታቸው በወራሪው ተዘረፈ። ግፍና በደሉ በዚህም አልበቃ ብሎ ፊንፊኔ ከወራሪው ጦር መቀመጫነት ወራሪውን ጦር ተከትለው የመጡ ነዋሪዎች መስፈሪያ ከተማ ሆነች።
የፊንፊኔ ነባር ነዋሪዎች ከርስታቸው ተነቅለው ለወራሪው ሹሞች ተሰጡ። ለዚህ አስከፊ ተግባር ህጋዊ መሰረትና ድጋፍ ለመስጠት ሲባል 1907 .. የመሬት አዋጅ (Land Charter) ተከትሎ በወጣው ማስታወቂያ የፊንፊኔ ነባር ኦሮሞዎች ካርታ ያልወሰደ በመሬቱ ከመቀመጥ በስተቀር መሬቱ ያንተ አይደለም ተባለ። የፊንፊኔ ነባር የኦሮሞ ተወላጆች በገዛ መሬታቸው ጪሰኛ ሆኑ፤ በእምነትና ባህላቸው መሰረት አምልኮአቸውን እንዳይፈፅሙ ታግደው የወራሪውን እምነት የመቀበል የመከራ ቀንበር በግዳጅ በላያቸው ላይ ተጫነ፣ ከዚህም አልፎ የጉለሌና የኤካ ጉሳዎች ሊመናመኑ ችለዋል።
በወራሪው ጨቋኝ ገዢ የፊንፊኔ ነባር የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የወደቀው ግፍና መከራ በግድያ፣ በምርኮ፣ ከርስት መነቀልና በጭሰኝነት ጉልት ሥርዓት በማደር ብቻ ያበቃ አልነበረም። በኦሮሞ ተወላጅ ላይ እንደተጫነው የወራሪው ባህል ሁሉ በኦሮሞ ባህልና የቋንቋ ስያሜ ይታወቁ የነበሩ የፊንፊኔና ዙሪያዋ አካባቢዎች የከተሞችና የቦታ ጥንታዊ መጠሪያዎች እንዲቀየር ተደረገ። ከነዚህ ውስጥ ፊንፊኔ የሚለው የጥንት መጠሪያዋ በሃይል ተቀይሮ "አዲስ አበባ" በሚል ስያሜ ተተካ።

በሳባመጠሪያ
የጥንት/ቀድሞመጠሪያ
አዲስመጠሪያ
Agamsa
አገምሳ
መርካቶ
Doobbii
ዶቢ
ቀጨኔ
Hurufa Boombii
ሁሩፈቦምቢ
ጃንሜዳ
Dildila
ድልድለ
እንጦጦ
Eekkaa
ኤካ
የካ
Birbirsa Gooroo
ቢርቢርሰጎሮ
ፒያሳ
Caffee Araaraa
ጨፌአራራ
አራትኪሎ
Malkaa Daabus
መልካዳቡስ
ቸርቺልጉዳና
Caffee Tumaa
ጨፌቱማ
ስድስትኪሎ
Caffee Aannanii
ጨፌኣነኒ
ሜክሲኮ
Qarsaa
ቀርሳ
ካዛንቺስ
Baddaa Ejersaa
በዳኤጀርሳ
ራስካሳሰፈር
Mujjaa
ሙጃ
ሽሮሜዳ
Garbii
ገርቢ
ሰንጋተራ
Golboo
ጎልቦቄራ
ቂርቆስ
Calcalii
ጨልጨሊ
ሳርቤት
Roobii
ሮቢ
ነፋስስልክ
Burqaa Finfinnee
ቡርቃ
ፊንፊኔፍልውሀ
Tulluu Heexoo
ቱሉሔጦ
ትልቁቤተመንግስት
Lupha Kormaa
ሉጳኮርማ
ራስብሩሰፈር
Baaroo Kormaa
ባሮኮርማ
ራስተሰማሰፈር
Hrbuu Irrechaa
ሐርቡእሬቻ
ራስሀይሉሰፈር
Karra Qirixi
ከራቂሪጢ
ሰሜንበር
Adami
አዳሚ
ሰሜንማዘጋጃ
Babo
ባቦ
አዲሱቄራ
Burqa Qoricha
ቡርቃቆርቻ
የካሚካኤል
የነፍጠኛው ድርጊት የኦሮሞ ጥንታዊ ስሞችን መቀየር ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ጥንታዊ ስያሜዎችን በማዛባትም ጭምር ግፍ የተሰራ መሆኑ ለምሳሌ፡- ሀቃቂ ወደ አቃቂ፣ ቀሊቲ ወደ ቃሊት፣ ቀበነ ወደ ቀበና፣ ኤካ ወደ የካ...ወዘተ አዛብቶ እንዲጠሩም የተደረጉ እስከ ዛሬም ምስክሮች ናቸው።
በሚኒሊክ እግር የአገዛዙን ሥርዓተ-መንበር የተቀበሉት አፄ /ሥላሴም ነባሩን የኦሮሞ ተወላጅ ከመሬቱ የማፈናቀል እና ማንነቱን የመፋቅና የመደምሰሱን እርምጃ ከአፄ ሚኒሊክ ባልተናነሰ ይልቁንም በረቀቀና በመጠቀ የትምህርትና ባህል ፖሊሲ በመቅረፅ አጠናክረው ገፉበት። የኦሮሞን ህዝብ ከሀገሪቱ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ውስጥ በማግለልና በመግፋት ባህል እና ቋንቋው እንዲጠፋ የተጠናከረ ዘመቻ አካሄዱበት። ነባሩ የኦሮሞ ተወላጅ ራሱ በመሰረታት ከተማ ከገዛ መሬት ከመፈናቀል አልፎ በቋንቋው እንዳይማር እንዳይገለገል በተቃራኒው ባይተዋር ተደርጎ በባህል በቋንቋው እንዲሸማቀቅ ተደረገ። ኦሮሞ ራሱ በመሰረታት ፊንፊኔ 1960 . ማብቂያ አካባቢ የመሬት ይዞታ መረጃ እንደሚያመላክተው የመሬት ይዞታ ክፍፍሉ ከመሬቱ 50 በመቶ ያህሉ በመኳንንትና መሳፍንቱ እጅ የነበረ ሲሆን፣ 33 በመቶ የሚሆነው ደግሞ የእምነት ተቋማት ሥር ወድቆ እንደነበር ተጨባጭ የጽሁፍ መረጃዎች ያረጋገጡት እውነታ ሲሆን ነባሩ የኦሮሞ ተወላጅ ግን ከይዞታው እየተነቀለ ወደ አልለማውና በወባ ነዲድ በተወረረው ወደከተማዋ ጥግ በመግፋት በከተማው መሃል የኦሮሞ ተወላጅ ቁጥር አናሳ እንዲሆን ተደረገ።
እግር በግር የተተኩት የአፄ ሥርዓቶች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የጫኑትን የመከራ ቀንበር የኦሮሞ ሕዝብ ያለተቃውሞ አሜን ብሎ የተቀበላቸው አልነበሩም። እንደሁሉም የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝቦች ወቅትና ጊዜው በፈቀደውና በተለያየ መንገድ ጭቆናውን እምቢ/አልቀበልም በማለት አምጿል። የመጫና ቱለማ የመረዳጃ ማህበር የዚሁ የሰላማዊ አመፅ መገለጫ ነው። የባሌ ኦሮሞ ገበሬዎች አመፅም እንዲሁ። ምንም እንኳ እነዚህ የመብት ጥያቄዎች እና አመፆች የኦሮሞን ሕዝብ ወደድል ባይመሩትም 1966 . ሕዝባዊ ንቅናቄ እርሾ ለመሆናቸው በወቅቱ ይስተጋቡ የነበሩት የመሬት ላራሹ፣ የብሔርና የዲሞክራሲ መብት ጥያቄዎች ማስረጃ ተደርገው ሊቀርቡ ይችላሉ።
የአፄውን መንግስት በሀይል ገልብጦ ኢትዮጵያን 17 ዓመታት የገዛው ወታደራዊ መንግስት ለእነዚህ ሕዝባዊ የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ባህሪም ሆነ መሰረት ያልነበረው የአፄዎቹ ተቀጥላ ከመሆን ያለፈ አልነበረም። በመሆኑም የብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች ጥያቄን ፈታሁ በሚል በሀይል የተጫነን አንድነት በህዝቦች ላይ አጠናክሮ በመጫን የኦሮሚያን ሀብትና የኦሮሞ ወጣቶችን የስልጣን ዘመኑ ተጀምሮ እስከጨረሰ ላኬሄዳቸው ጦርነቶች መስዋዕት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መላ ሀገሪቷ በጦርነት እሳት ከጫፍ እስከጫፍ ከመንደዷ በተጨማሪ ሕዝቦቿም የጦርነቱ ገፈት ቀማሽ ሆነው በአስከፊ የድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲማቅቁ ያደረጋቸው መሆኑ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፤ ደርግ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ አትሞ ያለፈው ጥቁር የታሪክ ጠባሳ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ጭቁን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ እና ለብሄር መብት መረጋገጥ የሚየደርጉት ትግል በየማዕዘኑ ተፋፍሞ እንዲቀጣጠል ያደረገ ሲሆን ይህም እስካልተረጋገጠ ድረስ ሀገሪቷ ከጦርነት ወደ ጦርነት ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እንጂ የሰላምም ሆነ የልማትን ጭላንጭል የማየት እድል እንደማይኖራት ሁሉም የዲሞክራሲ ሀይሎች በገሀድ የተረዱበት ዘመን ነበር። የኦሮሞ ሕዝብ በአጠቃላይ የፊንፊኔ ነባር ተወላጆች የቱለማ ጎሳዎች እና ሌሎች ነዋሪ የኦሮሞ ተወላጆች በፊንፊኔ ላይ ያላቸውንየልዩ ጥቅምሥረ-ነገር ከዚህ የታሪክና የህግ መብት የሚመነጭ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ የሚሆነውም በዚህ የተነሳ ነው።

3.2. ከዴሞክራሲያዊ የፌደራል ሥርዓት ግንባታ አንፃር የአጀንዳው ወሳኝነት
የደርግ አምባገነን ሥርዓት በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሀይሎች ግንቦት 20 ቀን 1983 . ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገርስሶ ወደማይመለስበት ጉድጓድ ሲወረወር የአፈናና የጭቆና ዘመን አብቅቶ የነፃነት ጎህ ሲቀድ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብም ልክ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦችና የዴሞክራሲ ሀይሎች ሀገሪቱ ለዘመናት የተጓዘችበትን አቅጣጫ በመቀየር በሀይል የሚጫን አንድነት ሳይሆን በመፈቃቀድ በመተባበር የምትመሰረት አዲሲቷን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ መሰረት ላይ ማነፅ እንደዲቻል በጋራ ባካሄደው ዘርፈ- ብዙ እንቅስቃሴ የዲሞክራሲ የእኩልነት መብቶችና የሁሉም ሕዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት መርሆዎች የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መብት ምሰሶዎች የሚሆኑበት የአዲስ ምዕራፍ ጅማሮ በር የሚከፈትበትን ጎዳና የኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተርን በማፅደቅ ወደ ተግባር ገብቷል።
ሐምሌ 15 ቀን 1983 . በነጋሪት ጋዜጣ ፀድቆ የወጣው የሽግግር መንግስት ቻርተር የዲሞክራሲ መብቶች በሚል ርዕስ በክፍል አንድ አንቀፅ ሁለት ስር የብሔሮች የብሔረሰቦችና የሕዝቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን የሚያረጋግጥ ድንጋጌ ማካተቱ የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ትግል ከሌሎች የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝቦችና የዲሞክራሲ ሀይሎች ጋር ያደረጉት የዘመናት ትግልና መስዋዕትነት ያስገኘው ቀዳሚ የድል ፍሬ ተደርጎም ሊቆጠር ይችላል።
የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ የሰላማዊ ሽግግር ጉባኤ አካል በመሆን በቻርተሩ ላይ በክፍል አንድ በአንቀጽ 1 እና 2 ስር የሰፈሩትን ዲሞክራሲያዊ መብቶች በተለይ እንዲካተቱ የታገለበት ዋነኛ ምክንያት የኦሮሞ ሕዝብ የፈቃድ እንጂ ዳግም የሀይል አንድነት እንዳይጫንበት ያሳለፋቸው የመቶ ዓመት የጭቆናና የመገፋት ስርዓት እንዳይመለስ እንዲሁም እንደግለሰብ ሁሉ ለቡድን መብቶችም እውቅናና ጥበቃ መስጠት እንዲቻል በማሰብ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሁሉ የራሱን ማንነት የመጠበቅና የማስክበር ባህሉንና ታሪኩን የማበልፀግ እንዲሁም በቋንቋው የመጠቀምና ቋንቋውን የማበልፀግ መብቱን እንዲያረጋግጥ በማስቻል በመፈቃቀድና በእኩልነት የተመሰረተች አዲሲቷን ኢትዮጵያ ከመፍጠር ውጭ ሌላ መንገድ እንደሌለ ከታሪክ መማር በመቻሉ ነው።
የኢ... ህገመንግስትና የፌዴራል ስርዓቱ አጠቃላይ ዓላማ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲን ለማስፈን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን ለማፋጠን የሚያስችል አንድ የጋራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ መገንባት ነው። በዚህም መሰረት ሕገመንግስቱ የህጎች ሁሉ የበላይ ሆኖ በተለያዩ ድንጋጌዎቹ ውስጥ የሀገራችንን የፖለቲካ ስርዓት፣ የስልጣን ባለቤትነት፣ የመንግስት አካላትን አወቃቀር የስልጣን ክፍፍልና የመንግስት አሰራርን እንዲሁም የዜጎችን መብቶች፣ ነፃነቶች በመንግስትና በዜጎች መካከል ያለውን ግንኙነት በግልፅ ደንግጓል። ሕገ-መንግስቱን መሰረት አድርገው የሚወጡ ዝርዝር ሕጎችም ከሕገ-መንግስቱ ጋር መቃረን እንደሌለባቸውና የሚቃረኑም ሆነው ከተገኙ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው በግልጽ የተመለከተ ጉዳይ ነው።
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ዲሞክራሲያዊ የፌደራል ሥርዓት ለመገንባት የተደረጉት ጥረቶች አንድነትን በልዩነት ውስጥ ለመገንባት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ካደረጓቸው ጥረቶችና ርብርቦሽ ጋር ተጣምሮ መታየት የሚገባው ታላቅ ታሪካዊ ጉዳይ ነው የሚባልበት መሰረታዊ ምክንያት ከዚህ የሚመነጭ ነው። በከተማዋ ውስጥ የሚገኘው ነባሩ የኦሮሞ ህዝብ እነዚህ መብቶች ማለትም በቋንቋው የመጠቀምና የመማር፣ ባህሉን የመንከባከብና የማሳደግ መብትና እድል ተነፍጎ የሚገኝ በመሆኑ መብቱን ለማስከበር ተጨባጭ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚገባቸው አንዱ ማሳያ ነው። በመሆኑም በፊንፊኔ/ አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖረው ነባር የኦሮሞ ተወላጅና ነዋሪ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 39 ንዑስ አንቀፅ (1) እና (2) መሠረት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን፣ በቋንቋው የመናገር፣ የመፃፍ፣ ቋንቋውን የማሳደግና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት ያለው በመሆኑ ሊከበርለት ይገባል።
ከዚህም በተጨማሪም ፌዴራላዊ የአስተዳደር ሥርዓታችን እየዳበረ መምጣቱ የሕገመንግስቱን አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልገው ዝርዝር ሕግ ሊያካትታቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጉዳዮችን አንጥረን እንድናወጣ ሰፊ እድልም ሰጥቶናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የሁለት አስርት አመታት ጉዟችን በትክክለኛ ጎዳና ላይ እንደነበር የሚያረጋግጥን እውነታ የልዩ ጥቅም ማስጠበቂያ ዝርዝር ሕጉም ሳይወጣ እንኳ የብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መስተዳድሮችን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ 7/1984 አንቀፅ 15(1) () መሰረት በፀደቀው የመጀመሪያው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መስተዳድር ሕገ መንግስት በአዋጅ ቁጥር 2/1985 አንቀፅ 58 መሰረት ፊንፊኔ የክልሉ ዋና ከተማ ሆኖ በመወሰኑ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የክልሉ ዋና ከተማ በመሆኑ የክልሉ መንግስት በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውስጥ ተስፋ ሰጪ ሥራዎችን አከናውኗል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት /ቤት፣ የኦሮሞ ባህል ማዕከል እና የአፋን ኦሮሞ /ቤቶች የሚገነቡበትን ቦታ ከሊዝ ነፃ በማግኘት ግንባታዎች ተጀምሯል። እነዚህን የግንባታ ቦታዎች ከማግኘት ባሻገር አብሮ ለመልማትና ደህንነትን ለማስጠበቅ በትብብር ክልላችንና መስተዳድሩ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ገላጭ ሲሆን ከሽግግሩ መንግስት ምስረታ አንስቶ በአመዛኙ የመስተዳድሩ ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የኦሮሞ ተወላጅ መሆናቸው ሕገመንግስታዊ ድጋፍ ያለውና የዚሁ መልካም ግንኙነት መገለጫ ነፀብራቅ ነው።
በሌላም በኩል ተቋማዊና ሥርዓታዊ ገፅታ ያላቸው ባይሆኑም እንኳ የህገመንግስቱን መንፈስ ሊጎዱ የሚችሉ አንዳንድ ተግባራት መከናወናቸውን ማስተዋል ከባድ አይደለም።
በተለይም የፌደራላዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ባህል ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ ለሚገኝ ህብረተሰብ ወደመቃብር የወረዱትን የአፄዎቹና ወታደራዊው መንግስት የጉዞና የሀገር ግንባታ አሻራ የሚያስታውሱ በዚሁ በእኛ ዘመን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት (መሪ ሎቄን በሲኤምሲና በሰንሻይን መተካት፣ ካራን በሀያት፣ ፉሪን በጀርመን አደባባይ፣ በሻሌን በሰሚት ወዘተ በመሰሉ የባእድ ስሞች እንዲተኩ የማድረግ ተግባራት)እዚህም እዚያም ብቅ ሲሉ ማየት መራር እውነታ በመሆኑ ፈጣን እርማትን የሚሹ የአደባባይ እውነታ መሆናቸውን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።
በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ከመጣው የልማት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ የኦሮሞ ተወላጆች የልማት ተነሺዎችን በተመለከተ መስተዳድሩ የሚከተለው የካሳ ስርዓትና የምትክ ቦታ መስጠት ተግባራት መኖራቸው የሚካድ ባይሆንም አጠቃላይ ሂደት በልማት ተነሺዎች ላይ የሚያሳድረው ትውልድ ተሻጋሪ ጉዳቱን ለመቀነስ ሊወሰዱ ከሚገባቸው እርምጃዎች አንፃር ሰፊ ክፍተቶች ያሉበት ነው። ነባር ተወላጆችን አስመልክቶ በአህጉርና በአለምአቀፍ ደረጃ የወጡ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችም [1. Art. 20 of the African Charter of Human and Peoples Rights of 1981, 2. International Human Rights, Indeginous rights, rights to self Determination] ጋር ይጋጫል። በተለይም ይህ ሂደት ከመቶ አመታት በፊት በተካሄደ የግፍ ወረራ ከነባር ነዋሪነት ወደ አናሳ ብሔርነት እየተቀየረ ለመጣው የፊንፊኔ ነባር ተወላጅ የህልውና ጉዳይም በመሆኑ መስተዳድሩ የሚከተለው የካሳ ስርዓትና የምትክ ቦታ አሰጣጥ ተግባራትን በተጨማሪ ደጋፊ የማስተካከያ እርምጃዎች የሕግ ማዕቀፍ ማበጀትን የሚሻ ጉዳይ ነው።
ለዚህ ማሳያነት ከማዕከላዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን በተገኘው መረጃ መሰረት 1999 . በተካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ከአዲስ አበባ ከተማ 2,739,551 ነዋሪዎች ውስጥ አማራ 1,288,895(47%) ኦሮሞ 534,547(19.5%) ጉራጌ 447,777 (16.3%) ትግሬ 169,082(6.2%) እና ሌሎች 299,150(10.1%) ሲሆን የኦሮሞ ተወላጅ በተወለደበት መሬቱ ላይ አናሳ መሆኑ አንድ ማሳያ ነው።
ስለሆነም የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ላይ ያለውን የታሪክና የህግ መብት የሚያረጋግጥለት ‹‹የልዩ ጥቅም›› ሥረ-ነገር በአንድ ፊት ከታሪክ መሰረት የሚነሳ የመሆኑን ያህል ሁለተኛው የመብት መነሾ የአዲስ አበባ መስተዳድር የኦሮሞ መሬት አንድ አካልና እምብርት መሆኗ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማም በመሆኗ ጭምር የሚመነጭ መሆኑን መረዳት ተገቢ ይሆናል። የአዲስ አበባን ነዋሪ ውሀ ሲያጠጣ የኖረው የገፈርሳ እና የለገዳዲ ውሀ በደጁ የሚያልፈው የኦሮሞ አርሶአደር ከውሀው እንዲጠቀም ለማድረግ በቂ ጥረቶች አለመደረጋቸው እና ከተማዋ ነባር የኦሮሞ አርሶ አደሮችን እያፈነቀለች ከጊዜ ወደ ጊዜ መስፋትዋ መሬት ላይ ያለው ገሃድ ሀቅ በመሆኑ ሁሌም ሀብትን ምክንያት አድርጎ ማቅረብ የሚቻል አይደለም። በፊንፊኔ/አዲስ አበባ የሚቋቋሙት ኢንዱስትሪዎች ወደ አጎራባች የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚለቀቀውን የተበከለ ፍሳሽ ለማከም በምትኩም የተጠቃሚነትን ያህል የፊንፊኔ ባለቤትና የኦሮሞ ተወላጅ በአዲስ አበባ የመንግስት /ቤቶች አገልግሎትን በቋንቋው እንዲያገኝ ለማድረግ በጥቂት አጋዥ እርምጃ ቢደገፍ መልካም ይሆን ነበር።

TSAGAYE ARAARSAATIIN.



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman